Monday, February 26, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ዜናየዕንባ ጠባቂ መርማሪዎች ያለ መከሰስ ልዩ መብት እንዲኖራቸው የሚፈቅድ አዋጅ ፀደቀ

የዕንባ ጠባቂ መርማሪዎች ያለ መከሰስ ልዩ መብት እንዲኖራቸው የሚፈቅድ አዋጅ ፀደቀ

ቀን:

የኢትዮጵያ የሕዝብ ዕንባ ጠባቂ ተቋምን እንደ አዲስ ለማቋቋም ተሻሽሎ በፓርላማ ሙሉ ድምፅ የፀደቀው አዋጅ፣ የተቋሙ መርማሪዎች ያለ መከሰስ መብት እንዲኖራቸው መፍቀዱ ታወቀ፡፡

ያለ መከሰስ ልዩ መብት ለተቋሙ መርማሪዎች እንዲሰጥ በፓርላማ አዋጁ የፀደቀው፣ መርማሪዎቹ ከዚህ ቀደም ከሕዝብ የቀረቡ አቤቱታዎችን ለማጣራት ሲንቀሳቀሱ በአንዳንድ አካላት እየተያዙ ምርመራቸውን እንዲያቋርጡ በመገደዳቸው ምክንያት መሆኑን፣ በፓርላማው የዴሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ኃላፊ አቶ እውነቱ አለነ ገልጸዋል፡፡

በፀደቀው አዋጅ መሠረት የዕንባ ጠባቂ መርማሪዎች ከፓርላማው አባላት፣ እንዲሁም ከሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ሠራተኞች እኩል ያለ መከሰስ መብት ይኖራቸዋል፡፡

- Advertisement -

Video from Enat Bank Youtube Channel.

‹‹የዕንባ ጠባቂ ተቋሙ ሠራተኞችና መርማሪዎች በድፍረት ሥራቸውን እንዲሠሩ እያደረግን አይደለም፡፡ በከፍተኛ ሥጋት ውስጥ ሆነው ነው ሲሠሩ የነበረው፡፡ ይኼ ትክክል አይደለም፡፡ የዕንባ ጠባቂ ተቋም ሠራተኞች አቤቱታ ሊያጣሩ ሲሄዱ ተይዘው ሥራቸውን እንዳይሠሩ የተደረጉበት ሁኔታ አለ፡፡ አቤቱታ እየመረመሩ ባሉበት ሁኔታ ተይዘው ሥራቸውን እንዲያቋርጡ የተደረገበት ሁኔታ አለ፤›› ሲሉ አቶ እውነቱ አብራርተዋል፡፡

የተሻሻለው አዲሱ የዕንባ ጠባቂ ተቋም መቋቋሚያ አዋጅ አምስት ዋና ዋና ለውጦችን ያዘለ ሲሆን፣ የተቀረው ግን የተቋሙን የምርመራ ወሰንና ሥልጣን የተመለከተ ነው፡፡

ተቋሙ እስካሁን በመንግሥት ተቋማትና መንግሥታዊ አካላት ላይ የሚቀርቡ አቤቱታዎችን ማጣራትና መመርመር ላይ ብቻ ያተኮረ ሲሆን፣ አሁን ግን በአዋጁ የግል ድርጅቶችንም እንዲመረምር ሥልጣን ተሰጥቶታል፡፡

ከግል ድርጅቶች ውስጥ ተቋሙ እንዲመረምር ሥልጣን የተሰጠው ኃላፊነታቸው የተወሰነ የግል ማኅበርና አክሲዮን ማኅበራትን ብቻ ነው፡፡ ለዚህ ምክንያት የሆነው ባለፈው ዓመት ወደ ዕንባ ጠባቂ ተቋሙ ከመጡት ስድስት ሺሕ አቤቱታዎች ውስጥ 75 በመቶ ያህሉ በግል ድርጅቶች ላይ የቀረቡ በመሆናቸው ነው ተብሏል፡፡ ‹‹በግል ተቋማት አካባቢ የሚፈጸሙ በደሎች ይበዛሉ፤›› ሲሉ የቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢው ገልጸዋል፡፡

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባዔ አቶ ታገሰ ጫፎ በበኩላቸው፣ ‹‹አብዛኛው አቤቱታ በግል ተቋማት ላይ ነው የሚቀርበው፡፡ በተለይ በፋይናንስ ትልልቅ ድርጅቶች፣ እንዲሁም ከመንግሥት ጋር ግንኙነት ባላቸው ተቋማት የሚፈጸም በደል ይበዛል፤›› ብለዋል፡፡ ‹‹ወደ ግል ተቋማት ከመግባታችን በፊት በመንግሥት ተቋማት ላይ የሚቀርበውን አቤቱታ መርምረን ጨርሰናል ወይ?›› ሲሉ ጠይቀዋል፡፡

ሌላው በአዋጁ የተሻሻለው ለዕንባ ጠባቂ ተቋም በክልል ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤቶች የሚሾሙ ኃላፊዎችን ሹመት ለማፅደቅ፣ ከዚህ በኋላ የፓርላማ ሒደት ማለፍ አስፈላጊ አለመሆኑ ነው፡፡ ለአሥራ ሁለት ክልሎችና ለሁለት የከተማ አስተዳደሮች ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኃላፊዎች ሲሾሙ በቀጥታ ሹመታቸው ይፀድቃል ማለት ነው፡፡

ከዚህ ቀደም በነበረው አሠራር እያንዳንዱን የቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ለመምረጥ በፓርላማው መፅደቅ ነበረበት፡፡ ሒደቱ ረዥም ጊዜ በመፍጀቱ ባለፉት ሦስት ዓመታት ኃላፊ የሌላቸው ቅርንጫፎች ጽሕፈት ቤቶች መኖራቸው ተገልጿል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የመጣንበትና አብረን የምንዘልቅበት የጋራ እሴታችን ለመሆኑ ነጋሪ ያስፈልጋል ወይ?

በኑረዲን አብራር በአገራችን ለለውጥ የተደረጉ ትግሎች ከመብዛታቸው የተነሳ ሰላም የነበረበት...

አልባሌ ልሂቃንና ፖለቲከኞች

በበቀለ ሹሜ በ2016 ዓ.ም. ኅዳር ማክተሚያ ላይ ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ...

አሜሪካ የኢትዮጵያ የባህር በር ጥያቄ ተገቢነት ቢኖረውም ከጎረቤት አገሮች ጋር በሚደረግ ንግግር መሆን አለበት አለች

መንግሥትን ከፋኖና ከኦነግ ሸኔ ጋር ለማነጋገር ፍላጎቷን ገልጻለች የኢትዮጵያ የባህር...