Monday, February 26, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ስፖርትወደ ዓለም ዋንጫ ለመግባት 90 ደቂቃ የቀራቸው ሉሲዎቹ

ወደ ዓለም ዋንጫ ለመግባት 90 ደቂቃ የቀራቸው ሉሲዎቹ

ቀን:

የኢትዮጵያ የእግር ኳስ ታሪክ ሲነሳ እ.ኤ.አ. 2001 በአርጀንቲና የተሰናዳው ከ20 ዓመት በታች ዓለም ዋንጫ ይታወሳል፡፡ የኢትዮጵያ ከ20 ዓመት በታች ወንዶች ብሔራዊ ቡድን በጣሊያናዊው አሠልጣኝ ዲያጎ ጋርዚያቶ እየተመራ በዓለም ዋንጫ ያደረገው ተሳትፎ ምንጊዜም ይታወሳል፡፡

እ.ኤ.አ. 2001 ኢትዮጵያ ባሰናዳቸው የአፍሪካ ወጣቶች ሻምፒዮና ስምንት አገሮች ወደ ዓለም ዋንጫው ለመሻገር ተሳትፈዋል፡፡ የኢትዮጵያ ከ20 ዓመት በታች ወንዶች ብሔራዊ ቡድን በምድብ አንድ ከግብፅ፣ ካሜሮንና ደቡብ አፍሪካ የተደለደሉ ሲሆን፣ በምድብ ሁለት ጋና፣ አንጎላ፣ ማሊና ናይጄሪያ ተደልድለዋል፡፡

አራት ብሔራዊ ቡድን ብቻ ወደ ዓለም ዋንጫ ማለፍ የሚቻል ሲሆን፣ በኢትዮጵያ ምድብ የሚገኙትን የግብፅና የካሜሮን ተያይዘው ለማለፍ ሲያደርጉት የነበረው ጥረት በሁሉም ዘንድ ይታወሳል፡፡ በአዲስ አበባና በአበበ ቢቂላ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ፣ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ደቡብ አፍሪካን 4 ለ1 በመርታት ወደ አርጀንቲናው ዓለም ዋንጫ መሻገር የቻለበት ክስተት በሁሉም የእግር ኳስ አፍቃሪ ዘንድ የሚረሳ አይደለም፡፡

- Advertisement -

Video from Enat Bank Youtube Channel.

የኢትዮጵያ ወንዶች ከ20 ዓመት ብሔራዊ ቡድን በታሪኩ ለመጀመርያ ጊዜ በዓለም ዋንጫ ከተሳተፈ 22 ዓመት ሞልቶታል፡፡ ኢትዮጵያ በሁሉም ብሔራዊ ቡድኖች በአኅጉር አቀፍ፣ እንዲሁም በዓለም አቀፍ በሚያደርጓቸው የማጣሪያ ውድድሮች ከምድባቸው መሻገር ተስኗቸው ዘመናት ተቆጥረዋል፡፡

በአንፃሩ ኢትዮጵያ ከወንዶች ብሔራዊ ቡድን ተሳትፎ ይልቅ በሴቶቹ ያላት ተሳትፎ የተስፋ ጭላንጭል እየታየበት ነው፡፡ የኢትዮጵያ የሴቶች ብሔራዊ ቡድን በአኅጉር አቀፍ ደረጃ የሚያደርገው ተሳትፎ ከዓመት ዓመት እየተሻሻለ መጥቷል፡፡

የኢትዮጵያ ከ20 ዓመት በታች ሴቶች ብሔራዊ ቡድን እ.ኤ.አ. በ2024 በኮሎምቢያ በሚሰናደው የዓለም ዋንጫ ጨዋታ ለመካፈል የ90 ደቂቃ ዕድሜ ብቻ ቀርቶታል፡፡ 35 የአፍሪካ ብሔራዊ ቡድኖች በተደለደሉበት ማጣሪያ፣ ኢትዮጵያ በሁለተኛው የምድብ ጨዋታዋ ኢኳቶሪያል ጊኒን በደርሶ መልስ 5 ለ2 መርታት ችላለች፡፡

በሦስተኛ የምድብ ጨዋታ የማሊ አቻቸውን የገጠሙት የኢትዮጵያ ከ20 ዓመት በታች ሴቶች ብሔራዊ ቡድን በደርሶ መልስ ውጤት የማሊ ብሔራዊ ቡድንን 6 ለ0 በማሸነፍ የመጨረሻ ምዕራፍ ላይ ይገኛሉ፡፡

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ወደ ኮሎምቢያ ዓለም ዋንጫ ለማለፍ አራተኛ የማጣሪያ ጨዋታውን ከሞሮኮ ብሔራዊ ቡድን ጋር ያደርጋል፡፡

የመጨረሻ የማጣሪያ ጨዋታቸውንም ከጥር 12 እስከ የካቲት 13 ቀን 2016 ዓ.ም. ባለው ጊዜ ውስጥ በደርሶ መልስ የሚያከናውኑ ይሆናል፡፡ ሉሲዎቹ በደርሶ መልስ ጨዋታ የሞሮኮ አቻቸውን መርታት ከቻሉ ከ22 ዓመት በፊት ወደ አርጀንቲናው የዓለም ዋንጫ መሳተፍ ከቻለው የኢትዮጵያ ከ20 በታች ወንዶች ብሔራዊ ቡድን ጋር ታሪክ ይጋራሉ፡፡

በአሠልጣኝ ፍሬው ኃይለ ገብርኤል የሚመራው የሉሱዎቹ ስብስብ ለመጨረሻ የማጣሪያ ጨዋታ በቂ ዝግጅት ማድረግ እንደሚጠበቅበት ይታመናል፡፡

ከማሊ ጨዋታ በኋላ አስተያየቱን ለሪፖርተር የሰጠው አሠልጣኝ ፍሬው፣ ተጫዋቾቹ ጥሩ ብቃት ላይ እንደሚያገኙ ገልጾ፣ ለቀሪው ጨዋታ አስፈላጊውን ዝግጅት ለማድረግ ትኩረት ማድረግ ይገባል ብሏል፡፡

አሠልጣኙ ሞሮኮ ጠንካራ ቡድን መሆናቸውን ያነሳ ሲሆን፣ ጠንካራ ዝግጅት እንደሚያስፈልግ፣ ለዚህም ብሔራዊ ቡድን የወዳጅነት ጨዋታ እንዲያደርግ ፌዴሬሽኑ ቢያመቻች የሚል አስተያየት ሰጥቷል፡፡

‹‹ኢትዮጵያ ትልቅ ታሪክ እንድትጽፍ ምኞቴ ነው፡፡ ተጫዋቾቹም ጥሩ መነቃቃት ላይ ናቸው፤›› በማለት አሠልጣኝ ፍሬው አስተያየቱን ሰጥቷል፡፡

ከ20 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድኑን የተዋቀረውም ከዓምናው ከ20 ዓመት በታች ቡድን አምስት ተጫዋች፣ ከ17 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን ደግሞ 13 ተጨዋቾችን በማካተት ጠንካራ ቡድን መገንባት እንዳስቻለው አሠልጣኝ ፍሬው አብራርቷል፡፡

በአኅጉር አቀፍ መድረኮች ንቁ ተሳትፎ በማድረግ ውጤታማ ጊዜ እያሳለፉ የሚገኙት ሊሲዎቹ፣ አስፈላጊውን ትኩረት አለማግኘታቸው ይነገራል፡፡ ዋናው የሴቶች ብሔራዊ ቡድንን ጨምሮ በሁሉም የዕድሜ ዕርከን ውስጥ የሚገኙ ቡድኖች ውጤታማ ጊዜ እያሳለፉ ቢሆንም ከወንዶቹ አንፃር ትኩረት እንዳልተሰጣቸው ይነሳል፡፡

የኢትዮጵያ ወንዶች ብሔራዊ ቡድኖች ድል ሲያድርጉ የሚሰጣቸው የሽልማት መጠንና በአንፃሩ ለሴቶቹ የሚሰጠው የማበረታቻ ሽልማት ተመጣጣኝ እንዳልሆነ በተደጋጋሚ ይተቻል፡፡

ሆኖም የእንስቶቹ የአኅጉር አቀፍ ተሳትፎ ከአፍሪካ መድረክ አልፎ በዓለም ዋንጫው ለመካፈል ከመጨረሻ ምዕራፍ ደርሷል፡፡ ይህም ከ22 ዓመት በፊት ‹‹በጋሬዜቶ ዘመን የተሳካው ድል በአሠልጣኝ ፍሬው ይደገማ፤›› የሚለው 90 ደቂቃ ዕድሜ ብቻ ይቀረዋል፡፡

የሴቶች ከ20 ዓመት በታች የፊፋ ዓለም ዋንጫ ጨዋታ ከነሐሴ 25 ቀን 2016 ዓ.ም እስከ መስከረም 12 ቀን 2017 ዓ.ም በኮሎምብያ አስተናጋጅነት ይካሄዳል፡፡ አዘጋጅ አገርን ጨምሮ የ24 አገሮች ብሔራዊ ቡድኖች ይሳተፋሉ፡፡ እ.ኤ.አ በ2002 የጀመረው ዓለም ዋንጫ ዕድሜያቸው ከ19 ዓመት በታች የሆኑ ተጫዋቾች ብቻ ይሳተፉ ነበር፡፡ በአንፃሩ  ከ2006 ዓ.ም. በኋላ ዕድሜያቸው ከ20 ዓመት በታች የሆኑ ተጫዋቾች እንዲሳተፉ ተደርገዋል፡፡  

ናይጀሬያና ዲሞክራቲክ ኮንጎ ከአፍሪካ የነቃ ተሳትፎ ያላቸው ቡድኖች ናቸው፡፡ የናይጄሪያ ብሔራዊ ቡድን በ2004 ዓ.ም. እና 2006 ዓ.ም. አራተኛ ደረጃን ይዞ ማጠናቀቅ ችሏል፡፡ በዓለም ዋንጫው የጀመርመንና የአሜሪካ ብሔራዊ ቡድኖች ሦስት፣ ሦስት ጊዜ ዋንጫ በማንሳት ቀዳሚ አገሮች ናቸው፡፡  

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የመጣንበትና አብረን የምንዘልቅበት የጋራ እሴታችን ለመሆኑ ነጋሪ ያስፈልጋል ወይ?

በኑረዲን አብራር በአገራችን ለለውጥ የተደረጉ ትግሎች ከመብዛታቸው የተነሳ ሰላም የነበረበት...

አልባሌ ልሂቃንና ፖለቲከኞች

በበቀለ ሹሜ በ2016 ዓ.ም. ኅዳር ማክተሚያ ላይ ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ...

አሜሪካ የኢትዮጵያ የባህር በር ጥያቄ ተገቢነት ቢኖረውም ከጎረቤት አገሮች ጋር በሚደረግ ንግግር መሆን አለበት አለች

መንግሥትን ከፋኖና ከኦነግ ሸኔ ጋር ለማነጋገር ፍላጎቷን ገልጻለች የኢትዮጵያ የባህር...