Thursday, February 29, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ስፖርትዓለም አቀፉ የቴኒስ ሻምፒዮን በአዲስ አበባ ይካሄዳል

ዓለም አቀፉ የቴኒስ ሻምፒዮን በአዲስ አበባ ይካሄዳል

ቀን:

የአዲስ አበባ ቴኒስ ክለብ ከኢትዮጵያ ቴኒስ ፌዴሬሽን ጋር በመተባበር፣ የጂኤ 30 የዓለም የታዳጊዎች ቴኒስ ውድድርን በአዲስ አበባ ሊያስተናግዱ ነው፡፡

በውድድሩ ዕድሜያቸው ከ13 እስከ 18 ዓመት የሆኑ ታዳጊዎች በሁለቱም ፆታ ተካፋይ እንደሚሆኑ ለማወቅ ተችሏል፡፡

በውድድሩ 20 አገሮችን የሚወክሉ ከ40 በላይ ተጫዋቾች ተሳታፊ የተገለጸ ሲሆን፣ ተወዳዳሪዎቹ ከህንድ፣ እስራኤል፣ አውስትራሊያ፣ አሜሪካ፣ ስፔን፣ ፊንላንድ፣ ግብፅ፣ ፖላንድ፣ ሩሲያ፣ እንዲሁም ሴሪላንካ የተወከሉ መሆናቸው ተረጋግጧል፡፡

- Advertisement -

Video from Enat Bank Youtube Channel.

ዓለም አቀፍ ሻምፒዮናው እ.ኤ.አ. ከኅዳር 27 እስከ ታኅሳስ 9 ቀን 2023 ድረስ በአዲስ አበባ ቴኒስ ክለብ እንደሚካሄድም ለመረዳት ተችሏል፡፡ ከተመሠረተ 53 ዓመታት ያስቆጠረው አዲስ አበባ ቴኒስ ክለብ ከኢትዮጵያ ቴኒስ ፌዴሬሽን ጋር በጋራ በመሆን ውድድሩን አዘጋጅቷል፡፡

ኢትዮጵያ ይህንን ዓለም አቀፍ ውድድር ማስተናገድ መቻሏ ኢትዮጵያውያን ተጫዋቾች ውድድር እንዲያገኙ ከማስቻሉም በላይ አሠልጣኞች ዓለም አቀፍ ልምድ እንዲያገኙ ዕድል ይሰጣል ተብሏል፡፡ ውድድሩ አፍሪካ ላይ ከኢትዮጵያ ጋር በተመሳሳይ በቶጎ፣ ዚምባቤና ሞሮኮ ይከናወናል፡፡

በኢትዮጵያ ያሉ ዳኞችም በዓለም አቀፍ መድረክ በሚሰናዱ ውድድሮች ላይ እንዲሳተፉ ያስችላቸዋል፡፡ በሌላ በኩል ኢትዮጵያ በስፖርት ቱሪዝም አማካይነት ከፍተኛ የውጭ ምንዛሪ እንድታገኝ የሚያስችል መሆኑም ተጠቅሷል፡፡

በዚህም መሠረት ውድድሩ ላይ የሚሳተፉ አገሮች ወደ ኢትዮጵያ ሲመጡ የአየር ትኬት፣ የሆቴል፣ እንዲሁም የተለያዩ አገልግሎቶችን በመጠቀም ከ60 እስከ 60 ሺሕ ዶላር ገቢ እንደሚያስገኝ ይገመታል፡፡

ኢትዮጵያ ባፈለው ዓመት ባስተናገደችው ዓለም አቀፍ የቴኒስ ውድድር ውጤታማ መሆን በመቻሏ፣ የዘንድሮ ዝግጅት ላይ በፋሲሊቲ፣ በአማራጭ የሜዳ ቴኒስ መጫወቻ ማግኘት መቻሉን አሮንጅ ስፖርት ሥራ አስኪያጅ አቶ ሚካኤል ለገሠ ለሪፖርተር አብራርቷል፡፡

ከዚህ ባሻገር ቱሪዝም ሚኒስቴር የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር፣ እንዲሁም ስፖንሰር አደራጊዎች ትኩረት እየሰጡ ይገኛል፡፡

ሌላው ከዓለም አቀፉ የሜዳ ቴኒስ ፌዴሬሽን ጋር ያለው ግንኙነት እየጠነከረ መምጣቱ የተገለጸ ሲሆን፣ 50 ሺሕ ዶላር የፋይናንስ ድጋፍ ለኢትዮጵያ ቴኒስ ፌዴሬሽን እንድታገኝ ዕድል እየፈጠረ ነው፡፡

ኢትዮጵያ በምሥራቅ ካሉ አገሮች ማለትም ጂቡቲ፣ ኬንያና ዑጋንዳ ያነሰ ውድድር ስታደርግ የቆየች ሲሆን፣ ባለፉት ዓመታት ዓለም አቀፍ ዝግጅቶችን ማድረጓን ተከትሎ የዓለም አቀፍ ትኩረት መሳብ ችላለች፡፡ እንደ ሚካኤል አስተያየት ኢትዮጵያ በርካታ የመጫወቻ ሜዳ ቢኖራትም ያለውን መሠረተ ልማት መጠቀም አልተቻለም፡፡

በአንፃሩ ከመከላከያ ዩኒቨርሲቲዎች፣ እንዲሁም በትምህርት ቤቶች ስፖርቱን በማስፋፋት፣ ክለቦችን በመመሥረት፣ የአገር ውስጥ ውድድሮችን የማከናወን ዕቅድ መኖሩን ያነሳል፡፡

በአንፃሩ የመጫወቻ ኳስ እንደ ቅንጦት ዕቃ ተቆጥሮ እንዲቋረጥ መደረጉና የቪዛ፣ እንዲሁም ስፖንሰርሺፕ ማጣት እንደ ችግር ይነሳል፡፡ የኢትዮጵያ ቴኒስ ፌዴሬሽን የቴኒስ ስፖርትን ለማስፋፋት ባደረገው እንቅስቃሴና የዓለም አቀፍ ውድድሮችን በማስተናገዱ ከዓለም አቀፍ ቴኒስ ፌዴሬሽን ሽልማት ተበረከተለት፡፡

በቅርቡ በ50ኛው አፍሪካ ቴኒስ ኮንፌዴሬሽን ስብሰባ በተሰናዳበት ኬንያ ሽልማት የተበረከተለት የኢትዮጵያ ቴኒስ ፌዴሬሽን፣ በአፈጻጸሙ ከምሥራቅ አፍሪካ ቀዳሚ በመሆኑ ሽልማት እንደተቸረው መገለጹ ይታወሳል፡፡

የኢትዮጵያ ቴኒስ ፌዴሬሽን እ.ኤ.አ. በ2022 እና 2023 የቴኒስ ስፖርትን በኢትዮጵያ ለማስፋፋትና ስፖርቱን ተወዳጅ ለማድረግ፣ በታዳጊ ወጣቶችና በትምህርት ቤቶች እንቅስቃሴ እንደገና እንዲጀመርና ከዋና ከተሞች በዘለለ በክልሎች እንዲስፋፋ ማድረጉ ተጠቅሷል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

[ክቡር ሚኒስትሩ ወደ መኖሪያ ቤታቸው ሲገቡ ባለቤታቸው በቴሌቪዥን የሚተላለፈውን ዜና በመደነቅ እየተመለከቱ አገኟቸው]

እንዲያው የሚደንቅ ነው እኮ። ምኑ? ዜና ተብሎ በቴሌቪዥን የሚተላለፈው ነገር ነዋ፡፡ ምኑ...

በኦሮሚያ የሚፈጸሙ ግድያዎችና የተጠያቂነት መጥፋት

የካቲት 11 ቀን 2016 ዓ.ም. ቢሾፍቱ አቅራቢያ በሚገኘው የዝቋላ...

የኢትዮጵያ መዋዕለ ንዋይ ገበያ ከሚያስፈልገው ካፒታል ውስጥ 90 በመቶውን ሰበሰበ

እስካሁን 15 ባንኮች የመዋዕለ ንዋይ ገበያው ባለድርሻ ሆነዋል የኢትዮጵያ መዋዕለ...

አዲሱ የንብ ባንክ ቦርድ የባንኩን ካፒታል በአሥር ቢሊዮን ብር ለማሳደግ ማቀዱ ተሰማ

አዲሱ የንብ ኢንተርናሽናል ባንክ የዳይሬክተሮች ቦርድ የባንኩን ካፒታል በአሥር...