Friday, March 1, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ዜናበአገራዊ ምክክሩ የተጎጂነትና የተበዳይነት ስሜቶች ከፋፋይ እንዳይሆኑ ጥንቃቄ እንዲደረግ ማሳሰቢያ ተሰጠ

በአገራዊ ምክክሩ የተጎጂነትና የተበዳይነት ስሜቶች ከፋፋይ እንዳይሆኑ ጥንቃቄ እንዲደረግ ማሳሰቢያ ተሰጠ

ቀን:

የአገራዊ ምክክር ኮሚሽን በጀመረው የምክክር ሒደት ወቅት ሊነሱ የሚችሉ የተጎጂነትና ተበዳይነት ስሜቶች፣ የበለጠ ከፋፋይ እንዳይሆኑ ጥንቃቄ እንዲደረግ ማሳሰቢያ ቀረበ፡፡

የኢትዮጵያ ሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ምክር ቤት ከደኅንነት ጥናት ኢንስቲትዩት (Institute for Security Studies) በጋራ በመተባበር አገራዊ ምክክርን ለተቀናጀ፣ አካታችነትን ላረጋገጠና ትርጉም ያለው ተሳትፎ ለማሳደግ በሚል መሪ ቃል ማክሰኞ ኅዳር 11 ቀን 2016 ዓ.ም. ምክክር አካሂደው ነበር።

በመድረኩ ከሲቪል ማኅበረሰብ ዘርፍ፣ የመንግሥት አካላት፣ የፖለቲካ ፓርቲዎችና ምሁራን ሲሳተፉ የተጀመረው አገራዊ ምክክር አካታች፣ አሳታፊና መተማመን የሚፈጠርበት ሒደት እንዲሆን ተሳታፊዎች ጠይቀዋል፡፡

- Advertisement -

Video from Enat Bank Youtube Channel.

የፖለቲካ ሳይንስ ባለሙያው ሰሚር የሱፍ (ዶ/ር)፣ ‹‹ተጎጂነትና ተበዳይነት የምንከፋፈልበት አጀንዳ ሳይሆን፣ በጋራ ወንድማማችነት አብሮ ለመቆም የሚያስችል የአብሮነት መሣሪያ›› ሊሆን እንደሚገባ አስረድተዋል፡፡

በመሆኑም በምክክር ሒደት አንዱ ተበዳይ ሌላው በዳይ ሆኖ መቆም መወቃቀስን እንደሚያስከትል፣ ይህ መወቃቀስ ደግሞ ወደ መከፈፋል የሚያመራ አደገኛ መንገድ ሊሆን ስለሚችል ሁሉም እንደ ተጎጂ ከመናገር ይልቅ፣ እንደ በዳይና ተበዳይ በጋራ በመቆም የተደላደለ የወንድማማችነት መንገድ የሚያቀላጥፍ ምክክር መደረግ አለበት ብለዋል፡፡

የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ መምህሩ ገብሬ ይንጢሶ (ዶ/ር) በበኩላቸው የተጎጂነት ስሜት በምክክር ሒደቱ የተሻለ መግባባት ለመፍጠር እንጂ፣ ወደ ባሰ መከፋፋል የሚያመራ መሆን የለበትም የሚል ማሳሰቢያ ሰጥተዋል፡፡ በመሆኑም የምክክር ሒደት የተራራቁ የሚመስሉ ዕሳቤዎችንና አካላትን የበለጠ ወደ አንድ የማምጣት ዕድል ሊፈጥር ይገባል ብለዋል፡፡

የምክክር ሒደቱ ልዩነትን በሚያጎላ መንገድ ሳይሆን በማጥበብ ተጎጂ ነኝ የሚለውን በዳይ ከተባለው አካል ጋር የበለጠ ሊያቀራርብ የሚችል መሆን እንዳለበት ጠቅሰው፣ ብሶትን የበለጠ የሚያጎላ እንዳይሆን አሳስበዋል፡፡

ለዚህም ይረዳ ዘንድ የምክከሩ ሒደት በጋራ እሴቶች ላይ ያተኮረ፣ ከልዩነት ይልቅ አንድነትና መተሳሰብን መሠረት ያደረገ አካታችና አሳታፊ ውይይት ማድረግ ላይ ያተኮረ እንዲሆን ጠይቀዋል፡፡

ገብሬ (ዶ/ር) የምክክር ሒደቱ አሳታፊነትን በተመለከተ ሲያብራሩ የፌዴሬሽን ምክር ቤት አባል ብሔረሰቦች 76 መሆናቸውን፣ ነገር ግን ያልተቆጠሩ ወይም በምክር ቤቱ ዕውቅና ያልተሰጣቸው በርካቶች በመሆናቸው በቀጣይ ወጥነት ባለው መንገድ የጋራ ስምምነት ላይ መድረስ አስፈላጊ ነው ብለዋል፡፡ የምክር ቤቱ አባል ያልሆኑትንም ድምፃቸው በተገቢው ሁኔታ የሚደመጥበት አሠራር መፍጠር አስፈላጊነትንም ጠቁመዋል፡፡

የሃይማኖት ተቋማት እኩል ተሳትፎን በተመለከተ የመነሻ ጽሑፍ ያቀረቡት የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ መምህሩ ተካልኝ ነጋ (ዶ/ር)፣የምክክር ኮሚሽኑ የሃይማኖት ተቋማትን ለማሳተፍ ወደ ሃይማኖት ተቋማት ጉባዔ ቢያመራ የኮሚሽኑ አካታችነትና አሳታፊነት የሚለካው የጉባዔው አባል የሆኑ ሰባት የሃይማኖት ተቋማትን እንጂ፣ ኢትዮጵያ ውስጥ አሉ የሚባሉ ህዳጣንና ባህላዊ ሃይማኖቶችን ያላካተተ እንደሚሆን ተናግረዋል፡፡

በተጨማሪም የጉባዔው ዓላማ አባላቱን ብቻ መሠረት ያደረገ ከመሆኑም በላይ፣ ለመንግሥት ቅርብ የሆነ ተቋም በመሆኑ የእምነት ተቋማቱን ቁርጥ ቁመና ወካይ የመሆኑ ጉዳይ አጠራጣሪ ስለመሆኑ ገልጸዋል፡፡

የማኅበራዊ አንትሮሎጂ ባለሙያው አሉላ ፓንክረስት (ዶ/ር) በምክክር ሒደቱ አካታችና አሳታፊነት በተመለከተ መደረግ ያለበትን ቅድመ ጥንቃቄ ሲያብራሩ፣ በምክክሩ ለይስሙላ አሳተፍኩ ለማለት በኮታ ድልድል ሳይሆን ትኩረት ተሰጥቶት የጉዳዩ ባለቤቶች የሚሳተፉበት መንገድ ሊፈጠር እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡

የአገራዊ ምክከር ኮሚሽነሩ አቶ መላኩ ወልደ ማርያም በአገራዊ ምክክር ሒደቱ፣ ‹‹ሰው ሆነን እንነጋገር፣ ደም ከሚያፈስ አዙሪት እንውጣ፣ ለዚህ ደግሞ ቁጭ ብሎ መነጋገርና መመካከር እንጂ ሌላ አማራጭ የለም፤›› ብለዋል፡፡

የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን የሴቶች ሕፃናት፣ አረጋዊያንና አካል ጉዳተኞች መብቶች ኮሚሽነር ርግበ ገብረ ኃዋሪያ በበኩላቸው፣ ከ17 በመቶ በላይ ኢትዮጵያውን አካል ጉዳተኛ መሆናቸውን ጠቅሰው ለአካል ጉዳተኞች የሚሰጠው ትኩረት ከሌላው ማኅበረሰብ እኩል እንዲሆን ጠይቀዋል፡፡ ይሁን እንጂ ለአካል ጉዳተኞች የሚደረጉ ትኩረቶችን አንደ ችሮታ በመቁጠር ወይም ግለሰቦቹ ሕመም ላይ እንዳሉ አድርጎ ማሰብ አግላይ መሆኑን አስረድተዋል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

[ክቡር ሚኒስትሩ ወደ መኖሪያ ቤታቸው ሲገቡ ባለቤታቸው በቴሌቪዥን የሚተላለፈውን ዜና በመደነቅ እየተመለከቱ አገኟቸው]

እንዲያው የሚደንቅ ነው እኮ። ምኑ? ዜና ተብሎ በቴሌቪዥን የሚተላለፈው ነገር ነዋ፡፡ ምኑ...

በኦሮሚያ የሚፈጸሙ ግድያዎችና የተጠያቂነት መጥፋት

የካቲት 11 ቀን 2016 ዓ.ም. ቢሾፍቱ አቅራቢያ በሚገኘው የዝቋላ...

የኢትዮጵያ መዋዕለ ንዋይ ገበያ ከሚያስፈልገው ካፒታል ውስጥ 90 በመቶውን ሰበሰበ

እስካሁን 15 ባንኮች የመዋዕለ ንዋይ ገበያው ባለድርሻ ሆነዋል የኢትዮጵያ መዋዕለ...

አዲሱ የንብ ባንክ ቦርድ የባንኩን ካፒታል በአሥር ቢሊዮን ብር ለማሳደግ ማቀዱ ተሰማ

አዲሱ የንብ ኢንተርናሽናል ባንክ የዳይሬክተሮች ቦርድ የባንኩን ካፒታል በአሥር...