ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) ማክሰኞ ኅዳር 4 ቀን 2016 ዓ.ም. ከሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት በበርካታ ጉዳዮች ላይ ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች ከሰጡት ምላሽ የተወሰደ፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከክላሽ ይልቅ ብርዕና ሐሳብን በመያዝ ለመወያየት ቅድሚያ መስጠት እንደሚገባ ተናግረው፣ ‹‹በመገዳደል ልናሳካ የምንችለው ዓላማም ሆነ የሚገኝ ትርፍ የለም፡፡
ለኢትዮጵያ የሚበጀውም በውይይት የበለፀገች አገር መገንባት ነው፤›› ብለዋል፡፡ ‹‹… እኛ የየትኛውም ሠፈር ጽንፍ የወጣ ዋልታ ረገጥ ዕሳቤ መጠቀሚያ አይደለንም፣ እኛ የምንከተለው አገራዊ ዕይታ ነው፡፡ ችግሮቻችንን የምንመለከትበት ሁኔታ በስሜትና በሴራ የሚመራ ሊሆን አይገባም፣ የጋራ ግንዛቤ በመያዝ ወደ መፍትሔ መሄድ አለብን፡፡ ኢትዮጵያ የእያንዳንዱ ዜጋ ውጤት ናት፣ በጋራ መኖርና በጋራ መበልፀግም እንችላለን፤›› ሲሉ አስረድተዋል፡፡