Monday, December 11, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊበብሔራዊ ፈተና ከወደቁ ተማሪዎች አገር ቀያሪ ሐሳብ ያላቸው በርካታ ልጆች እንደሚኖሩ ተገለጸ

በብሔራዊ ፈተና ከወደቁ ተማሪዎች አገር ቀያሪ ሐሳብ ያላቸው በርካታ ልጆች እንደሚኖሩ ተገለጸ

ቀን:

የአሥራ ሁለተኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ወስደው የወደቁ ልጆች ወድቀው ቀሩ ማለት እንዳልሆነና ከወደቁት ውስጥ አገር ቀያሪ ሐሳብ ያላቸው በርካታ ተማሪዎች እንደሚኖሩ ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) ተናገሩ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህንን የገለጹት፣ ስድስተኛው የኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሦስተኛ ዓመት የሥራ ዘመን አራተኛ መደበኛ ስብሰባውን ማክሰኞ ኅዳር 4 ቀን 2016 ዓ.ም. ባካሄደበት ወቅት ነው፡፡

በብሔራዊ ፈተና ከወደቁ ተማሪዎች አገር ቀያሪ ሐሳብ ያላቸው በርካታ ልጆች እንደሚኖሩ ተገለጸ | Ethiopian Reporter | ሪፖርተር
ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር)

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከአባላት ከተነሱላቸው ጥያቄዎች መካከል ከ12ኛ ክፍል ፈተና ውጤት ጋር በተያያዘ ማብራሪያ ሲሰጡ እንደገለጹት፣ በትምህርት ሥርዓቱ ውስጥ ያለውን ስብራት ማስተካከል ካልተቻለ ልጆች በሕይወት ፈተና ይወድቃሉ፡፡

‹‹ባለፉት ዓመታት የትምህርት ሥርዓት መውደቅ ኢትዮጵያን እየጎዳ ነው ብለን ከለውጡ በፊትና ለውጥ ከጀመርንበት ጊዜ ጀምሮ አጀንዳችን ነው፤›› ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ በሥርዓተ ትምህርቱ ማሻሻያ ከተደረገባቸው ነጥቦች ውስጥ አንዱ የፈተና መስጫ መገንገድን መቀየር መሆኑን ገልጸዋል፡፡

በዚህ መሠረት ዘንድሮ የተመዘገበው አነስተኛ ውጤት የተጠበቀ እንደሆነ፣ ሆኖም ከአሥራ ሁለተኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና የወደቁ የተለያዩ ክህሎት ያላቸው በርካታ ተማሪዎች እንዳሉ፣ እነዚህም በቴክኒክና ሙያ ትምህርት ቤቶች የመማር አማራጭ እንዳላቸው ተናግረዋል፡፡

የፈተና ኩረጃና ስርቆት እየተለመደ በመምጣቱ በተማሪዎች ዘንድ የመማር፣ የመመራመርና፣ ተግቶ የማንበብ ፍላጎት እንደቀነሰ የትምህርት ምዘና ጥናቶች እንደሚያመላክቱ፣ ይህም በትምህርት ሥርዓቱ ውስጥ ልህቀትን እያቀጨጨው ከመምጣቱ በተጨማሪ የትምህርት ፍትሐዊነትን እንደጎዳው ተናግረዋል፡፡

መንግሥት ችግሩን በመገንዘብ በዘላቂነት ለመፍታት በርካታ የሪፎርም ሥራዎችን እየሠራ እንደሆነ፣ የፈተና አስተዳደር ሥርዓትን በተለይም የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ማጠናቀቂያ ፈተና በሒደት እያጋጠመው የመጣውን ችግር ለመቅረፍ በትኩረት ሲሠራ መቆየቱን ተናግረዋል፡፡

የትምህርት ፖሊሲው ከ50 በመቶ በላይ ያመጡ ተማሪዎች በቀጥታ ዩኒቨርሲቲ ገብተው ይማራሉ ቢልም፣ ዓምናም ዘንድሮም እስከ 30 በመቶ ተወርዶ ለበርካቶች የአንድ ዓመት ሥልጠና መሰጠቱን አስታውሰዋል፡፡

‹‹በአዲሱ የትምህርት ፖሊሲ ከተሸሻሉ ነገሮች አንዱ አንድ ተማሪ ማትሪክ ወድቆ በቴክኒክና ሙያ ገብቶ ደረጃ 1፣ 2፣ 3 እና 4 ብሎ ከተመረቀ በኋላ፣ ወደ ቀለም ትምህርት መሄድ ይችላል፣ ዝግ አይደለም፤›› ያሉት ዓብይ (ዶ/ር)፣ በቀለም ትምህርት ለዲግሪ ያመጣ ተማሪ ቀለም ብቻ ሳይሆን በሙያም እሠለጥናለሁ ካለ የሚማርበት አግባብ እንዳለ ገልጸዋል፡፡

በኢትዮጵያ 1,400 የቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ኮሌጆች መኖራቸውን የገለጹት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ በዓመት 600 ሺሕ ተማሪዎቸ ለቴክኒክና ሙያ ሥልጠና የመቀበል አቅም እንዳላቸውም ጠቁመዋል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ለሰው ልጅ መብት መከበር ስናወራ 75 ዓመት ሞላን!

በገነት ዓለሙ ዓለም ስለሰብዓዊ መብቶች ሲያወራ፣ ሲምል፣ ሲገዘት፣ ሲፈጠም፣ ቃል...

ካልተማከለ የካፒታል ገበያ ወደ ዘመናዊና የተደራጀ የሰነደ ሙዓለ ንዋዮች ገበያ

በእሱፈቃድ ተረፈ በአገራችን የካፒታል ገበያ አዋጅ መውጣትን ተከትሎ የተማከለ የሰነደ...

ለማይቀረው ምክክርና ድርድር እንዘጋጅ

በያሲን ባህሩ  የዘመናዊት ኢትዮጵያ ፖለቲካ ውዝግብ በትንሹ የአንድ ምዕተ ዓመት...

ደንብ አስከባሪዎች ደንብ ያክብሩ!

በአዲስ አበባ ከተማ ደንብ አስከባሪዎች፣ ሌሎች የፀጥታ አካላት፣ እንዲሁም...