ከኒው ዮርክ ተነስቶ ወደ ቤልጂየም በመብረር ላይ የነበረ ቦይንግ 747 ዕቃ ጫኝ አውሮፕላን፣ አሳፍሮት የነበረው ፈረስ ከነበረበት የፈረስ ማጎሪያ ሳጥን በመውጣቱ፣ አውሮፕላኑ ወደ ኒውዮርክ እንዲመለስ መገደዱን ስካይ ኒውስ ዘግቧል፡፡
አውሮፕላኑ ወደ ቦስተን ፊቱን እንዲያዞር ከመገደዱ በፊት 31000 ጫማ ከፍታ ላይ ነበር፡፡ አውሮፕላኑ ወደ ኒውዮርክ ተመልሶ ለማረፍ የነበረው ክብደት ለማረፍ ከሚያስፈልገው ገደብ በላይ ስለነበር ለደኅንነቱ ሲባል 20 ቶን ነዳጅ ወደ አትላንቲክ ማፍሰሱንም ስካይ ኒውስ አሥፍሯል፡፡