Friday, March 1, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ዜናየአማራ ሕዝብ ንስር ፓርቲ ምሥረታውን ይፋ ሊያደርግ ነው

የአማራ ሕዝብ ንስር ፓርቲ ምሥረታውን ይፋ ሊያደርግ ነው

ቀን:

ከአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) የለቀቁ አባላትን ያሰባሰበውና ‹‹የአማራ ሕዝብ ንስር ፓርቲ›› በሚል ስም የተደራጀው ፓርቲ፣ ሐሙስ ኅዳር 13 ቀን 2016 ዓ.ም. በአዲስ አበባ ራስ አምባ ሆቴል ምሥረታውን ይፋ እንደሚያደርግ ገለጸ፡፡

ሐምሌ 2 ቀን 2015 ዓ.ም. 245 መሥራች አባላት ተሰባስበው በወሰኑት መሠረት፣ ለብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የዕውቅና ጥያቄ ማቅረቡንና ነሐሴ 11 ቀን 2015 ዓ.ም. ቅድመ ዕውቅና ሰርተፊኬት እንደተሰጠው የፓርቲው አደራጆች ለሪፖርተር ተናግረዋል፡፡

አማራ ሆን ተብሎ በተለየ ሁኔታ ለጥቃት መጋለጡን ያስረዱት የፓርቲው አደራጆች፣ አገር አቀፍ ዕውቅና ለማግኘት እየሠሩ መሆኑንም ገልጸዋል፡፡

- Advertisement -

Video from Enat Bank Youtube Channel.

የአደራጅ ኮሚቴው ሰብሳቢ አቶ አንተነህ ስለሺ የመመሥረቻ ጉባዔ ለማካሄድ ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ ምርጫ ቦርድ በፈቀደው የሦስት ወራት የመሥራች ጉባዔ ማድረጊያ የዝግጅት ጊዜን በመጠቀም ርዕዮተ ዓለም፣ ፕሮግራም፣ ማኒፌስቶና ድርጅታዊ አሠራርን የተመለከቱ ደንቦችን ጨምሮ የተለያዩ ሰነዶች እየተዘጋጁ መሆናቸውንም አስረድተዋል፡፡

የአዲሱ ፓርቲ ዋና የትግል ግብ ምን እንደሆነ የተጠየቁት አቶ አንተነህ፣ በአማራ ላይ ያነጣጠረውን ማንነት ተኮር ጥቃት ቅድሚያ ሰጥቶ ማስቆም እንደሆነ ገልጸዋል፡፡

‹‹በእኛ ግምገማ በተጨባጭ የአማራ ሕዝብ የህልውና አደጋ አጋጥሞታል፤›› ሲሉ የተናገሩት አቶ አንተነህ፣ ‹‹በየአካባቢው ማንነቱን መሠረት ያደረገ ዘር ተኮር ጭፍጨፋ እየተካሄደበት ይገኛል፤›› ብለዋል፡፡

አቶ አንተነህ አክለውም፣ ‹‹የአማራ ሕዝብ ፍላጎት የሚሟላውና ጥያቄዎቹ የሚመለሱት የሌላው ሕዝብ ጥያቄ ሳይጨፈለቅ ነው፡፡ ከዚያ ውጪ መሆን አይቻልም፤›› ሲሉም አክለዋል፡፡

አዲሱ ፓርቲያቸው ከሌሎች ወንድምና እህት ሕዝቦች ፓርቲዎች ጋር በጋራ ሆኖ የሚታገልባቸው ጉዳዮች እንዳሉ ጠቁመው፣ ለአማራ ሕዝብ እንቆማለን ከሚሉም ሆነ ከሌሎች ጋር በሚያቀራርቡ ጉዳዮች ላይ አብሮ መሥራትን እንደሚመርጥ አስረድተዋል፡፡

በሌላ በኩል የአማራ ሕዝብን ጥያቄ ፓርቲ በማብዛት ማስመለስ ይቻላል ወይ? አብን፣ የአማራ ብልፅግናና ሌሎችም በተበታተነ መንገድ እየተንቀሳቀሱ ከሚታገሉ ይልቅ ተሰባስቦና አቅምን አጠናክሮ መታገሉ የሕዝቡን ጥያቄ ለመመለስ የተሻለው አማራጭ አይሆንም ወይ? የሚል ጥያቄም ተነስቶላቸው ነበር፡፡

‹‹በእኛ እምነት አማራ ብልፅግና የለም፤›› ሲሉ ምላሽ የሰጡት አቶ አንተነህ፣ ‹‹አብን የሚባለው ፓርቲም አለሁ የሚል ከሆነ አሁን ባለው የፖለቲካ ገበያ ውስጥ የሚያደርገው የነቃ ተሳትፎ የታለ?›› ሲሉ በጥያቄ ምላሽ ሰጥተዋል፡፡ ሕዝቡ አሁን ለአማራ ሕዝብ እንታገላለን የሚሉ ፓርቲዎችን እንቅስቃሴ የሚከታተል በመሆኑ፣ የትኛው ለአማራ ሕዝብ እንደቆመ ጠንቅቆ ያውቃል ብለዋል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

[ክቡር ሚኒስትሩ ወደ መኖሪያ ቤታቸው ሲገቡ ባለቤታቸው በቴሌቪዥን የሚተላለፈውን ዜና በመደነቅ እየተመለከቱ አገኟቸው]

እንዲያው የሚደንቅ ነው እኮ። ምኑ? ዜና ተብሎ በቴሌቪዥን የሚተላለፈው ነገር ነዋ፡፡ ምኑ...

በኦሮሚያ የሚፈጸሙ ግድያዎችና የተጠያቂነት መጥፋት

የካቲት 11 ቀን 2016 ዓ.ም. ቢሾፍቱ አቅራቢያ በሚገኘው የዝቋላ...

የኢትዮጵያ መዋዕለ ንዋይ ገበያ ከሚያስፈልገው ካፒታል ውስጥ 90 በመቶውን ሰበሰበ

እስካሁን 15 ባንኮች የመዋዕለ ንዋይ ገበያው ባለድርሻ ሆነዋል የኢትዮጵያ መዋዕለ...

አዲሱ የንብ ባንክ ቦርድ የባንኩን ካፒታል በአሥር ቢሊዮን ብር ለማሳደግ ማቀዱ ተሰማ

አዲሱ የንብ ኢንተርናሽናል ባንክ የዳይሬክተሮች ቦርድ የባንኩን ካፒታል በአሥር...