Sunday, December 10, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ስፖርትፌዴሬሽን ምሥረታ ሒደት ላይ የሚገኘው የኢትዮጵያ ግሎባል ቴኳንዶ

ፌዴሬሽን ምሥረታ ሒደት ላይ የሚገኘው የኢትዮጵያ ግሎባል ቴኳንዶ

ቀን:

በኢትዮጵያ በፌዴሬሽን ደረጃ ተቋቁመው ከሚከናወኑ ስፖርቶች በዘለለ፣ በማኅበር ተዋቅረው በክልልም ሆነ በከተማ አስተዳደሮች የሚከናወኑ በርካታ ስፖርቶች ይገኛሉ፡፡ ስፖርቶች በሥራቸው በርካታ ክለቦችን አቅፈው የሚተገብሩ ሲሆን፣ በአገር ውስጥ ውድድሮች ላይ ተሳትፎ ያደረጋሉ፡፡

በቅርቡ በማኅበር ተደራጅቶ እየተከናወነ የሰነበተው የኢትዮጵያ ግሎባል ቴኳንዶ ወደ ፌዴሬሽን ለማደግ የመጨረሻ ምዕራፍ ላይ መድረሱ ተጠቁሟል፡፡

ግሎባል ቴኳንዶ ከሌሎች የአርት ስፖርቶች በተለየ ሁኔታ ሴቶችን በብዛት በማሳተፍ ይታወቃል፡፡ በእያንዳንዱ ውድድር ላይ ሴቶችን በማሳተፍ ይታወቃል፡፡ በዚህም መሠረት የግሎባል ቴኳንዶ ውድድርን ለማከናወን የግድ ሴቶችን ማካተት ያስፈልጋል፡፡

ግሎባል ቴኳንዶ በደቡብ ኮሪያው ‹‹ማስተር ፓርክ ጁንግ ቴይ›› ዕውቅና ማግኘቱ ይነገራል፡፡ በዓለም ላይ በ33 አገሮች የሚዘወተር ሲሆን፣ በኢትዮጵያ ስምንት ክልሎች ላይ እንቅስቃሴ አለው፡፡ በአዲስ አበባ በማኅበር (Association) ተደራጅቶ የሚንቀሳቀስ ሲሆን በስምንት ክልሎች በፌዴሬሽን ደረጃ ተዋቅሮ ይገኛል፡፡

በኢትዮጵያ በፌዴሬሽን ደረጃ ለመቋቋም የመጨረሻ ምዕራፍ ላይ የሚገኘው ግሎባል ቴኳንዶ ምሥረታውን ለማከናወንና ክልሎችን ለማደራጀት ከባህልና ስፖርት ሚኒስቴር ፈቃድ ማግኘቱን የኢትዮጵያ የግሎባል ቴኳንዶ መሥራች ኢንስትራክተር ሳቦም መሐመድ መኪ ለሪፖርተር አስረድተዋል፡፡

በኢትዮጵያ መተግበር ከጀመረ ሦስት ዓመታትን የተሻገረው ግሎባል ቴኳንዶ፣ በክልሎች ላይ እንቅስቃሴ ለማድረግ ፈቃድ ካገኙ ሰባት ወራት ማስቆጠራቸው ተገልጿል፡፡

‹‹ፈቃዱን ለማግኘት በአገር ውስጥና ከአገር ውጭ በነበሩ ባለሙያዎች ጥናት አስጠንተን ነበር፡፡ ስፖርቱ ከሌሎች የአርት ስፖርቶች ልዩ መሆኑን ከተማመንን በኋላ ፈቃድ ልናገኝ ችለናል፤›› በማለት ሳቦም መሐመድ ያስረዳል፡፡

ግሎባል ቴኳንዶ፣ ኢንተርናሽናል ቴኳንዶ፣ እንዲሁም ከሌሎቹ ማርሻል አርቶች የሚለይበትን ጉዳይ በተመለከተ ጥናት የተደረገበት መሆኑን የሚያነሱት ሳቦም መሐመድ፣ ግሎባል ቴኳንዶ ከምሥረታው ጀምሮ የተለዩ ባህሪያት እንዳሉት ያብራራሉ፡፡

በዚህም መሠረት ግሎባል ቴኳንዶ 30 ዓይነት አርት ያለው ሲሆን፣ በአለባበስ፣ በሎጎ፣ በቀበቶ፣ በውድድር፣ በሕግ፣ እንዲሁም በመወዳደሪያ ሜዳው እንደሚለይ ይጠቅሳሉ፡፡

ከዚህም ባሻገር ግሎባል ቴኳንዶ በዓለም አቀፍ ደረጃ 1990 ዓ.ም. የተመሠረተ ሲሆን፣ ኢንተርናሽናል ቴኳንዶ 1966 ዓ.ም.  ነው የተመሠረተው፡፡ ግሎባል ቴኳንዶ ወደ ኢትዮጵያ ዘግይቶ ቢገባም፣ ባለሙያው ዓለም አቀፍ ሕጎችን አጢኖና መሠረታዊ ልዩነቱን ካሳወቀ በኋላ ወደ ምሥረታው መግባቱን ያብራራሉ፡፡

በኢትዮጵያ በግሎባል ቴኳንዶ ሥር የሚተዳደሩ ከ80 በላይ ክለቦች ሲኖሩ፣ ከ2,000 በላይ አባላት እንዲሁም ተከታዮች አሉት፡፡

ግሎባል ቴኳንዶ ለአባላቱ የዳኝነት ሥልጠና ሲሰጥ መቆየቱን የሚያነሱት ሳቦም፣  በቅርቡ በአዲስ አበባ ውድድር ለማሰናዳት ውጥን እንዳላቸው ጠቁመዋል፡፡

በቅርቡ ወደ ፌዴሬሽን እንደሚያድግ የሚጠበቀው ግሎባል ቴኳንዶ፣ ከዓለም አቀፉ የግሎባል ቴኳንዶ ፌዴሬሽን ጋር ጥብቅ ግንኙነት እንዳለው የተነሳ ሲሆን፣ ሳቦም በቅርቡ ወደ ኢትዮጰያ መጥተው ሥልጠና እንዲሰጡ ለማድረግ በንግግር ላይ እንደሚገኙ ተገልጿል፡፡

በቅርቡ የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር የስፖርት ማኅበራት ስለሚቋቁሙበት ሁኔታ ለመወሰን በወጣው መመርያ መሠረት ቁጥር 907/2014 አንቀጽ1 (13) መሠረት የኢትዮጵያ ቴኳንዶ ፌዴሬሽን፣ የኢትዮጵያ ኢንተርናሽናል ቴኳንዶ ፌዴሬሽንና የኢትዮጵያ ዩናይትድ ፌዴሬሽን ስፖርቶች በክልልና በከተማ አስተዳደር ተስፋፍተው ተግባራዊ እየሆኑ እንደሚገኙ ተጠቅሶ ነበር፡፡

በአንፃሩ የግሎባል ቴኳንዶ ፌዴሬሽን አደረጃጀትን በተመለከተ የስፖርት ማኅበሩ መመርያ ቁጥር 907/2014 አንቀጽ 7 ከተራ ቁጥር 1 እስከ 6 ያሉትን መሥፈርቶች አሟልቶ በስፖርት ማኅበር ስም የአገር አቀፍ ዕውቅና አግኝቶ እንዲመዘገብና እንዲቋቋም ለማድረግ ክልሎችና ከተማ አስተደደሮች ትብበር እንዲያደርጉ ጥሪ መቅረቡ ይታወሳል፡፡

ፌዴሬሽን ተቋቁሞ ሠርተፍኬት ለማግኘት የመጨረሻ ምዕራፍ ላይ የሚገኘው ግሎባል ቴኳንዶ በቅርቡ ጉባዔ አድርጎ ሕጋዊ የፌዴሬሽን እንደሚሆን ይጠበቃል፡፡.

እንደ ሳቦም አስተያየት ከሆነ የፌዴሬሽን ምሥረታውን ለማከናወን የሚያስፈለጉ ሒደቶች ከተጠናቀቁ በኋላ ግን የተወሰኑ ቅሬታዎች መነሳታቸውን አንስቷል፡፡ ይህም በስፖርቱ ላይ የሚገኙ አንድ አንድ ባለሙያዎች የተዛባ መረጃ በማኅበራዊ ሚዲያ እያሠራጩ ነው፡፡

‹‹ስፖርቱንና እንዳይዳከምና እንዳይወድቅ የሚሠራውን ወጣት ለማደናቀፍ የሚንቀሳቀሱ ግለሰቦች አሉ፤›› በማለት፣ ሳቦም መሐመድ አስተያየታቸውን ይሰጣሉ፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ለሰው ልጅ መብት መከበር ስናወራ 75 ዓመት ሞላን!

በገነት ዓለሙ ዓለም ስለሰብዓዊ መብቶች ሲያወራ፣ ሲምል፣ ሲገዘት፣ ሲፈጠም፣ ቃል...

ካልተማከለ የካፒታል ገበያ ወደ ዘመናዊና የተደራጀ የሰነደ ሙዓለ ንዋዮች ገበያ

በእሱፈቃድ ተረፈ በአገራችን የካፒታል ገበያ አዋጅ መውጣትን ተከትሎ የተማከለ የሰነደ...

ለማይቀረው ምክክርና ድርድር እንዘጋጅ

በያሲን ባህሩ  የዘመናዊት ኢትዮጵያ ፖለቲካ ውዝግብ በትንሹ የአንድ ምዕተ ዓመት...

ደንብ አስከባሪዎች ደንብ ያክብሩ!

በአዲስ አበባ ከተማ ደንብ አስከባሪዎች፣ ሌሎች የፀጥታ አካላት፣ እንዲሁም...