Monday, February 26, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊበከተማዋ ለመተግበር አዳጋች የሆኑ ደንብና መመርያዎች

በከተማዋ ለመተግበር አዳጋች የሆኑ ደንብና መመርያዎች

ቀን:

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አዳዲስ መመሪያዎችን እያወጣ ተግባር ላይ እንዲውል ሲሠራ ይስተዋላል፡፡ በቅጣት፣ በማስጠንቀቂያና በምክር የታጀቡ፣ በርካታ ሕጎችና መመርያዎችም አዳዲስ አሠራሮች ያሉ ሲሆን አንዳንዶቹ በከፊልም ቢሆን ሲተገበሩ ይስተዋላል፡፡

መንገድ ዳር ቆሞ ሽንት መሽናት 200 ብር ቅጣት ይጠብቀዋል የሚል መመርያ ቢኖርም ዛሬም የከተማዋ ጥጋጥግ፣ የታክሲና አውቶቡስ መናኸሪያ ከችግሩ አልፀዱም፡፡

በከተማዋ ለመተግበር አዳጋች የሆኑ ደንብና መመርያዎች | Ethiopian Reporter | ሪፖርተር

- Advertisement -

Video from Enat Bank Youtube Channel.

 በየቦታው ሽንታቸውን የሚሸኑ ማየትም የተለመደ ነው፡፡ ወዴት ሄደን እንሽና? የሕዝብ ሽንት ቤት የለም፣ “ሽንት መሽናት ያስቀጣል” የሚለውን ሕግ ከማውጣት በፊት የሕዝብ መፀዳጃ ቤት መሠራት ነበረበት የሚሉ አስተያየቶችም ይቀርባሉ።

ለመሆኑ እነዚህና ሌሎች የወጡ ደንቦች እንዴትና በማን ፀደቁ? ዓላማቸውስ ምንድነው? የሚሉትን ሪፖርተር የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለሥልጣንን ጠይቆ ነበር።

በማለት የባለሥልጣኑ የቁጥጥር ዕርምጃ አወሳሰድ ዘርፍ ኃላፊ አቶ ደሳለኝ ፉፋ እንደሚሉት፣ ቀደም ሲል ከነበሩት ደንቦችና መመርያዎች በተጨማሪ ዘጠኝ ዓበይት ተጨማሪ ሕጎችን በማፅደቅ ወደ ሥራ ገብተዋል፡፡ የወጡ ሕጎችንና መመርያዎችን የተላለፈ ደግሞ በመመርያው የተቀመጠውን የገንዘብ ቅጣት እንዲከፍል ይደረጋል፡፡

ሶፍት፣ ወረቀት፣ የአውቶብስ ትኬት፣ የታሸገ ውኃ መያዥያ ፕላስቲክና የመሳሰሉትን ቆሻሻዎች በመዲናዋ ሲጥል የተገኘ የገንዘብ ቅጣት ይጠብቀዋል ብለዋል፡፡

የወጡ ሕጎችን ተከትሎ ከተለያዩ የማኅበረሰብ ክፍሎች የተለያዩ አዎንታዊና አሉታዊ አስተያየቶች ሲቀርቡ ይስተዋላል።

 የአፍሪካ መዲና የሆነችውን አዲስ አበባ እንደ ስሟ “አዲስ አበባ” ለማድረግ የወጣው መመርያ አስፈላጊ ነው፣ በአግባቡ ሥራ ላይ መዋል ይኖርበታል፣  ከተለያዩ ደረቅና ፈሳሽ ቆሻሻዎች የፀዳች ከተማ መሆን ይኖርባታል፣ በማለት የሚደግፉ አካላት ሲኖሩ፣ በሌላ በኩል ይህ መሆኑ ጥሩ ሆኖ ሳለ ነገር ግን መመርያው ሲወጣ መደረግ የነበረበት ቅድመ ዝግጅት ሳይደረግ ባለ ጉዳዮች ተሰባስበው ሳይወያዩ መውጣቱ ተግባራዊነቱን ይፈትነዋል የሚሉ አሉ፡፡ በኅብረተሰቡ ዘንድ ሰፊ የግንዛቤ ማስጨበጥ ሥራ አልተሠራም፣ ቆሻሻ መጣል ያስቀጣል ከመባሉ በፊት በቂ የቆሻሻ ማጠራቀሚያ መኖር ነበረበት በማለትም ይናገራሉ።

በከተማዋ ለመተግበር አዳጋች የሆኑ ደንብና መመርያዎች | Ethiopian Reporter | ሪፖርተር

ከወጡ መመርያዎች መካከል ሰሞኑን በከተማዋ በስፋት እየተተገበረ የሚታየው  የመንገድ ላይ ማስታወቂያን ማስወገድ ተግባር ይገኝበታል።

ሕገወጥ የሚባሉት ማስታወቂያዎች የትኞቹ ናቸው የሚለውን አቶ ደሳለኝ ሲያስረዱ፣ ከከተማ ግንባታና ቁጥጥር ባለሥልጣን ፈቃድ ሳይኖራቸው ማንኛውንም የማስታወቂያ ወረቀት በድልድዮች፣ በእግረኛ መንገዶች ማንጠልጠልና የማስታወቂያ ቋሚዎችን መትከልን ያጠቃልላል ብለዋል፡፡

በሌላ በኩል በራሪ ወረቀቶችን በብሮሸር ወይም በማንኛውም መንገድ ማሠራጨትና እንዲሠራጭ ማድረግ እንዲሁም ማባዛትን ጨምሮ ሲሠራ የተገኘ ማንኛውም ግለሰብም ሆነ ድርጅት ቅጣት ይጠብቀዋል ያሉት አቶ ደሳለኝ፣ ነገሩ በቅጣት ብቻ አይቀርም በማለት አክለዋል።

የገንዘብ ቅጣት ያስከትላሉ የተባሉት እነዚህ ማስታወቂያዎች ግን ከግንባታና ቁጥጥር ባለሥልጣን ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ ወስደው በተቀመጠላቸው ጊዜ ግብር ከፍለው የሚያስገቡ ከሆኑ ማንጠልጠልም ሆነ መለጠፍ ይችላሉ ተብሏል፡፡

ኃላፊው ይህንን ይበሉ እንጂ በተለይ በማስታወቂያ ሥራ ላይ ተደራጅተው ትልልቅ ሥራዎችን እየሠሩ የሚገኙ ድርጅቶችም ሆኑ ግለሰቦች ችግር ውስጥ መግባታቸውን ተናግረዋል።

የኢትዮጵያ የማስታወቂያ ሥራ ማኀበር በበኩሉ፣ በአስተዳደሩ በኩል ታውቆ፣ ተጠንቶ ደረጃውን በጠበቀ መልክ ተመርተው ለማስታወቂያ ሥራ እንዲውሉ የተፈቀዱ ትልልቅ ቢልቦርዶች ጭምር በአሁን ሰዓት ተነስተው በስክሪን ማስታወቂያዎች እንዲተኩ የተወሰነበት አግባብ ባለሙያዎቹን አስደንግጧል፣ ለህልውና አደጋም ሊዳርገን የሚችል መሆኑ አሳስቦናል ሲል ቅሬታውን አቅርቧል።

በከተማ አስተዳደሩ ዕውቅናና ውሳኔ ደረጃ መጠበቁ ተረጋግጦ በሕጋዊ የማስታወቂያ ድርጅቶች ተመርተው እንዲተከሉ የተደረጉ፣ በአሁን ሰዓት በምርት ሒደት ውስጥ የሚገኙ ትልልቅ ቢልቦርዶች በድንገት እንዲነሱ ወይም ከአሁን በኋላ እንዳይታዩ የመወሰኑ ጉዳይ በዘርፉ የተሰማራን፣ ሠርተው በየዓመቱ ከፍተኛ ግብር ለመንግሥት የሚያስገቡ ድርጅቶችን ህልውና አደጋ ላይ የጣለ ውሳኔ ነው በማለት ማኅበሩ አስታውቋል።

እንደ ማኅበሩ ፕሬዚዳንት አለባቸው ወዳይ በዘርፉ የተሰማሩ ድርጅቶች በአስተዳደሩ የተቀመጠውን ደረጃ ጠብቀው፣ ለአንድ የቢልቦርድ ማስታወቂያ በነፍስ ወከፍ ከ3‚000 ሺሕ ብር በላይ ወጪ እያደረጉ የተተከሉ ሲሆን፣ ሥራዎቹ ከውበትና ደረጃቸውን ከመጠበቅ አንፃር እንከን የሚወጣላቸው አልነበሩም። ነገር ግን ጥቂት ግለሰቦችን ለመጥቀም በሚመስል መልክ ከፍተኛ መዋዕለ ንዋይ የፈሰሰባቸው የቢልቦርድ ማስታወቂያዎች ከያሉበት ነቃቅሎ በመጣል ከተማዋ በስክሪን ማስታወቂያ ታሸብርቅ ብሎ መወሰን በእጅጉ ኃላፊነት የጎደለው ውሳኔ ሆኖ በማግኘቱ በውሳኔው ላይ ያለውን ቅሬታ አሰምቷል።

ከውሳኔው በፊት ከዘርፉ ዋንኛ ባለድርሻዎች ጋር ምክክር አለመደረጉ በእጅጉ እንዳሳዘናቸው፣ ከሁለት ሺሕ በላይ ሕጋዊ የማስታወቂያ ድርጅቶችንና ቤተሰቦቻቸውን፣ በሺ የሚቆጠሩ ሠራተኞቻቸውን እንዲሁም ከዘርፉ በተዘዋዋሪ ተጠቃሚ የሆኑ አካላትን የሚመለከት መሆኑን፣ በእነዚህ ወገኖች ሥራ መጎዳት የስንት ወገኖችን ቤት እንደሚዘጋ መዘንጋት እንደሌለበትም አክለዋል፡፡

ማኅበሩ ቢልቦርዶች እንዲፈርሱ የተወሰነው ውሳኔ ሙሉ ለሙሉ ከመተግበሩ በፊት የከተማው የዲዛይንና ግንባታ ቁጥጥር ባለሥልጣን፣ የደንብ ማስከበር ጽሕፈት ቤት ኃላፊዎች የዘርፉ ተዋንያንን ባሳተፈ መልክ ምክክር እንዲያደርጉ ጠይቀዋል።

በሌላ በኩል ደንብ አስከባሪዎች በትንንሽ ሱቆች ሳይቀር በመዞር ማንኛውንም ጽሑፍ  የያዘ ወረቀትና ብሮሸር ያለ አግባብ እየቀደዱ ነው ሲሉ የከተማዋ አንዳንድ ነጋዴዎች ተናግረዋል።

ስሜ እንዳይጠቀስ ያለች በሴቶች የፀጉር ሥራ ላይ የተሰማራች ወጣት፣ ‹‹ለምሠራበት ሥራ የንግድ ፈቃድ አውጥቼ የሚጠበቅብኝን የመንግሥት ግብር እየከፈልኩ፣ በየወሩ ኪራይ በሚጨምር ቤት ውስጥ ተቀምጬ  ምንም ዓይነት ትርፍ ቦታ ለማትጠይቅ ባነር ተጨማሪ ገንዘብ መክፈል አለብሽ ካልከፈልሽ ወደ ውስጥ አስገቢ ተብየ አንስቻለሁ፤›› ስትል ታስረዳለች።

በተመሳሳይ ሌሎች ስማችን ቢጠቀስ ሌላ ችግር ያስከትላል ያሉ ነጋደዎች ተመሳሳይ ችግር እንደገጠማቸው ተናግረዋል። ‹‹የከተማ ውበትን ለማስጠበቅ የሚለው ሐሳብ እየተደረገ ካለው እንቅስቃሴ ጋር በፍፁም የሚጋጭ ነው፤›› ያሉት አስተያየት ሰጭዎቹ፣ ከተማዋ የበለጠ ውበቷ የሚጠበቀው ነጋደ ተረጋግቶ ሲሠራና ከሚያገኘው ገቢ በአግባቡ ግብር ሲከፍል ነው ብለዋል።

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የመጣንበትና አብረን የምንዘልቅበት የጋራ እሴታችን ለመሆኑ ነጋሪ ያስፈልጋል ወይ?

በኑረዲን አብራር በአገራችን ለለውጥ የተደረጉ ትግሎች ከመብዛታቸው የተነሳ ሰላም የነበረበት...

አልባሌ ልሂቃንና ፖለቲከኞች

በበቀለ ሹሜ በ2016 ዓ.ም. ኅዳር ማክተሚያ ላይ ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ...

አሜሪካ የኢትዮጵያ የባህር በር ጥያቄ ተገቢነት ቢኖረውም ከጎረቤት አገሮች ጋር በሚደረግ ንግግር መሆን አለበት አለች

መንግሥትን ከፋኖና ከኦነግ ሸኔ ጋር ለማነጋገር ፍላጎቷን ገልጻለች የኢትዮጵያ የባህር...