Friday, March 1, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ዜናየመንግሥትና የኦነግ ሸኔ ንግግር ያለ ውጤት ተጠናቀቀ

የመንግሥትና የኦነግ ሸኔ ንግግር ያለ ውጤት ተጠናቀቀ

ቀን:

መንግሥት ከኦነግ ሸኔ (የኦሮሞ ነፃነት ሠራዊት) ጋር በታንዛንያ ዋና ከተማ ዳሬሰላም ሲያካሂድ የነበረው ሁለተኛው ዙር ንግግር ያለ ውጤት መጠናቀቁን፣ ማክሰኞ ኅዳር 11 ቀን  2016 ዓ.ም፣ ምሽት ባወጣው መግለጫ አስታወቀ፡፡

ከዚህ ቀደም በታንዛኒያ ዛንዚባር የተካሄደው ንግግር ያለ ውጤት ተጠናቆ እንደነበር ያስታወሰው መንግሥት፣ የአሁኑም ፍሬ ሳያፈራ ውጤት አልባ ሆኖ መቅረቱን በመግለጫው ጠቁሟል፡፡

ባለፉት ሁለት ሳምንታትም የሽብር ቡድኑ ካለፈው ስህተት ተምሮ የድርድር ነጥቦቹንም ኢትዮጵያ ከደረሰችበት ምዕራፍ ጋር ለማጣጣም ይሞክር ይሆናል በሚል ተስፋ ሁለተኛ ዙር ውይይት በታንዛንያ ዳሬሰላም ሲካሄድ መቆየቱን ያስታወቀው መንግሥት፣  ‹‹በሽብር ቡድኑ ዘንድ በዚህኛው ዙርም ‹መንግሥት አዝሎ መንግሥት ያድርገኝ› ከሚል አጉራ ዘለልነት ያለፈ የድርድር ነጥብ ማምጣት አልቻለም ሲል ድርድሩ የከሸፈበትን ምክንያት አስረድቷል።

- Advertisement -

Video from Enat Bank Youtube Channel.

‹‹በኦሮሚያ ክልል አንዳንድ አካባቢዎች በመንቀሳቀስ በሕዝቦች ሕይወትና ንብረት ጉዳት በማድረስ የሰላም ጠንቅ ሆኖ ከቆየው የሸኔ የሽብር ቡድን ጋር፣ በታንዛንያ ዛንዚባር ከወራት በፊት ውይይት ተካሂዶ ሳይቋጭ መቅረቱ ይታወሳል፤›› ያለው መንግሥት፣ ‹‹በዚሁ ውይይት ወቅት የሽብር ቡድኑ ከ60 ዓመታት በፊት የኦሮሞም ሆነ የሌሎች የኢትዮጵያ ብሔረሰቦች በሙሉ ጥያቄዎች የነበሩና ተመልሰው ያደሩ ጥያቄዎችን አንስቷል፤›› ብሏል።

በተለይም ከለውጡ በኋላ በሥራ ላይ የዋሉ ጉዳዮችን ከማነብነብ ውጪ የሚቆጠርና የሚቋጠር አጀንዳ ማምጣት ያልቻለው ኦነግ ሸኔ፣ በመንግሥት በኩል በስክነትና በማግባባት ላይ ብቻ ታጥሮ በቀጠሮ ተንጠልጥሎ እንዲቆይ ማድረጉ ተመራጭ አካሄድ ነበር ሲልም መንግሥት አስታውቋል።

‹‹ነገር ግን የኢፌዴሪ መንግሥት በአገሪቱ ሰላም ሰፍኖ ኢትዮጵያ ያሏትን ፀጋዎች ወደ ተጨባጭ ሀብትና አቅም ቀይራ ብልፅግናዋን ታረጋግጥ ዘንድ ካለው ጉጉት በመነጨ፣ ከግማሽ መንገድ በላይ ተጉዞ ለጉዳዩ ዕልባት ለመስጠት ሞክሯል። ነገር ግን የሽብር ቡድኑ በሰላም ጊዜ እንዴት መኖር እንዳለበት ለማሰብ ቸግሮት ታይቷል፤›› ብሏል።

‹‹ኦነግ ሸኔ በዜጎች ደምና እንግልት መነገዱን መርጧል፤›› ያለው መንግሥት፣ ውይይቱ በትናንትናው ዕለት ያለ ውጤት መበተኑንና ለሰላማዊ መፍትሔ ያለው አቋም እንደተጠበቀ ሆኖ ሕግና ሕገ መንግሥታዊ ሥርዓቱን የማስከበር ተልዕኮውን አጠናክሮ እንደሚቀጥል አስታውቋል። ውይይቱ እንዲሳካ ጥረት ሲያደርጉ ለነበሩ አካላት ሁሉ ምሥጋናውን አቅርቧል፡፡

በመንግሥት በኩል ሕገ መንግሥቱንና የአገሪቱን ሉዓላዊነት ለመቀበል ዝግጁ ከሆነ ከማንኛውም ኃይል ጋር በውይይት ችግሮችን ለመፍታት ያለማሳለስ ጥረት እንደሚያደርግ፣ ይህ እንደተጠበቀ ሆኖ ከመከላከያ ትይዩ የሚታይ ትጥቅ የመያዝና በመንግሥት ውስጥ መንግሥት የመሆን ልክፍትን ግን በውይይት ሽፋን መለማመድ አደገኛ አገር አፍራሽ አዝማሚያ ነው ብሎ እንደሚያምን መንግሥት በመግለጫው አስታውቋል፡፡

መንግሥት ከኦነግ ሸኔ ጋር ከሁለት ሳምንት በፊት የጀመረውን ሁለተኛ ዙር ንግግር ኢጋድ፣ አሜሪካ፣ ኬንያና ኖርዌይ ማመቻቸታቸው መዘገቡ ይታወሳል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

[ክቡር ሚኒስትሩ ወደ መኖሪያ ቤታቸው ሲገቡ ባለቤታቸው በቴሌቪዥን የሚተላለፈውን ዜና በመደነቅ እየተመለከቱ አገኟቸው]

እንዲያው የሚደንቅ ነው እኮ። ምኑ? ዜና ተብሎ በቴሌቪዥን የሚተላለፈው ነገር ነዋ፡፡ ምኑ...

በኦሮሚያ የሚፈጸሙ ግድያዎችና የተጠያቂነት መጥፋት

የካቲት 11 ቀን 2016 ዓ.ም. ቢሾፍቱ አቅራቢያ በሚገኘው የዝቋላ...

የኢትዮጵያ መዋዕለ ንዋይ ገበያ ከሚያስፈልገው ካፒታል ውስጥ 90 በመቶውን ሰበሰበ

እስካሁን 15 ባንኮች የመዋዕለ ንዋይ ገበያው ባለድርሻ ሆነዋል የኢትዮጵያ መዋዕለ...

አዲሱ የንብ ባንክ ቦርድ የባንኩን ካፒታል በአሥር ቢሊዮን ብር ለማሳደግ ማቀዱ ተሰማ

አዲሱ የንብ ኢንተርናሽናል ባንክ የዳይሬክተሮች ቦርድ የባንኩን ካፒታል በአሥር...