Monday, February 26, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊበኢትዮጵያ በሚጥል በሽታ የሚሰቃዩ ሕሙማን ትኩረት እየተሰጣቸው አይደለም ተባለ

በኢትዮጵያ በሚጥል በሽታ የሚሰቃዩ ሕሙማን ትኩረት እየተሰጣቸው አይደለም ተባለ

ቀን:

በኢትዮጵያ በሚጥል በሽታ የሚሰቃዩ ሕሙማን አስፈላጊውን የሕክምና አገልግሎት እያገኙ እንዳልሆነና ችግሩም በተለያዩ የሕክምና ተቋማት ውስጥ እንዲታይ፣ የተሻለ ሕይወት በሚጥል በሽታ ለሚሰቃዩ ሰዎች በኢትዮጵያ የበጎ አድራጎት ግብረ ሰናይ ድርጅት አስታወቀ፡፡

ድርጅቱ ቅዳሜ ኅዳር 8 ቀን 2016 ዓ.ም. በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ፣ በኢትዮጵያ ውስጥ በሚጥል በሽታ የሚሰቃዩ ሕሙማን የሕክምና አገልግሎት ለማግኘት ወደ ሕክምና ተቋማት ሲሄዱ ተገቢው እንክብካቤ እየተደረገላቸው አይደለም ብሏል፡፡

የተሻለ ሕይወት በሚጥል በሽታ ለሚሰቃዩ ሰዎች የተሰኘው ግብረ ሰናይ ድርጅት መሥራችና የማኅበሩ ፕሬዚዳንት ወ/ሮ አርሴማ በቀለ እንደገለጹት፣ በሚጥል በሽታ የሚስቃዩ ሕሙማን ተገቢውን ድጋፍ እንዲያገኙ ተቋሙ ሦስት ፕሮጀክቶችን ቀርፆ እየሠራ ነው፡፡

- Advertisement -

Video from Enat Bank Youtube Channel.

በኢትዮጵያ ውስጥ በሚጥል በሽታ እየተሰቃዩ ያሉ ሕሙማን ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ተፅዕኖ እየደረሰባቸው መሆኑን ገልጸው፣ እነዚህንም ችግሮች ለመፍታትና ለሕሙማኑ አስፈላጊውን ድጋፍ ለማድረግ ከሥልጠና ጀምሮ የተለያዩ አገልግሎቶችን ማኅበሩ እየሰጠ መሆኑን አብራርተዋል፡፡

በችግሩ ውስጥ ለሚገኙ ሰዎች በፈትልና የንብ ቀፎ በመግዛት ወደ ሥራ እንዲሠማሩ ማድረጉን ያስታውሱት መሥራቿ፣ በአብዛኛው የሕክምና ተቋማት ውስጥ የሚደርስባቸውን እንግልት ለማስቀረት የሥነ ልቦናና የማማከር ሥራ እየሠሩ እንደሆነ አክለዋል፡፡

በሌላ በኩል በሚጥል በሽታ የሚሰቃዩ ሕሙማን ከመንግሥት በኩል የሚደረግላቸው የጤና መድን ድጋፍ ዝቅተኛ ስለሆነ፣ ማኅበሩ የገንዘብ ድጋፍ በማድረግ በዚህ ችግር ውስጥ የሚገኙ ሰዎችን እየታደገ መሆኑን አስረድተዋል፡፡

በተመሳሳይ በዚህ ሥራ ከተሠማሩ ድርጅቶች መካከል ‹‹ኬርኤፕሊፕሲ›› ኢትዮጵያ በሚጥል ሕመም ላይ የሚሠራ የበጎ አድራጎት ድርጅት አይገኝበታል፡፡

ድርጅቱ ከ1,500 በላይ የሚጥል ሕመም ያለባቸው ታማሚዎችን በማቀፍ የጤናቸው ሁኔታ እንዲሻሻል ነፃ የሕክምና፣ የምርመራ፣ የመድኃኒትና የመረጃ አገልግሎት እየሰጠ መሆኑን አስታውቋል፡፡

በበርካታ የጤና ተቋማት ትምህርት ቤቶች፣ ዩኒቪርሲቲዎች፣ ማረሚያ ቤቶች እንዲሁም በተለያዩ ድርጅቶች በሚጥል ሕመም ዙሪያ ለባለሙያዎች ሥልጠናዎችና የግንዛቤ ማስጨበጫ ትምህርቶችን መስጠቱንም ተቋሙ ማክሰኞ ኅዳር 11 ቀን 2016 ዓ.ም. ጉዳዩን አስመልክቶ በነበረው መድረክ አመልክቷል፡፡

የኬርኢፕሊፕሲ መረጃ እንደሚያሳየው፣ በኢትዮጵያ የሚጥል በሽታ ከተዘነጉ በሽታዎች የሚመደብ ነው፡፡ ለአካል ጉዳተኝነት ከሚዳርጉ ዋና ዋና ምክንያቶች አንዱ ቢሆንም፣ በኢትዮጵያ ለሕመሙ ሕክምና የሚሰጡ ተቋማት አነስተኛ ናቸው፡፡

በኢትዮጵያ ከአንድ ሚሊዮን ሰዎች በላይ ከሕመሙ ጋር እንደሚኖሩ፣ በርካታ ሕፃናት ሕሙማን በሕመማቸው ምክንያት በዝቅተኛ የትምህርት ደረጃ እንደሚወሰኑ፣ ይህም ሥራ እንዳያገኙ ወይም የመቀጠር ዕድላቸው ዝቅተኛ እንዲሆንና ለድህነት እንዲጋለጡ ማድረጉን ተቋሙ ገልጿል፡፡

ሕመሙን በተመለከተ ያለው ግንዛቤ አነስተኛ መሆን፣ ሕመሙን ከእምነት፣ ከአሉታዊ ነገሮች ጋር ማያያዝ፣ በማኅበረሰብ፣ በሥራ ቦታና በትምህርት ቤት መገለል እያስከተለ መሆኑንም አክሏል፡፡   

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የመጣንበትና አብረን የምንዘልቅበት የጋራ እሴታችን ለመሆኑ ነጋሪ ያስፈልጋል ወይ?

በኑረዲን አብራር በአገራችን ለለውጥ የተደረጉ ትግሎች ከመብዛታቸው የተነሳ ሰላም የነበረበት...

አልባሌ ልሂቃንና ፖለቲከኞች

በበቀለ ሹሜ በ2016 ዓ.ም. ኅዳር ማክተሚያ ላይ ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ...

አሜሪካ የኢትዮጵያ የባህር በር ጥያቄ ተገቢነት ቢኖረውም ከጎረቤት አገሮች ጋር በሚደረግ ንግግር መሆን አለበት አለች

መንግሥትን ከፋኖና ከኦነግ ሸኔ ጋር ለማነጋገር ፍላጎቷን ገልጻለች የኢትዮጵያ የባህር...