Monday, February 26, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ዜናፓርላማው የዳኝነት ክፍያን ለማሻሻል የቀረበለትን ረቂቅ ደንብ ለሁለተኛ ጊዜ ወደ አረቀቀው አካል...

ፓርላማው የዳኝነት ክፍያን ለማሻሻል የቀረበለትን ረቂቅ ደንብ ለሁለተኛ ጊዜ ወደ አረቀቀው አካል መለሰ

ቀን:

  • በፍትሕ ሥርዓቱ ተጎጂ የሆነን ሰው መካስ ሲገባ የዳኝነት

ክፍያ መጠየቅ ተገቢ አይደለም ተብሏል

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሕግና ፍትሕ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የፌዴራል ፍርድ ቤቶች የዳኝነት የክፍያ መጠንን ለማሻሻል የተመራለትን ረቂቅ ደንብ በድጋሚ መታየት አለበት በማለት፣ ለሁለተኛ ጊዜ ደንቡን ላረቀቀው የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት መለሰ።

ቋሚ ኮሚቴው በተመራለት ረቂቅ ደንብ ላይ ዓርብ ኅዳር 7 ቀን 2016 ዓ.ም. ከባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት ያደረገ ሲሆን፣ በመድረኩ የተሳተፉ የፍትሕ ሥርዓቱ ባለድርሻዎች በረቂቅ ደንቡ ድንጋጌዎች ላይ የሰሉ ትችቶችን ጨምሮ ሊስተካከሉ ይገባቸዋል ያሏቸውን ነጥቦች አቅርበዋል። በተለይም በረቂቅ ደንቡ የተቀመጡ የዳኝነት ክፍያ ተመኖች የተጋነኑ መሆናቸው፣ እንዲሁም አንዳንዶቹ ቅቡል የሆነ አመክንዮ ይጎድላቸዋል የሚል አስተያየት ጎልቶ ተደምጧል።

- Advertisement -

Video from Enat Bank Youtube Channel.

በባለድርሻ ውይይቱ ላይ ከተገኙት አካላት መካከል አንዱ የፌዴራል የጠበቆች ማኅበር ሲሆን፣ ማኅበሩ በተወካዩ አማካይነት በረቂቅ ደንቡ ላይ በርካታ አስታያየቶችን አቅርቧል። ከእነዚህም መካከል ረቂቅ ደንቡ የክስ አቤቱታ ሲሻሻል ድጋሚ የዳኝነት ክፍያ መጠየቁ ተገቢ አለመሆን፣ ምክንያቱም አቤቱታው ተሻሻለ እንጂ የተጠየቀው ዳኝነት አልተቀየረም የሚለው ይገኝበታል። አቤቱታን ማሻሻል ክሱን በማጥራት ፍርድ ቤትን ያግዛል እንጂ፣ ሌላ ዳኝነትን የሚጠይቅ ባለመሆኑ ዳግመኛ የዳኝነት ክፍያ መጠየቅ ተገቢ ባለመሆኑ እንዲሻሻል ማኅበሩ ጠይቋል። 

ሌላው ለሰበር በሚቀርብ አቤቱታ ላይም ለዳኝነት አንድ አራተኛ እንዲከፈል የሚል ድንጋጌ በረቂቅ ደንቡ መካተቱ ተገቢ አይደለም የሚል ክርክር ማኅበሩ አቅርቧል።

በንጉሡ ዘመን እንዲሁም በደርግ ጊዜ ለሰበር የሚቀርብ አቤቱታ በነፃ ይታይ እንደነበረ፣ በኢሕአዴግ ዘመን የመጀመሪያ ዓመታትም ቢሆን ለሰበር የሚቀርብ አቤቱታ በነፃ ሲስተናገድ ከቆየ በኋላ በአንድ ቀላጤ የዳኝነት ክፍያ መወሰኑን የማኅበሩ ተወካይ አብራርተዋል።

ለሰበር ችሎት የሚቀርብ አቤቱታ መሠረታዊ የሕግ ስህተትን ለማረም የሚቀርብ መሆኑን የጠቆሙት የማኅበሩ ተወካይ፣ አንድ ሰው ገንዘቡን አሟጦ እስከ መጨረሻ ተከራክሮ መሠረታዊ የሕግ ስህተት ተፈጽሞበት፣ ፍትሕ አጣሁ በማለት የተፈጸመበትን መሠረታዊ የሕግ ስህተት እንዲታረምለት አቤቱታ በማቅረቡ የዳኝነት ሊጠየቅ አይገባም ብለዋል። 

‹‹በፍትሕ ሥርዓቱ መሠረታዊ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት ሰው ተጎጂ ነው፣ ሲሆን ሊካስ ነበር የሚገባው። ካሳው ቢቀር የፍትሕ ሥርዓቱ መሠረታዊ የሕግ ስህተት የፈጸመበት ሰው እንዴት የዳኝነት ክፈል ይባላል? ስለዚህ ይኼ ነገር ቢስተካከል ጥሩ ነው፤›› ሲሉ አሳስበዋል። 

የቋሚ ኮሚቴው ምክትል ሰብሳቢ በሰጡት አስተያየት፣ የዳኝነት ክፍያን ማሻሻል ተገቢ ቢሆንም፣ ፍትሕ የማግኘት መብትን እንዳይጋፋ ግን መጠንቀቅ እንደሚያስፈልግ ገልጸዋል። በዚህም ምክንያት የቀረበው ረቂቅ ደንብ እንደገና ሊታይ ይገባል ብለዋል።

ይኸው ቋሚ ኮሚቴ በጥቅምት ወር 2016 ዓ.ም. የመጀመሪያ ሳምንት ላይ በረቂቅ ደንቡ ላይ ከፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት አመራሮች ጋር ተወያይቶ የነበረ ሲሆን፣ በዚህም ወቅት የዳኝነት ክፍያ ተመኑ ፍትሕ የማግኘት መብትን እንዳያጣብብ ማስተካከያ ሊደረገበት ይገባል ብሎ ረቂቅ ደንቡን ላመነጨው ጠቅላይ ፍርድ ቤት እንደመለሰው ይታወሳል።

ረቂቅ ደንቡ ለ60 ዓመታት የቆየውን ደንብ የሚተካና ፍርድ ቤቶች በገቢ ራሳቸውን እንዲደጉሙ ለማስቻል ያለመ ነው። አሁን ባለው አሠራር የሚጠየቀው የዳኝነት ክፍያ ከ0.50 ሳንቲም እስከ 12 ሺሕ 850 ብር ብቻ ሲሆን፣ ረቂቅ ደንቡ ይህንን ተመን በማሻሻል የዳኝነት ክፍያዎች በመቶኛ የአከፋፈል መጠን እንዲሰሉ ለማድረግ አቅዷል።

በዚህም መሠረት እስከ 20,000 ብር የገንዘብ መጠን የሚደርስ ዳኝነት ለሚጠይቁ መዝገቦች ስምንት በመቶ የዳኝነት ክፍያ የሚጠይቅ ሲሆን፣ የገንዘብ መጠኑ በጨመረ ቁጥር በመቶኛ የሚሰላው የክፍያ መጠን እየቀነሰ እንደሚሄድ ረቂቅ ደንቡ ያስረዳል። በመሆኑም ከዚህ ቀደም የዳኝነት ክፍያ ተመን ላልነበራቸው የገንዘብ መጠኖች አዲስ ተመን ያወጣ ሲሆን፣ ከ200 ሚሊዮን ብር በላይ ለሆኑ መዝገቦች አንድ በመቶ የዳኝነት ክፍያን ተምኖ ደንግጓል።

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የመጣንበትና አብረን የምንዘልቅበት የጋራ እሴታችን ለመሆኑ ነጋሪ ያስፈልጋል ወይ?

በኑረዲን አብራር በአገራችን ለለውጥ የተደረጉ ትግሎች ከመብዛታቸው የተነሳ ሰላም የነበረበት...

አልባሌ ልሂቃንና ፖለቲከኞች

በበቀለ ሹሜ በ2016 ዓ.ም. ኅዳር ማክተሚያ ላይ ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ...

አሜሪካ የኢትዮጵያ የባህር በር ጥያቄ ተገቢነት ቢኖረውም ከጎረቤት አገሮች ጋር በሚደረግ ንግግር መሆን አለበት አለች

መንግሥትን ከፋኖና ከኦነግ ሸኔ ጋር ለማነጋገር ፍላጎቷን ገልጻለች የኢትዮጵያ የባህር...