Friday, March 1, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊከስድስት ሚሊዮን በላይ ኢትዮጵያውያን ሕፃናት የመቀንጨር ተጠቂ መሆናቸው በጥናት ተመላከተ

ከስድስት ሚሊዮን በላይ ኢትዮጵያውያን ሕፃናት የመቀንጨር ተጠቂ መሆናቸው በጥናት ተመላከተ

ቀን:

በኢትዮጵያ በተከሰተው ድርቅ፣ ግጭትና የዋጋ ግሽፈት ሳቢያ በተከሰተ የተመጣጣኝ የምግብ እጥረት ከስድስት ሚሊዮን በላይ ሕፃናት የመቀንጨር ተጠቂ መሆናቸውን በጥናት ተመላከተ፡፡

‹‹አምስተኛው የኢትዮጵያ ሥርዓተ ምግብ መሪዎች›› ኔትወርክ ዓርብ ኅዳር 14 ቀን 2016 ዓ.ም. ዓመታዊ ጉባዔውን ሲያደርግ፣ በጉባዔው ድርቅ፣ ግጭት፣ የዋጋ ግሽበት፣ የአንበጣ መንጋ፣ ጎርፍና የመሳሰሉት ሰው ሠራሽና ተፈጥሯዊ አደጋዎች የሥርዓተ ምግብ ዕቅዶችን ለማሳካት ፈተና ሆነዋል ተብሏል፡፡

እ.ኤ.አ. በ2020 የተሠራ ጥናትን ዋቢ በማድረግ ንግግር ያደረጉት የኢትዮጵያ ሥርዓተ ምግብ ከፍተኛ የፕሮግራም ሥራ አስኪያጅና የሰቆጣ ቃል ኪዳን ፌዴራል ማስፈጻሚያ ክፍል ሲሳይ ሲናሞ (ዶ/ር) ናቸው፡፡

- Advertisement -

Video from Enat Bank Youtube Channel.

ላለፉት 20 ዓመታት በተከናወኑ ሥራዎች የምግብና የሥርዓተ ምግብ የመሻሻል ሁኔታዎች ቢያሳዩም፣ በአሁኑ ወቅት ከስድስት ሚሊዮን በላይ ሕፃናት የመቀንጨር ችግር ያጋጠማቸው መሆኑን፣ አንድ ሚሊዮን ያህል ሕፃናት ደግሞ በአጣዳፊ የሥርዓተ ምግብ ችግር ውስጥ ሆነው የሕክምና ድጋፍ እየተደረገላቸው እንደሚገኙ ሲሳይ (ዶ/ር) አስረድተዋል፡፡

በአሁኑ ወቅት የምግብ ሥርዓቱ ያለበት ሁኔታ እጅግ አሳሳቢ እንደሆነ የተናገሩት (ዶ/ር) ሲሳይ፣ ለማሻሻል ብዙ ሥራዎችን ማከናወን ያስፈልጋል ብለዋል፡፡ በአገር ደረጃ የምግብና የሥርዓተ ምግብ ፖሊሲ መዘጋጀቱን ገልጸው፣ ‹‹ፖሊሲውን ተግባራዊ ለማድረግ በምግብና በሥርዓተ ምግብ ስትራቴጂ፣ እንዲሁም በሰቆጣ ቃል ኪዳን ትግበራ እየተደረገ ቢሆንም ለተግባራዊነቱ በርካታ ተግዳሮቶች እየገጠሙት ነው፤›› ብለዋል፡፡

በተለይ ደግሞ ከአየር ንብረት ለውጥ ጋር ተያይዞ እየተከሰተ ያለው ድርቅ፣ ሥርዓተ ምግባቸው ተስተካክሎ የነበሩ አካባቢዎች እንደገና ለከፋ ችግር እያጋለጣቸው መሆኑን አብራርተዋል፡፡

በዓለም አቀፍና በአገር አቀፍ ደረጃ እየገጠመ ያለው የምግብ ዋጋ ንረት፣  በተለያዩ አካባቢዎች ያሉ ግጭቶችና ባለፉት ዓመታት የነበሩ ጦርነቶች፣ መንግሥት አስቀምጧቸው የነበሩ የምግብና ሥርዓተ ምግብ ዕቅዶች እንዳይሳኩ አድርገዋል ሲሉ አክለዋል፡፡

‹‹አሁንም ለምግብና ለሥርዓተ ምግብ የሚመደበው ገንዘብ በመንግሥትም ሆነ በለጋሽ ድርጅቶች የመቀነስ ሁኔታ እያሳየ ነው፤›› ያሉት ሲሳይ (ዶ/ር)፣ ለምግብና ለሥርዓተ ምግብ ከሚያስፈልገው ሀብት እስከ 50 በመቶ የሚሆን ክፍተት አለ ብለዋል፡፡

እ.ኤ.አ. በ2022 የተረጂዎች ሀብት መጠን ፍላጎት በአገር ደረጃ እ.ኤ.አ. በ2023 ለተረጂዎች ያስፈልጋል ተብሎ ከተጠየቀው ሀብት 30 በመቶ ገደማ የሚሆነው ብቻ መገኘቱን የገለጹት ሲሳይ (ዶ/ር)፣ ይህ የሚያመለክተው ብዙ ተረጂዎች ሲኖሩ የተገኘው ሀብት ግን በጣም ጥቂት መሆኑን ነው ብለዋል፡፡ እንዲህ ከሆነ ደግሞ የሚደረገው የምግብ ድጋፍ የቅድሚያ ቅድሚያ ተብለው በጣም ለባሰባቸው አካባቢዎች የማድረስ ሥራ እየተሠራ ነው፤›› ሲሉ አስረድተዋል፡፡

በኢትዮጵያ ያለው ምግብና ሥርዓተ ምግብ በተለያዩ ምክንያቶች ሥጋት ውስጥ መግባቱን የገለጹት ደግሞ በኢትዮጵያ የተቋሙ ዋና ዳይሬክተር ናሙኮሎ ኮቪክ ናቸው፡፡ ናሙኮሎ ባቀረቡት ጥናታዊ ጽሑፍ በአማራና በትግራይ ክልሎች ከአምስት ሚሊዮን በላይ ሰዎች የተመጣጠነ የምግብ እጥረት እንደገጠማቸው፣ 2.1 ሚሊዮን ያህሉ ደግም በግጭት ምክንያት በደረሰባቸው ጉዳት ከቀዬአቸው ተፈናቅለዋል ብለዋል፡፡

በአፋር፣ በአማራ፣ በኦሮሚያ፣ በትግራይ፣ በሶማሌ ክልሎች፣ እንዲሁም በድሬዳዋ የተከሰተው ድርቅ ወደ ሁለት ሚሊዮን የሚጠጉ ሰዎችን ለመመገብ የሚችል ሰብል ማሳጣቱን ገልጸዋል፡፡

በቅርብ ሳምንታት ደግሞ ከአንድ ሺሕ በላይ የሚሆኑ ሰዎች በጎርፍ ምክንያት መፈናቀላቸውን ተወካይዋ አብራርተዋል፡፡

ለችግሩ መስፋፋትና ዘላቂ መፍትሔን ለማምጣት ተግዳሮች ናቸው ተብለው በጥናቱ ከቀረቡ ምክንያቶች መካከል የመንግሥት የገንዘብ ድጋፍ ውስንነት፣ ሰላምና መረጋጋት አለመኖር፣ በግጭት ሳቢያ ከቀዬአቸው ለሚፈናቀሉ ሰዎች በቂ የሆነ መጠለያ ማጣት የምግብ ሥርዓቱን የሚያፋልሱ የሚሉት ይገኙበታል፡፡

በአጠቃይ በኢትዮጵያ ያለውን ሥርዓተ ምግብ ለማስተካከል አራት ቢሊዮን ዶላር የገንዘብ ድጋፍ ቢያስፈልግም፣ ባለው የሀብት ውስንነት ምክንያት እ.ኤ.አ. በ2023 የተገኘው 1.2 ቢሊዮን ዶላር ወይም 30 በመቶ የሚሆነው ብቻ እንደሆነ በቀረበው ጥናት ላይ ተገልጿል፡፡  

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

[ክቡር ሚኒስትሩ ወደ መኖሪያ ቤታቸው ሲገቡ ባለቤታቸው በቴሌቪዥን የሚተላለፈውን ዜና በመደነቅ እየተመለከቱ አገኟቸው]

እንዲያው የሚደንቅ ነው እኮ። ምኑ? ዜና ተብሎ በቴሌቪዥን የሚተላለፈው ነገር ነዋ፡፡ ምኑ...

በኦሮሚያ የሚፈጸሙ ግድያዎችና የተጠያቂነት መጥፋት

የካቲት 11 ቀን 2016 ዓ.ም. ቢሾፍቱ አቅራቢያ በሚገኘው የዝቋላ...

የኢትዮጵያ መዋዕለ ንዋይ ገበያ ከሚያስፈልገው ካፒታል ውስጥ 90 በመቶውን ሰበሰበ

እስካሁን 15 ባንኮች የመዋዕለ ንዋይ ገበያው ባለድርሻ ሆነዋል የኢትዮጵያ መዋዕለ...

አዲሱ የንብ ባንክ ቦርድ የባንኩን ካፒታል በአሥር ቢሊዮን ብር ለማሳደግ ማቀዱ ተሰማ

አዲሱ የንብ ኢንተርናሽናል ባንክ የዳይሬክተሮች ቦርድ የባንኩን ካፒታል በአሥር...