Monday, February 26, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊበዋግ ኸምራ ብሔረሰብ ዞን በተከሰተ የኮሌራ ወረርሽኝና የምግብ እጥረት ዘጠኝ ሰዎች ሕይወት...

በዋግ ኸምራ ብሔረሰብ ዞን በተከሰተ የኮሌራ ወረርሽኝና የምግብ እጥረት ዘጠኝ ሰዎች ሕይወት ማለፉ ተሰማ

ቀን:

በአማራ ክልል በዋግ ኸምራ ብሔረሰብ ዞን በተከሰተው ድርቅ ሳቢያ ከጥቅምት 19 2016 ዓ.ም. ጀምሮ በተቀሰቀሰ የኮሌራ ወረርሽኝና የምግብ ዕጦት፣ የዘጠኝ ሰዎች ሕይወት ማለፉን የዞኑ ጤና መምርያ አስታወቀ፡፡

የኤችአይቪ/ኤድስና የቲቪ በሽታ ታማሚዎች የነበሩ ስድስት ሰዎች በወቅቱ ሕክምና ባለማግኘታቸውና በተከሰተው የምግብ ዕጦት ሳቢያ ሲሞቱ፣ ወረርሽኙ መከሰቱ ሳይታወቅ የበሽታው ተጠቂ የነበሩ ሦስት ሰዎች ወደ ሕክምና ተቋም ሳይደርሱ ሕይወታቸው ማለፉን፣ የዞኑ ጤና መምርያ ኃላፊ አቶ አሰፋ ነጋሽ ለሪፖርተር ተናግረዋል፡፡

ወረርሽኙ ዞኑ ውስጥ ባሉ ዘጠኝ ወረዳዎች መዳረሱን የተናገሩት አቶ አሰፋ፣ ከ160 በላይ ሰዎች በወረርሽኙ ተጠቅተው ሕክምና እየተደረገላቸው ነው ብለዋል፡፡

- Advertisement -

Video from Enat Bank Youtube Channel.

በዞኑ የተከሰተውን የኮሌራ ወረርሽኝ ለመከላከል የተባበሩት መንግሥታት የሕፃናት መርጃ ድርጅት (ዩኒሴፍ) 3.6 ሚሊዮን ብር የሚገመት የቁሳቁስ ድጋፍ ማድረጉን፣ የመምርያ ኃላፊው አስረድተዋል፡፡

በዞኑ የወባ በሽታ ባልተለመደ ሁኔታ መጨመሩን የተናገሩት አቶ አሰፋ፣ ‹‹ወባን ለመከላከል በምንሠራበት ወቅት ኮሌራ መከሰቱ ችግሩ እንዲባባስ አድርጎታል፤›› ብለዋል፡፡

‹‹በዞኑ በሚገኙ ሁለት ወረዳዎች ውስጥ ባያ 20 ቀበሌዎችን ከሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት ጀምሮ መንግሥት እያስተዳደራቸው አይደለም፡፡ ዛሬም የሕወሓት ኃይሎች እንደፈለጉ እየገቡና እየወጡ በመሆናቸው፣ ለኅብረተሰቡ የሕክምና ቁሳቁሶችን ጨምሮ ሌሎች መሠረታዊ አገልግሎቶችን ለማድረስ አልተቻለም፤›› ሲሉ የመምርያ ኃላፊው ገልጸዋል፡፡

‹‹በክልሉ ባለው ወቅታዊ ችግር መንገዶች በመዘጋታቸው የጤና አገልግሎት ተደራሽ ለማድረግ መሠረታዊ ክፍተት ፈጥሮብናል፤›› ያሉት አቶ አሰፋ፣ የክልሉን መንግሥት ጨምሮ አጋር ድርጅቶች ድጋፍ እያደረጉ ቢሆንም ለሕክምና የሚወጣው ወጪ ከፍተኛ በመሆኑ ታካሚዎች የሚተኙበት አልጋ፣ ፍራሽ፣ ድንኳኖችና የመሳሰሉት ግብዓቶች እጥረት እንዳሉባቸው ገልጸዋል፡፡ ከእነዚህ ዓብዓቶች በተጨማሪ ለሕክምና ባለሙያዎች ደመወዝ ስለማይከፈላቸው ክፍተት መፈጠሩን ጠቁመዋል፡፡

‹‹በየአቅጣጫው በታጣቂዎች ተከበን ነው ያለነው፤›› ያሉት የመምርያ ኃላፊው፣ ባለው የፀጥታ ችግር በተለይም ሴቶችና ሕፃናት ለከፋ ችግር መጋለጣቸውን አብራርተዋል፡፡

መንግሥትና የዓለም የምግብ ድርጅት ችግሩ በዞኑ በስፋት መኖሩን ተገንዝበው የሕክምና ቁሳቁስና ተጨማሪ አልሚ ምግቦችን በስፋት ቢያቀርቡም፣ ታጣቂዎች ወደ ጤና ተቋማት በመግባት እንደሚዘርፉ አቶ አሰፋ ገልጸዋል፡፡

ችግሩን ለመቅረፍ ከባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት መደረጉን የጠቀሱት የመምርያ ኃላፊው፣ የጤና ተቋማት ከፍተኛ ጥበቃ እንዲደረግላቸው ከመደረጉም በሻገር ሥጋት ባለባቸው የጤና ተቋማት የሚገኙ አልሚ ምግቦችን ወደ አንድ ማዕከል በማሰባሰብ ለተረጂ ሕፃናት እንዲከፋፈል ለማድረግ እየተሠራ ነው ብለዋል፡፡

ከዚህ ባሻገር በአልሚ ምግቦች ስርቆት የተሰማሩ ገበያ አውጥተው ሲሸጡ የተገኙ ከጤና ባለሙያዎች እስከ ምክትል መምርያ ኃላፊ ድረስ፣ ቅጣት ተላልፎባቸው ማረሚያ ቤት እንዲገቡ መደረጉንም አክለዋል፡፡

‹‹ሌሎች በዚህ ወንጀል ተሳታፊ ሆነው የተገኙ ግለሰቦችም እስከ ሁለት ዓመታት እስራት ተፈርዶባቸዋል፤›› ሲሉ አቶ አሰፋ ተናግረዋል፡፡

በዞኑ ለተከሰተው የኮሌራ ወረርሽኝና የምግብ እጥረት የአማራ ክልል እያደረገ ያለውን የምግብ የመድኃኒት አቅርቦት በተመለከተ መረጃ ለማግኘት ሪፖርተር በተደጋጋሚ ጥረት ቢያደርግም፣ የክልሉ አደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና፣ እንዲሁም የጤና ቢሮ ኃላፊዎች ስልክ ባለመመለሳቸው ምክንያት መነሻቸውን ማካተት አልተቻለም፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የመጣንበትና አብረን የምንዘልቅበት የጋራ እሴታችን ለመሆኑ ነጋሪ ያስፈልጋል ወይ?

በኑረዲን አብራር በአገራችን ለለውጥ የተደረጉ ትግሎች ከመብዛታቸው የተነሳ ሰላም የነበረበት...

አልባሌ ልሂቃንና ፖለቲከኞች

በበቀለ ሹሜ በ2016 ዓ.ም. ኅዳር ማክተሚያ ላይ ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ...

አሜሪካ የኢትዮጵያ የባህር በር ጥያቄ ተገቢነት ቢኖረውም ከጎረቤት አገሮች ጋር በሚደረግ ንግግር መሆን አለበት አለች

መንግሥትን ከፋኖና ከኦነግ ሸኔ ጋር ለማነጋገር ፍላጎቷን ገልጻለች የኢትዮጵያ የባህር...