Monday, February 26, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ስፖርትበቫሌንሺያው ማራቶን የሚጠበቀው ቀነኒሳ በቀለ

በቫሌንሺያው ማራቶን የሚጠበቀው ቀነኒሳ በቀለ

ቀን:

የፓሪስ ኦሊምፒክ የወራት ዕድሜ ቀርቶታል፡፡ የኮቪድ-19 ወረርሽኝ መከሰት በውድድር ፕሮግራሞች ላይ ሽግሽግን በማስከተሉ የዓለም ሻምፒዮንና የዓለም ኦሊምፒክ ጨዋታዎች የሚካሄዱበት ጊዜ ተቀራርቧል፡፡ በዚህም የተነሳ የዓለም አትሌቶች ውድድሮች የተደራረቡባቸው ቢሆንም፣ በአትሌቲክስ ሕይወት የሚፈልጉትን ስኬት ለማሳካት ዕድል እንደሚሰጣቸው ግን ይታመናል፡፡

በቫሌንሺያው ማራቶን የሚጠበቀው ቀነኒሳ በቀለ | Ethiopian Reporter | ሪፖርተር
ቀነኒሳ በቀለ በቫሌንሺያ ማራቶን ይካፈላል

እ.ኤ.አ. ከ2019 በኋላ የቶኪዮ ኦሊምፒክ በመቀጠልም የ2022 የኦሪጎን ዓለም ሻምፒዮና፣ እንዲሁም 19ኛው የቡዳፔስት ዓለም ሻምፒዮን መካሄዳቸው አትሌቶች በአጭር ጊዜ ውስጥ ያላቸውን አቅም እንዲያሳዩ ረድቷቸዋል፡፡

በተለይ አትሌቶች ከትራክ ውድድር ይልቅ ወደ ጎዳና ፊታቸውን ባዞሩበት በዚህ ዘመን፣ በዓለም ሻምፒዮና በተሳተፉ በአንድ ዓመት ልዩነት የኦሊምፒክ ጨዋታዎች ለመወዳደር መቻላቸው እንደ ዕድል የሚቆጠር ነው፡፡

- Advertisement -

Video from Enat Bank Youtube Channel.

ከሐምሌ 19 እስከ ነሐሴ 6 ቀን 2016 ዓ.ም. በፈረንሣዩዋ ፓሪስ ከተማ የሚደረገው የኦሊሚፒክ ጨዋታ ላይ በርካታ የዓለም ከዋክብቶች እንደሚሳተፉ ይጠበቃል፡፡ በዚህ የኦሊምፒክ ጨዋታው ላይ ለመካፈል የሚያበቁ በርካታ የቅድመ ማሟያ ውድድሮች በተለያዩ ከተሞች እየተስተናገዱ ይገኛሉ፡፡

ከእነዚህም መካከል በስፔን ቫሌንሺያ የሚሰናዳው ዓለም አቀፍ የአዋቂዎች የማራቶን ውድድር ይጠቀሳል፡፡ ዘንድሮ ዋና ዋና (Major Marathon Race) የማራቶን ውድድሮች በበርሊንግ ቺካጎ፣ በለንደን ቦስተን፣ እንዲሁም ኒውዮርክ ከተሞች የተከናወኑ ሲሆን አዳዲስ ክብረ ወሰኖችም ተመዝግበዋል፡፡

በስፔን ቫሌንሺያው በተሰናዳው ውድድር በፓሪስ ኦሊምፒክ መሳተፍ የሚያስችላቸውን ሰዓት ያሟሉና የመሳተፍ ዕድል እንዳላቸው ቅድመ ግምት ያገኙ አትሌቶች ተሳታፊ እንደሚሆኑ ታውቋል፡፡

ኅዳር 23 ቀን 2016 ዓ.ም. የሚከናወነው የቫሌንሺያ ማራቶን የተለየ ግምት ያገኘና ተጠባቂ ሆኗል፡፡

የማራቶን ውድድሩን ተጠባቂ ካደረጉት ምክንያቶች ዋነኛው የሦስት ጊዜ የኦሊምፒክ ሻምፒዮናው፣ እንዲሁም የአምስት ጊዜ የዓለም ሻምዮናውና የምንጊዜም የረዥም ርቀት ድንቅ አትሌት የሆነው ቀነኒሳ በቀለ መሳተፉ ነው፡፡

በትራክ 5000 እና 10000 ሜትር፣ በአገር አቋራጭ፣ እንዲሁም በተለያዩ የማራቶን ውድድሮች በመሳተፍ በርካታ ክብረ ወሰኖችን በእጁ የጨበጠው ቀነኒሳ፣ በቫሌንሺያ ማራቶን ተሳትፎው በኋላ በፓሪስ ኦሊምፒክ በማራቶን አገሩን መወከል እንደሚፈልግ ተናግሯል፡፡

በረዥም ርቀት ሩጫ በርካታ ድሎችን መጎናፀፍ የቻለው ቀነኒሳ፣ የፓሪስ ኦሊምፒክ ተሳትፎውን ለማሳካት የቫሌንሺያውን የማራቶን ውድድር መወጣት ይጠበቅበታል፡፡

የዓለም ሦስተኛው ፈጣን ውድድር የሆነው የቫሌንሺያው ማራቶን ዘንድሮ በርካታ የፈጣን ሰዓት ባለቤት የሆኑ አትሌቶችን እንደሚያስተናግድ ታውቋል፡፡

ቀነኒሳ 41ኛው ዕድሜ ላይ የሚገኝ ሲሆን፣ በጉዳት ምክንያት ከተለያዩ የጎዳና ውድደሮች ርቆ ቆይቷል፡፡  

ኢትዮጵያን በማራቶን በኦሊምፒክና በዓለም አቀፍ ሻምፒዮን መወከል ፍላጎት ቢኖረውም ሳይሳካለት የቀረው ቀነኒሳ፣ ዘንድሮ በፓሪስ ያሳካው እንደሆነ የሚወስነው የቫሌንሺያ ማራቶን ተሳትፎ ነው፡፡  

ሆኖም በውድድሩ የ5000 እና 10 ሺሕ ሜትር የክብረ ወሰን ባለቤቱ ጆሽዋ ቺፕቴጌን ጨምሮ ከ2:05 በታች ሰዓት ያመጡ አትሌቶች ከፍተኛ ፉክክር ይጠብቀዋል። በተለይ በማራቶን የመጀመሪያ ተሳትፎ የሚያደርገው ዑጋንዳዊው ጆሽዋ፣ ቀነኒሳን ይፈትነዋል ከተባሉት አትሌቶች መካከል ይጠቀሳል።

ከዚህም ባሻገር በ2:04.29 ሰዓት ባለቤቱ አሌክሳንደር ሞቲሶ፣ 2:03.36 በመግባት የግሉን ምርጥ ሰዓት ያመጣው ሲሳይ ለማ፣ 2:04.02 ሰዓት ያለው ልዑል ገብረ ሥላሴ፣ 2:04.53 ያለው ጫሉ ደስ እንዲሁም 2:04.53 ምርጥ ሰዓቱን ያስመዘገበው ቲታስ ኪፕሪቶ ተጠባቂ አትሌቶች ናቸው።

በውድድሩ ከሚጠበቁት አትሌቶች  መካከል ኬንያዊው ኪቢውት ኪንዳይ አንደኛው ሲሆን በቫሌንሺያ ግማሽ ማራቶን መሳተፍ ልምድ አለው። በስፔን ምድር ጥሩ ሰዓት አምጥቶ ማሸነፍ የቻለ ወይም ደረጃ ውስጥ መካተት የቻለ አትሌት፣ ለፖሪስ ኦሊምፒክ የመመረጥ ዕድል ይኖረዋል። በፓሪስ  ኢትዮጵያን ለመወከል ከሚወዳደሩ አትሌቶች መካከል  ቀነኒስ ይሳካለታል? አይሳካለትም? የሚለው ቫሌንሺያ ማራቶን ምላሽ ይኖረዋል። 

‹‹ቀነኒሳ ከሩጫ ዓለም ይሰናበታል›› የሚል አስተያየት ሲዘዋወር የቆየ ቢሆንም፣ ምናልባት በፓሪስ ኦሊምፒክ መካፈል ከቻለ ከሩጫው ዓለም መሰናበቻው ሊሆን ይችላል የሚል ግምት አይሏል፡፡ 

በሌላ በኩል የቫሌንሺያ ማራቶን የሴት አትሌቶችንም የፖሪስ ኦሊምፒክ ተሳትፎ ይወስናል። በዚህም የኢትዮጵያ አትሌቶችን ጨምሮ የተለያዩ አትሌቶች ወደ ፓሪስ ኦሊምፒክ ሊያስገባቸው የሚያስችላቸውን የማሟያ ሰዓት ለማምጣት ስፔን ይከትማሉ።

በሴቶቹ ከሚጠበቁ አትሌቶች መካከል በቡዳፔስት ዓለም ሻምፒዮን መካፈል የቻለችውና 2:16.56 የራሷን ምርጥ ሰዓት የያዘችው ፀሐይ ገመቹ፣ የ10 ሺሕ ሜትር የዓለም ሻምፒዮናዋ አልማዝ አያና (2:17.20)፣ ወርቅነሽ ደገፋ (2:17.41)፣ እንዲሁም 2:19.10 ምርጥ ሰዓቷ የሆነው ሕይወት ገብረ ኪዳን ይጠበቃሉ። 

ከዚህም ባሻገር በአጭር ርቀት የምትታወቀው ቦሰና ሙላት የመጀመሪያ የማራቶን ተሳትፎዋን ታደርጋለች። 

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የመጣንበትና አብረን የምንዘልቅበት የጋራ እሴታችን ለመሆኑ ነጋሪ ያስፈልጋል ወይ?

በኑረዲን አብራር በአገራችን ለለውጥ የተደረጉ ትግሎች ከመብዛታቸው የተነሳ ሰላም የነበረበት...

አልባሌ ልሂቃንና ፖለቲከኞች

በበቀለ ሹሜ በ2016 ዓ.ም. ኅዳር ማክተሚያ ላይ ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ...

አሜሪካ የኢትዮጵያ የባህር በር ጥያቄ ተገቢነት ቢኖረውም ከጎረቤት አገሮች ጋር በሚደረግ ንግግር መሆን አለበት አለች

መንግሥትን ከፋኖና ከኦነግ ሸኔ ጋር ለማነጋገር ፍላጎቷን ገልጻለች የኢትዮጵያ የባህር...