Sunday, March 3, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ዜናየዓለም ምግብ ፕሮግራም ያቋረጠውን የምግብ ዕርዳታ ለመጀመር መወሰኑን አስታወቀ

የዓለም ምግብ ፕሮግራም ያቋረጠውን የምግብ ዕርዳታ ለመጀመር መወሰኑን አስታወቀ

ቀን:

  • እስከ ሚያዚያ ድረስ 9.8 ቢሊዮን ብር በአስቸኳይ ያስፈልገኛል ብሏል

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የዓለም የምግብ ፕሮግራም (WFP) በኢትዮጵያ ያቋረጠውን የዕርዳታ አቅርቦት በተሻሻለ የአሠራር ሥርዓት በድጋሚ ለመጀመር መወሰኑን፣ ለዚህም እስከ መጪው ሚያዚያ ወር ድረስ ለማቅረብ ላቀደው የሰብዓዊ ዕርዳታ 178 ሚሊዮን ዶላር (9.8 ቢሊዮን ብር) እንደሚያስፈልገው አስታወቀ።

በኢትዮጵያ መጠነ ሰፊ የምግብ ዕርዳታ ምዝበራ ማጋጠሙን ተከትሎ፣ የዓለም ምግብ ፕሮግራምና የአሜሪካ ዓለም አቀፍ ተራድኦ ድርጅት (ዩኤስኤድ) ያቀርቡት የነበረውን የምግብ ዕርዳታ በአገር አቀፍ ደረጃ ማቋረጣቸው ይታወሳል።

የዓለም ምግብ ፕሮግራም በኢትዮጵያ ያቋረጠውን የምግብ ዕርዳታ አቅርቦት እንደገና ለመጀመር የወሰነው የተፈጸመውን የዕርዳታ ምዝበራ የተመለከተ የተሟላ ግምገማ በማካሄድና ቀጣይ የዕርዳታ አቅርቦት ተግባር ተጋላጮችን አስመልክቶ የተሟላ ማስረጃ በመያዝ፣ ግልጽነትና የአሠራር ነፃነትን በሚያረጋግጥ መንገድ እንዲፈጸም የሚያስችል የአሠራር ሥርዓት ለመዘርጋት ከኢትዮጵያ መንግሥት ጋር ስምምነት በመደረሱ መሆኑን አስታውቋል።

- Advertisement -

Video from Enat Bank Youtube Channel.

በዚህም መሠረት የዓለም ምግብ ፕሮግራም የዕርዳታ አቅርቦቱን እንደገና ሲጀምር የጠንካራ ጥበቃና ቁጥጥር የተደገፈ ሥርዓት እንደሚዘረጋ፣ ከእነዚህም መካከል በጣም ተጋላጭ የሆኑትን ማኅበረሰቦች በጥንቃቄ የመለየትና በዲጂታል መንገድ የመመዝገብ ግልጽ መሥፈርቶችን ጥቅም ላይ ማዋል፣ በጣም የተጋለጡ ማኅበረሰቦችን ለማረጋገጥ ከአካባቢው ማኅበረሰቦች ጋር መሥራትና የምግብ ዕርዳታ ከማከማቻ መጋዘኖች ወደ ተጠቃሚዎች ሲንቀሳቀስ ክትትል የሚያደርግ ጠንካራ ሥርዓት በመዘርጋት እንደሚሆን ገልጿል።

በተጨማሪም የምግብ ዕርዳታን ያላግባብ ጥቅም ላይ የሚያውሉ ሕገወጦችን ለመለየትና ክትትል ለማድረግ የሚያስችል፣ የማኅበረሰብ ግብረ መልሶችና የሪፖርት አቀራረብ ዘዴዎችን ተግባራዊ እንደሚያደርግም አስታውቋል።

‹‹የዓለም ምግብ ፕሮግራም የኢትዮጵያ ቢሮና አጋሮቻችን እዚህ ደረጃ ላይ ለመድረስ ሌት ተቀን ሲሠሩ ቆይተዋል። በአሁኑ ወቅት በመንግሥትና በአጋሮች ተደግፎ ስምምነት የተደረሰበት የአሠራር ሥርዓት በአገሪቱ ውስጥ ለሰብዓዊ ዕርዳታ አዲስ መሥፈርት ያስቀምጣል ብለን እናምናለን። አሁን ሙሉ ትኩረታችን ዕርዳታ ሳያገኙ ብዙ ጊዜ ለቆዩ ኢትዮጵያውያን የምግብ ዕርዳታ እንዲደርስ ማድረግ ነው፤›› ሲሉ፣ የተቋሙ ዋና ዳይሬክተር ሲንዲ ማኬን ተናግረዋል።

አዲሱን የዕርዳታ አቅርቦት ሥርዓት ለመፈተሽ በትግራይ ክልል ውስን ሥርጭት የተካሄደ መሆኑንና፣ ስኬታማ ውጤት ማስገኘቱ መረጋገጡን የጠቀሰው ተቋሙ፣ በዚህም ምክንያት የዕርዳታ አቅርቦቱን በአፋር፣ በአማራ፣ በሶማሌና በትግራይ ክልሎች በድርቅና በግጭት ለተጎዱ የማኅበረሰብ ክፍሎች ለማሠራጨት ማቀዱን ገልጿል። በመቀጠልም በመላ አገሪቱ ለከፋ ችግር ለተጋለጡ ማኅበረሰቦች ዕርዳታ የማቅረብ ተግባሩ እንደሚስፋፋ አክሏል።

ያቋረጠውን አገልግሎት ለመጀመር በአገር ውስጥ የሚገኝ የምግብ ክምችትን ጥቅም ላይ እንደሚያውል የገለጸው ተቋሙ፣ ኢትዮጵያ ውስጥ በጣም ተጋላጭ ለሆኑ ሰዎች የምግብ ዕርዳታ እስከ ሚያዚያ ወር ድረስ ለማቅረብ ግን 178 ሚሊዮን ዶላር (9.8 ቢሊዮን ብር) በአስቸኳይ እንደሚያስፈልገው አስታውቋል።

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የአዲስ አበባ ነዋሪዎች ቁጥር ሲጨምር የሚኒባስ ታክሲዎች ቁጥር እየቀነሰ መምጣቱ ሊታሰብበት ይገባል

በአዲስ አበባ ከተማ የትራንስፖርት አገልግሎት በመስጠት ከፍተኛ የሚባለውን ድርሻ...

ሃምሳ ዓመታት ያስቆጠረው አብዮትና የኢትዮጵያ ፖለቲካ ውጣ ውረድ

የኢትዮጵያ ሕዝቦች የዴሞክራሲ ለውጥ ጥያቄ የሚነሳው ከፋሺስት ኢጣሊያ ወረራ...

በአዲስ አበባ ንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት የተፈጸመው ሕገወጥ ተግባር ምንድነው?

የአዲስ አበባ ንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት የዳይሬክተሮች ቦርድ፣...

በአዲስ አበባ ንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ላይ ምርመራ እንዲደረግ ውሳኔ ተላለፈ

ፕሬዚዳንቷና ዋና ጸሐፊው ተጠያቂ ሊሆኑ ይችላሉ ተብሏል ከአዲስ አበባ ንግድና...