Friday, June 14, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -

ኪንና ባህልየጃፓን ቀን ፌስቲቫል በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ

የጃፓን ቀን ፌስቲቫል በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ

ቀን:

በዳንኤል ንጉሤ

የአካዳሚክ፣ ውይይቶች፣ የባህል ዝግጅቶች በሚካሄዱበትና የሙዚየም ማዕከል ሆኖ በሚያገለግለው በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ራስ መኮንን አዳራሽ (ገነተ ልዑል ቤተ መንግሥት) በኢትዮጵያ የጃፓን ኤምባሲ፣ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲና የጃፓን ዓለም አቀፍ ትብብር ኤጀንሲ (ጃይካ) በጋራ ያዘጋጁት ዓመታዊ የጃፓን ቀን ፌስቲቫል ቅዳሜ ኅዳር 1 ቀን 2016 ዓ.ም. ተከብሯል፡፡

የጃፓናውያንን ባህል ለኢትዮጵያውያን ለማስተዋወቅ ባቀደው ፌስቲቫል ፊልሞች፣ ባህላዊ የዘፈን ትርዒቶች፣ የማርሻል አርት (ጁዶ) ትርዒት፣ ባህላዊ ምግብና  የጃፓን ጨዋታዎችን ጨምሮ የተለያዩ የባህል ክዋኔዎች የታዩበት ነበር፡፡

- Advertisement -

በፌስቲቫሉ ታዋቂው የሞሶብ የባህል ሙዚቃ ቡድን የኢትዮጵያን ባህላዊ ሙዚቃዎች  አሳይቷል። ዝግጅቱ እ.ኤ.አ. በ1882 በጃፓን መምህር ካኖ ጂጎሮ የተመሠረተው የማርሻል አርት የጁዶ ትርዒትን ያካተተ ነበር። በኢትዮጵያ ጁዶ ፌዴሬሽን የተመዘገበው የአዲስ አበባ ጁዶ ማኅበር የበዓሉ መርሐ ግብር አካል በመሆን ትርዒቱን አቅርቧል።

በጃፓን ቀን ፌስቲቫል ከተከናወኑ ዋና ዋና ተግባራት መካከል አንዱ የጃፓን ባህላዊ ምግብን የማጣጣም ነው። ሱሺ፣ ቴምፑራ፣ ራመንና ማቻ የተሰኙትን ምግቦችና ባህላዊ የሻይ አፈላላቸውን ጨምሮ የተለያዩ የጃፓናውያን ምግቦች ለተሳታፊዎች የቀረቡ ሲሆን፣ ተሳታፊዎችም የጃፓን ጣዕሞችንና የምግብ አሠራር ወጎችን እንዲያዩ አስችሏል።

በኢትዮጵያ የጃፓን አምባሳደር ኢቶ ታካኮ፣ የጃፓን ቀን ፌስቲቫል በጃፓንና በኢትዮጵያ መካከል ያለውን ግንኙነትና ጉልህ ክንውኖችን ለማስታወስ እንደ መድረክ ሆኖ ያገለግላል ብለዋል።

አንባሳደር ኢቶ ለሪፖርተር እንደገለጹት፣ የጃፓን ቀን ፌስቲቫል የጃፓንና ኢትዮጵያ የሁለትዮሽ ግንኙነታቸውን ለማጠናከር ያላቸውን ቁርጠኝነት እንደ ማሳያ ሆኖ ያገለግላል፡፡ በሁለቱ አገሮች መካከል የባህል ልውውጥና የጋራ መግባባት መድረክን ያጠናክራል።

በፌስቲቫሉ የተገኙ ታዳሚዎች በጃፓንና በኢትዮጵያ መካከል ስላለው የጋራ ዕሴትና ወጎች ጥልቅ ዕውቀት እንዲኖራቸው ዕድል እንደሚሰጥም አክለዋል፡፡

በሁለቱ አገሮች መካከል ያለውን ግንኙነት የበለጠ ለማጠናከር የልምድ ልውውጦችን፣ የአካዳሚክ ፕሮግራሞችንና የጋራ የምርምር ውጥኖችን ጨምሮ ትብብር እንደሚኖር፣ ፌስቲቫሉ ለወደፊት የሁለትዮሽ ግንኙነትና ለቀጣይ የባህል ግንኙነት እንደሚያገለግልም በመድረኩ ተገልጿል።

አምባሳደር ኢቶ ‹‹ይህ ዓመታዊ ዝግጅት የጃፓንን ባህል ለማሳየት፣ የጋራ መግባባትን ለማጎልበትና በሁለቱ አገሮች መካከል ያለውን ትብብር ለማሳደግ እንደ መድረክ ያገለግላል፤›› ብለዋል።

ፌስቲቫሉ የጃፓንና የኢትዮጵያን የጋራ እሴቶችና ወጎች አጉልቶ እንደሚያሳይም ተናግረዋል፡፡

የባህልና ስፖርት ሚኒስትር ዴኤታ ወ/ሮ ወርቅነሽ ብሩ በበኩላቸው፣ በኢትዮጵያና በጃፓን መካከል ያለው ግንኙነት ትልቅ ጠቀሜታ እንዳለው ገልጸው፣ ጃፓን  ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት በኋላ ከድህነት ወደ በለፀገች አገር የመቀየሯ ትልቁ ምክንያት ባህላዊ ማንነቷን ዕውቅና ሰጥታ ስለሠራች መሆኑንና ኢትዮጵያውያንም ከዚህ ትምህርት በመውሰድ ልትማርበት እንደሚገባ ተናግረዋል፡፡

ከጃፓን ልምድ መማርና በሁለቱ አገሮች መካከል የባህል ልውውጥን ማጎልበት አስፈላጊ መሆኑን፣ በሁለቱ አገሮች መካከል ያለውን የባህል ግንኙነት የበለጠ ለማሳደግ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ጋር ያለው ትብብርም በዘላቂነት እንደሚቀጥል ጠቅሰዋል፡፡

ፌስቲቫሉ የተዘጋጀው በኢትዮጵያና በጃፓን ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት የተጀመረበትን 93ኛ ዓመት፣ ጃይካ በኢትዮጵያ ቢሮ ሙሉ ሥራ የጀመረበትን 30ኛ ዓመትና የጃፓን በጎ ፈቃደኞች ወደ ሌሎች አገሮች ሄደው መሥራት የጀመሩትን 50ኛ ዓመት ማክበርን ታሳቢ ተደርጎም ነው፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

[ክቡር ሚኒስትሩ በመንግሥት የሚታወጁ ንቅናቄዎችን በተመለከተ ባለቤታቸው ለሚያነሱት ጥያቄ ምላሽ ለመስጠት እየሞከሩ ነው]

እኔ ምልህ? እ... ዛሬ ደግሞ ምን ልትይ ነው? ንቅናቄዎችን አላበዙባችሁም? የምን ንቅናቄ? በመንግሥት...

የመንግሥት የ2017 ዓ.ም በጀትና የሚነሱ ጥያቄዎች

የ2017 ዓመት የመንግሥት ረቂቅ በጀት ባለፈው ሳምንት መገባደጃ ለሚኒስትሮች...

ከፖለቲካ አባልነትና ከባንክ ድርሻ ነፃ የሆኑ ቦርድ ዳይሬክተሮችን ያካተተው ብሔራዊ ባንክ ያዘጋጃቸው ረቂቅ አዋጅና መመርያዎች

የኢትዮጵያ የብሔራዊ ባንክ የፋይናንስ ተቋማትን የተመለከቱት ድንጋጌዎችንና የባንክ ማቋቋሚያ...

የልምድ ልውውጥ!

እነሆ መንገድ ከቦሌ ሜክሲኮ። አንዱ እኮ ነው፣ ‹‹እንደ ሰሞኑ...