Friday, March 1, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ዓለምድብልቅልቅ ስሜት የፈጠረው የእስራኤል ሃማስ ተኩስ አቁም ስምምነት

ድብልቅልቅ ስሜት የፈጠረው የእስራኤል ሃማስ ተኩስ አቁም ስምምነት

ቀን:

ከወር በላይ ባስቆጠረው የእስራኤል ሃማስ ጦርነት በተለይ ፍልስጤማውያን መከራን ተቀብለዋል፡፡ ጋዛ የደምና የፍርስራሽ ምድር ሆናለች፡፡ እስራኤል በጥቅምት መጀመሪያ ‹‹ድንገተኛ የሮኬት ጥቃት ፈፅሞ 1‚200 ዜጎቼን ገድሏል፣ 240 አግቷል›› ያለችውንና በፍልስጤም ጋዛን የሚያስተዳድረውን ሃማስ እስካላንበረከከች ጥቃት ከመፈጸም አልቦዝንም ብላ ጋዛን ረፍት ነስታ ከርማለች፡፡

ችግሩን ለመፍታት ከመካከለኛው ምሥራቅ አገሮች መሪዎች ጋር የመከረችው አሜሪካም ጦርነቱ ይቁም ብላ አልወሰነችም፡፡ ይልቁንም የጦርነቱ መቆም ሃማስ መልሶ እንዲደራጅ ዕድል ይፈጥራል ስትል ነው አቋሟን የገለጸችው፡፡

ድብልቅልቅ ስሜት የፈጠረው የእስራኤል ሃማስ ተኩስ አቁም ስምምነት | Ethiopian Reporter | ሪፖርተር
በእስራኤል በጥቅምት መጀመርያ ከሃማስ በተተኮሰ ሮኬት ቤቶች ወድመዋል (ሮይተርስ)

በዚህ ሁሉ የፖለቲካ ሽኩቻ ከእስራኤል ወገን ቤቶች ፈራርሰው፣ 1‚200 ሰዎች ተገድለዋል፡፡ የፍልስጤማውያን ውድመት ደግሞ ልቋል፡፡ 14‚500 ፍልስጤማውያን በእስራኤል የቦምብ ጥቃት አልቀዋል፡፡ ከእነዚህ ከአራት ሺሕ የማያንሱት ሕፃናት ናቸው፡፡

- Advertisement -

Video from Enat Bank Youtube Channel.

በተለያዩ ዓለም አቀፍ መገናኛ ብዙኃን የሚለቀቁ ተንቀሳቃሽ ምሥሎችም ሆኑ ሮቶግራፎች የጋዛን መውደም፣ የፍልስጤማውያንን መሰቃየት አስቃኝተዋል፡፡

የሕፃናት አስክሬን ከፍርስራሽ ስር ሲወጣ፣ አባትና እናት በድን ልጃቸውን ይዘው ዕንባ ሲራጩ፣ ሕፃናት ወላጅ ሞቶባቸው የሚይዙት የሚጨብጡት ሲጠፋቸው የሚያሳዩ የፍልስጤማውያንን መከራ ለዓለም ሕዝብ አጋርተዋል፡፡

አይሁዳውያንን ጨምሮ በርካታ ሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች የእስራኤልን ድፍን የአየር ጥቃት ኮንነዋል፡፡ በንፁኃን ላይ የሚፈጸም የቦምብ ድብደባ ፍትሐዊ አይደለም ሲሉ ድምፅ አሰምተዋል፡፡

ኃያላን አገሮች ደግሞ በእስራኤልና በፍልስጤም መካከል የተጀመረው ጦርነት ይቁም ብሎ ለመወሰን የሐሳብ መከፋፈል ውስጥ ገብተዋል፡፡

በኳታር አደራዳሪነት ከዓርብ ኅዳር 14 ቀን 2016 ዓ.ም. ጀምሮ በእስራኤልና በፍልስጤም ሃማስ መካከል የተደረሰው የአራት ቀናት የተኩስ አቁም ስምምነት ለፍልስጤማውያን ዕፎይታን ሰጥቷል፣ ድብልቅልቅ ስሜትን ፈጥሯል፡፡

ቢቢሲ እንደዘገበው፣ በጋዛ የሚኖሩ ፍልስጤማውያን ከወር በላይ በዘለቀው ጦርነት የተራቆተውን ቤታቸውን ለመሙላት ራሳቸውን ከቦንብ ጥቃት ለመደበቅ ከነበሩበት ወጥተዋል፡፡

ከመሠረታዊ ፍላጎታቸው ጎን ለጎን የጠፉ ቤተሰቦቻቸውን ፍለጋ ይዘዋል፡፡ ከወደሙ መንደሮች ውስጥ መኖሪያቸው ይኑር አይኑር ለማወቅ ወደቀዬአቸው አቅንተዋል፡፡ አንዳንዶች ወደ ባህር ዳርቻ ወርደዋል፡፡ አንዳንዶች ከፈራረሱ ቤቶቻቸው ውስጥ የሚጠቅም ነገር ካገኘን በሚል በፍለጋ ተጠምደዋል፡፡

በኳታር አደራዳሪነት የተደረሰው የአራት ቀናት ተኩስ አቁም ስምምነት እስራኤላውያን ታጋቾችን፣ በእስራኤል እስር ቤት የሚገኙ ፍልስጤማውያንን መልቀቅን ያካትታል፡፡

ለፍልስጤማውያን መሠረታዊ ፍላጎቶች ፍጆታ የሚውሉ ቁሳቁሶችን ማስገባት የስምምነቱ አካል ሲሆን፣ በዚህም ነዳጅና የምግብ ማብሰያ ጋዝ ወደ ጋዛ ተጉዟል፡፡ የዕርዳታ ምግብና ቁሳቁስም እንዲሁ፡፡

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ጦርነቱ ከተጀመረ ከ15 ቀናት በኋላ ካስገባው ዕርዳታ አሁን ላይ በእጅጉ የላቀ ማስገባቱን አስታውቆ፣ በቂ አለመሆኑንና ተጨማሪ እንደሚያስፈልግ ጠቁሟል፡፡

ምግብ፣ ውኃና መድኃኒት የጫኑ መኪኖች ወደ ጋዛ ተጉዘዋል፡፡ እያንዳንዱ መኪና ከባድ ፍተሻ ተደርጎለት የሚገባ መሆኑ፣ መጓተት ቢፈጥርም፣ የፍልስጤም ቀይ ጨረቃ፣ ምግብ፣ ውኃና መድኃኒት የጫኑ 61 መኪኖች ከራፋህ ተነስተው ወደሰሜን ጋዛ ማቅናታቸውን ገልጿል፡፡ ነዋሪዎችም ዕርዳታ መቀበል ጀምረዋል፡፡

የተኩስ አቁሙ መደረጉ ደስታና ሐዘን የቀላቀለበት ስሜትን ፈጥሯል፡፡ በርካቶች ቤት አለን ብለው ወደ ቀዬአቸው ሲመለሱ፣ ፍርስራሽ ጠብቋቸዋል፡፡ የሚወዷቸውን ሰዎች በነፍሰ ሥጋ ሳይሆን አስከሬናቸውን ከፍርስራሽ ስር አግኝተዋል፡፡

በለበሱት ብቻ ራሳቸውን ለማትረፍ በየመጠለያው የገቡ በሚሊዮን ከሚቆጠሩ ፍልስጤማውያን ወደቀዬአቸው ከተመለሱት በተኩስ አቁሙ ደስታ፣ በቀዬአቸው ወደፍርስራሽነት መቀየርና በወዳጆቻቸው ሞት በሐዘን በተደበላለቀ ስሜት ውስጥ እንደሚገኙ መታዘቡን ቢቢሲ አስታውቋል፡፡ በእስራኤል ወገን ከእገታ የተለቀቁ ቤተሰቦች ይጠብቁናል ብለው የሚያስቧቸው ወገኖቻቸው መሞታቸውን ሰምተዋል፡፡ 

የተኩስ አቁም ስምምነቱ ለ48 ተጨማሪ ሰዓታት የተራዘመ ሲሆን፣ ነገ ኅዳር 20 ቀን 2016 ዓ.ም. ያበቃል ተብሎ ይታሰባል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

[ክቡር ሚኒስትሩ ወደ መኖሪያ ቤታቸው ሲገቡ ባለቤታቸው በቴሌቪዥን የሚተላለፈውን ዜና በመደነቅ እየተመለከቱ አገኟቸው]

እንዲያው የሚደንቅ ነው እኮ። ምኑ? ዜና ተብሎ በቴሌቪዥን የሚተላለፈው ነገር ነዋ፡፡ ምኑ...

በኦሮሚያ የሚፈጸሙ ግድያዎችና የተጠያቂነት መጥፋት

የካቲት 11 ቀን 2016 ዓ.ም. ቢሾፍቱ አቅራቢያ በሚገኘው የዝቋላ...

የኢትዮጵያ መዋዕለ ንዋይ ገበያ ከሚያስፈልገው ካፒታል ውስጥ 90 በመቶውን ሰበሰበ

እስካሁን 15 ባንኮች የመዋዕለ ንዋይ ገበያው ባለድርሻ ሆነዋል የኢትዮጵያ መዋዕለ...

አዲሱ የንብ ባንክ ቦርድ የባንኩን ካፒታል በአሥር ቢሊዮን ብር ለማሳደግ ማቀዱ ተሰማ

አዲሱ የንብ ኢንተርናሽናል ባንክ የዳይሬክተሮች ቦርድ የባንኩን ካፒታል በአሥር...