Sunday, December 10, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ዝንቅምነው ወላዲተ አምላክ…

ምነው ወላዲተ አምላክ…

ቀን:

እኔ አንድ ትቢያ፣ ሃጥያተኛ

የጊዜ ቀበኛ

አንቺን ደፍሮ ለመጠይቅ

ያላሟላሁ የመንፈስ ስንቅ

ዛሬ ደፍሬ ልጠይቅሽ

ምነው፣ ምነው ልበልሽ

እንቺ እመብርሃን፣ ተረሳሽ ወይ ርስትሽ????

የቃል ኪዳን ምድርሽ?

ምነው ጨከንሽ?

ምነው ባክሽ?

አይበቃም ወይ፣ ዋይታ

የሕፃናት ጩኸት፣ የእናቶች ኡኡታ

ደም እንደጎርፍ ሲወርድ…

በዱር በገደሉ ሰው ሲታረድ!!

ምነው ድንግል ማርያም፣ አስቻለሽ?

ተማለጂን ቶሎ ድረሽ

ሃምሳ ዓመታት ሙሉ ተሞከረ

ተማርን ባዩ ፎከረ

አንዱ አክራሪ

ሌላው አድሃሪ

ተባብሎ ዘመረ፣ አዘመረ

ጎራ ከፍሎ ቀይ በነጭ፣ ሬሳ ከመረ

የፈጣሪን አምሳል የሰው ልጅን

በዘር፣ በቋንቋ ለይቶ በመሸንሸን

ፈጀ፣ አፋጀን!!!

በቃ በይን፣ እንቺ እመብርሃን

ከልጅሽ አማልጅን

አትጨክኚ ተለመኝን!!

ቅድስት አገር ረከሰች

የሰው ደም ለሳጥናኤል ገበረች

የታቦተ ፅዮን፣ የግማደ መስቀሉ ማረፊያ

ነደደች በሰይጣን ቋያ

አገረ ኢትዮጵያ  

ሆነች የሰው ልጆች ማሰቃያ

ደጀ ሰላም፣ ተደፈረ

በመናፍቅ ተወረረ

ሕዝበ ክርስቲያን አፈረ

ተለመኚን እመብርሃን

ስጭን ፍርዱን

አብርጂ እሳቱን

በምድረ ኢትዮጵያ የነደደን

የሰው መንገድ ስላልበጀን

እባክሽን ስሚን

ከልጅሽ ይቅርታን ጠይቂልን!!!

የሳጥናኤል ፈረስ ጋላቢዎች

የዘመኑ ጉድ፣ ማንጉዶች

አታላይ፣ ወስላቶች

በልጅሽ ስም ነጋዴዎች

ሕዝቡን አባልተው ሳይጨርሱት

አሟጠው ሳይቀብሩት

አገሩን አፅጅለት

ከእትብት አልባ የጅብ ጅቦች

ሂትለሮ – ናዚያዊ ዘረኞች!!

እመብርሃን ለዚህ ሕዝብ ድረሽለት!!!

ክብሩን መልሽለት!!!

ፀሎቱን በሰላም ያድርስበት!!

አሃዱ ይበልበት!!!

አርሶ አምርቶ ይብላበት

መምህር ያስተሞር፣ ተማሪ ያጥናበት

ነጋደው ይነግድ፣ ጥሮ አዳሪው ይሩጥበት

እስላም ክርስቲያኑ በፍቅር ይኑርበት!!!

ለዘረኞቹ የሳጥናኤል ምርኮኞች

የዘመኑ ተረኞች

ለአፍሪካ አንድነት ፀሮች

ለአፍሪካ ሰላም አስጊዎች

አደራ በሊታዎች

ታላቅ፣ ታናሽ አዋራጆች

ምሕረቱን ላኪላቸው

ሰው መሆን ቢገባቸው!!

ወይም ቶሎ ውስዷቸው

ከዘላለም ቦታቸው

ትንታግ እሳት ከሞላበት

ማሩኝ ቢሉ ሰሚ ከሌለበት

ከሰማዩ ቦታ

ከሌለበት ፋታ

ገብተው ይለብለቡ ቀን ከለሊት

እየሰሙ የሳጥናኤልን ድምፅ

ከፊታቸው እየፎከረ በግልፅ!!

ያጠፉት ነፍስ ከገነቱ ሲለመልም 

ያ-የፈጁት በገሃዱ ዓለም

ሲያመሠገን ሲዘመር

እግዚአብሔር ሲከበር

ዘረኞቹ እንዲኖሩ እንዳረሩ

ውሰዷቸው ከሳይጥናኤል ከመንደሩ!!!!

እየካደሙ እንዲኖሩ!!

(ተመባ ጥቅምት 24 ቀን 2016 ዓ.ም. ሌሊት፣ ከሜዲትራንያን ባህረ ሰማይ፣ ተስፋዬ መኮንን (ዶ/ር)

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ለሰው ልጅ መብት መከበር ስናወራ 75 ዓመት ሞላን!

በገነት ዓለሙ ዓለም ስለሰብዓዊ መብቶች ሲያወራ፣ ሲምል፣ ሲገዘት፣ ሲፈጠም፣ ቃል...

ካልተማከለ የካፒታል ገበያ ወደ ዘመናዊና የተደራጀ የሰነደ ሙዓለ ንዋዮች ገበያ

በእሱፈቃድ ተረፈ በአገራችን የካፒታል ገበያ አዋጅ መውጣትን ተከትሎ የተማከለ የሰነደ...

ለማይቀረው ምክክርና ድርድር እንዘጋጅ

በያሲን ባህሩ  የዘመናዊት ኢትዮጵያ ፖለቲካ ውዝግብ በትንሹ የአንድ ምዕተ ዓመት...

ደንብ አስከባሪዎች ደንብ ያክብሩ!

በአዲስ አበባ ከተማ ደንብ አስከባሪዎች፣ ሌሎች የፀጥታ አካላት፣ እንዲሁም...