Monday, February 26, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ዓለምሕዝባቸውን ከቀውስ የታደጉት የላይቤሪያው ፕሬዚዳንት ጆርጅ ዊሃ

ሕዝባቸውን ከቀውስ የታደጉት የላይቤሪያው ፕሬዚዳንት ጆርጅ ዊሃ

ቀን:

የምዕራብ አፍሪካ አገሮች በወታደራዊ መፈንቅለ መንግሥት በወደቁበት ወቅት የፕሬዚዳንት ምርጫ ያደረገችው የቀጣናው አገር ላይቤሪያ ፕሬዚዳንት ጆርጅ ዊሃ፣ ሰላማዊ የሥልጣን ሽግግር በማድረግ ለቀጣናው ተጨማሪ ሥጋት ከመሆን ሕዝባቸውን ታድገዋል፡፡

እ.ኤ.አ. ከ2018 ጀምሮ የፕሬዚዳንትነቱን መንበር የተቆናጠጡት የቀድሞ የእግር ኳስ ኮከብ ጆርጅ ዊሃ፣ በምርጫው በተፎካካሪያቸው ጆሴፍ ቦአካይ መሸነፋቸውን ተከትሎ ባደረጉት ንግግር፣ ‹‹የላይቤሪያ ሕዝብ ተናግሯል፣ እኛም ድምጹን ሰምተናል›› ብለዋል፡፡

እ.ኤ.አ. በ2024 መጀመርያ ሥልጣናቸውን የሚያስረክቡት ፕሬዚዳንት ዊሃ፣ በ2018 ወደ ሥልጣን ሲመጡ፣ በተለይ ከወጣቱ ከፍተኛ ድጋፍ ነበራቸው፡፡ በወቅቱም ተፎካካሪያቸው የነበሩትንና የአሁኑ ተመራጭ ፕሬዚዳንት ቦአካይን በሰፊ ልዩነት ነበር ያሸነፉት፡፡

- Advertisement -

Video from Enat Bank Youtube Channel.

ሕዝባቸውን ከቀውስ የታደጉት የላይቤሪያው ፕሬዚዳንት ጆርጅ ዊሃ | Ethiopian Reporter | ሪፖርተር
የላይቤሪያ ተመራጭ ፕሬዚዳንት ጆሴፍ ቦአካይ ደጋፊዎች በሞኖሮቪያ ጎዳናዎች (ቢቢሲ)

ሆኖም በወቅቱ አገሪቱ ገብታበት ከነበረው ሙስና፣ የኑሮ ውድነት እንዲሁም የኢኮኖሚው አለመረጋጋት ይቀርፋል የሚል ሐሳብ የነበራቸው ላይቤሪያውያን ይህ አለመሳካቱ በዊሃ ላይ የነበራቸው እምነት እንዲሸረሽር አድርጓል፡፡

የነበራቸውን ተቀባይነት እያጡ የመጡት ዊሃ፣ ባለፈው ሳምንት ማብቂያ በተከናወነው የፕሬዚዳንት ምርጫ የተሸነፉት በጠባብ ልዩነት እንደሆነ ቢቢሲ አስፍሯል፡፡

የ78 ዓመቱ ቦአካይ 50.89 በመቶ፣ ጆርጅ ዊሃ ደግሞ 49.11 በመቶ ድምጽ በማምጣት በጠባብ ልዩነት መሸነፋቸው ሕዝቡ እኩል በሚባል ደረጃ ለሁለት መከፈሉን ያሳያል፡፡

ዊሃ ይህንን አስመልክተው እንዳሉትም፣ አገራቸው ሁለት ፍላጎት በሚያንፀባርቁ ሕዝቦች ተከፍላለች፡፡ በመሆኑም ተከታዩ ፕሬዚዳንት ቦአካይ፣ ይህንን ልዩነት በጥንቃቄ አስተናግደው አገሪቷን መምራት ይጠበቅባቸዋል፡፡

‹‹ወቅቱ ሽንፈታችንን በግርማ ሞገስ የምንቀበልበት ነው፣ ጊዜው አገራችንን ከፓርቲያችን በላይ የምናስቀምጥበት ነው፣ ከግል ፍላጎት የአገር ፍቅር የሚበልጥበት ነው፤›› ሲሉም ተናግረዋል፡፡

በሁለት የእርስ በርስ ግጭት 250 ሺሕ ዜጎቿን ያጣችው ላይቤሪያ ዳግም ወደዚህ መግባት የለባትም የሚሉት የላይቤሪያ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ሃሳን ቢሊቲ፣ የ57 ዓመቱ ዊሃ ለአሸናፊው ቦአካይ የእንኳን ደስ አለህ የስልክ ጥሪ ማድረጋቸው፣ ለላይቤሪያም ሆነ ለአፍሪካ ትልቅ ትምህርት ነው ብለዋል፡፡

የሰብዓዊ መብት ተሟጋቹ ለቢቢሲ እንዳሉት፣ የፕሬዚዳንት ዊሃ ድርጊት ከትልቅ የስፖርት ሰው የሚጠበቅ፣ እንደ አገር መሪና እንደ ሰላም ወዳድም የከፍተኛ ደረጃ መገለጫ ነው፡፡

የጆርጅ ዊሃ ልዩ አማካሪ ሴኩ ካላስኮ በበኩላቸው፣ ‹‹ዊሃ የሰላም ሰው ነው፡፡ የሕዝቡ ፍላጎት መከበር አለበት የሚልና ይህንንም ሁሌ አስጠብቆ የሚኖር ነው፤›› ሲሉ ፕሬዚዳንት ዊሃን ገልጸዋቸዋል፡፡

በወታደራዊ መፈንቅለ መንግሥት ምክንያት እየተፍረከረከ የሚገኘው የምዕራብ አፍሪካ የኢኮኖሚ ማኅበረሰብ፣ ለተሰናባቹ ዊሃ የመምራት አቅማቸውንና ያላቸውን ቆራጥ አቋም አድንቆ የምሥጋና መግለጫውን አውጥቷል፡፡

ተመራጩ ፕሬዚዳንት ጆሴፍ ቦአካይ ማን ናቸው?

የ78 ዓመቱ የላይቦሪያ ተመራጭ ፕሬዚዳንት ጆሴፍ ቦአካይ፣ ‹‹ዕድሜ ፀጋ ነው›› በሚለው ንግግራቸው ይታወቃሉ፡፡ በአፍሪካና በላይቤሪያ የመጀመርያ ሴት ፕሬዚዳንት ሆነው በተመረጡት ኤለን ጆንሰን የሥልጣን ዘመን ለ12 ዓመታት ምክትል ፕሬዚዳንት ሆነው አገልግለዋል፡፡

እ.ኤ.አ. በ2024 መጀመርያ ላይ የፕሬዚዳንትነት ሥልጣኑን የሚረከቡት ቦአካይ፣ እ.ኤ.አ. ከ1980 እስከ 1990 ድረስ የላይቤሪያ ግብርና ሚኒስትር ሆነው አገልግለዋል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የመጣንበትና አብረን የምንዘልቅበት የጋራ እሴታችን ለመሆኑ ነጋሪ ያስፈልጋል ወይ?

በኑረዲን አብራር በአገራችን ለለውጥ የተደረጉ ትግሎች ከመብዛታቸው የተነሳ ሰላም የነበረበት...

አልባሌ ልሂቃንና ፖለቲከኞች

በበቀለ ሹሜ በ2016 ዓ.ም. ኅዳር ማክተሚያ ላይ ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ...

አሜሪካ የኢትዮጵያ የባህር በር ጥያቄ ተገቢነት ቢኖረውም ከጎረቤት አገሮች ጋር በሚደረግ ንግግር መሆን አለበት አለች

መንግሥትን ከፋኖና ከኦነግ ሸኔ ጋር ለማነጋገር ፍላጎቷን ገልጻለች የኢትዮጵያ የባህር...