የጃፓንና የኢትዮጵያ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት የተጀመረው እ.ኤ.አ. በ1930 ነው፡፡ ወቅቱ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ውስጥ የሚገኘው የቀድሞ ገነተ ልዑል ቤተ መንግሥት (ራስ መኮንን አዳራሽ) ተገንብቶ የተጠናቀቀበት በመሆኑም፣ ሁለቱ አገሮች ግንኙነታቸውን በፊርማ ያፀደቁት በራስ መኮንን አዳራሽ ነው፡፡ ጃፓን ይህንን ታሳቢ በማድረግ የጃፓን ቀን ፌስቲቫሏን በኅዳር 1 ቀን 2016 ዓ.ም. በአዲስ አበባ ዩኒቪርሲቲ የኢትዮጵያ ጥናትና ምርምር ተቋም ራስ መኮንን አዳራሽ አክብራለች፡፡