Friday, March 1, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊለጨቅላ ሕፃናት ሕክምና ማዕከላት ከ24 ሚሊዮን ዶላር በላይ የሚያወጡ መሣሪያዎች መሟላታቸው ተገለጸ

ለጨቅላ ሕፃናት ሕክምና ማዕከላት ከ24 ሚሊዮን ዶላር በላይ የሚያወጡ መሣሪያዎች መሟላታቸው ተገለጸ

ቀን:

በተለያዩ አካባቢዎች በሚገኙና በተመረጡ 80 የመንግሥት ሆስፒታሎች ውስጥ በቅርቡ ለተቋቋሙ የሦስተኛ ደረጃ የጽኑ ጨቅላ ሕፃናት ሕክምና ማዕከላት፣ 24.2 ሚሊዮን ዶላር የሚያወጡ ዘመናዊ የሕክምና መገልገያ መሣሪያዎች እንደተሟላላቸው ጤና ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

በዓለም ከመወለጃ ቀናቸው በፊት ወይም በሕክምና አቆጣጠር ከ37ኛው የእርግዝና ሳምንት በፊት የሚወለዱ ጨቅላ ሕፃናት ቀን ታስቦ በዋለበት ሥነ ሥርዓት ላይ የሚኒስቴሩ የእናቶችና ሕፃናት፣ ወጣቶችና አፍላ ወጣቶች ጤና መሪ ሥራ አስፈጻሚ መሠረት ዘለዓለም (ዶ/ር) እንደገለጹት፣ አብዛኞቹ ማዕከላት የቀረቡላቸውን የሕክምና መገልገያ መሣሪያዎች ተክለውና ገጣጥመው ለአገልግሎት ዝግጁ አድርገዋል፡፡

መንግሥት በውድ ዋጋ መሣሪያዎችን ገዝቶ ለየማዕከላቱ ሊያቀርብ የቻለው ከመውለጃ ቀናቸው ቀድመውና ዝቅተኛ ክብደት ኖሯቸው የሚወለዱ ጨቅላ ሕፃናት ጥራት ያለውና ፍትሐዊ እንክብካቤ እንዲያገኙ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

- Advertisement -

Video from Enat Bank Youtube Channel.

ከመወለጃ ቀናቸው ቀድመው የሚወለዱ ጨቅላ ሕፃናትን በትንሽ ወጪ መታደግ የሚያስችለውን ‹‹የካንጋሮ ማዘር ኬር›› ወይም የገላ ለገላ ክብካቤን ማሳደግ ላይ ትኩረት ተሰጥቶ ሊሠራበት እንደሚገባም ጠቁመዋል፡፡

መረጃዎች እንደሚጠቁሙት፣ በየዓመቱ በዓለም ከ15 ሚሊዮን በላይ፣ በኢትዮጵያ ደግሞ 376,700 ጨቅላ ሕፃናት ከመወለጃ ቀናቸው አስቀድመው እንደሚወለዱ መሪ ሥራ አስፈጻሚዋ ገልጸዋል፡፡

በዓለም ደረጃ እ.ኤ.አ. በ2020 ወደ አንድ ሚሊዮን የሚጠጉ፣ በኢትዮጵያ ደግሞ እ.ኤ.አ. በ2016 ወደ 27,600 ከመወለጃ ቀናቸው አስቀድመው የተለዱ ጨቅላ ሕፃናት በተለያዩ የጤና እክሎች ሳቢያ ለሕልፈተ ሕይወት ተዳርግዋል፡፡

እንደ መሪ ሥራ አስፈጻሚዋ፣ የአምስት ዓመት የልደት በዓላቸውን ሳያከብሩ ከሚሞቱት ሕፃናት መካከል ብዙውን ቁጥር የያዙት ጨቅላ ሕፃናት ናቸው፡፡ ከእነዚህም ውስጥ ደግሞ የአንበሳውን ድርሻ የያዙት ከመወለጃ ቀናቸው አስቀድመው የተወለዱ ጨቅላ ሕፃናት ናቸው፡፡

ባለፈው ሳምንት ማብቂያ በፍሬንድሺፕ ኢንተርናሽናል ሆቴል ታስቦ በዋለው የጨቅላ ሕፃናት ቀን፣ አርቲስት መቅደስ ፀጋዬ አዲስ የተወለዱ ጨቅላ ሕፃናትና የሕፃናት ጤና የበጎ ፈቃድ አምባሳደር ተደርጋ መመረጧ ይፋ ሆኗል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

[ክቡር ሚኒስትሩ ወደ መኖሪያ ቤታቸው ሲገቡ ባለቤታቸው በቴሌቪዥን የሚተላለፈውን ዜና በመደነቅ እየተመለከቱ አገኟቸው]

እንዲያው የሚደንቅ ነው እኮ። ምኑ? ዜና ተብሎ በቴሌቪዥን የሚተላለፈው ነገር ነዋ፡፡ ምኑ...

በኦሮሚያ የሚፈጸሙ ግድያዎችና የተጠያቂነት መጥፋት

የካቲት 11 ቀን 2016 ዓ.ም. ቢሾፍቱ አቅራቢያ በሚገኘው የዝቋላ...

የኢትዮጵያ መዋዕለ ንዋይ ገበያ ከሚያስፈልገው ካፒታል ውስጥ 90 በመቶውን ሰበሰበ

እስካሁን 15 ባንኮች የመዋዕለ ንዋይ ገበያው ባለድርሻ ሆነዋል የኢትዮጵያ መዋዕለ...

አዲሱ የንብ ባንክ ቦርድ የባንኩን ካፒታል በአሥር ቢሊዮን ብር ለማሳደግ ማቀዱ ተሰማ

አዲሱ የንብ ኢንተርናሽናል ባንክ የዳይሬክተሮች ቦርድ የባንኩን ካፒታል በአሥር...