የጌዴኦ ማኅበረሰብ በርካታ ባህላዊ ምግቦችና ባህላዊ የአመጋገብ ሥርዓት አላቸው፡፡ ከጌዴኦ ሕዝብ ባህላዊ ምግቦች መካከል ቆጮ (ሆዳሞ)፣ ሻና ሚሊክ (ጎመን በሥጋ)፣ የተጋገረ ቆጮ እንደ እንጀራ ቁርጥ (ቁንጭሶ) ከብዙ በጥቂቱ ይጠቀሳሉ፡፡ ደራሮ (ከገብስ፣ ከማርና ከቅቤ በተቆላ ቡና) የሚዘጋጅ ባህላዊ ቆሎ ሲሆን፣ ከእንጨት በተሠራ ባህላዊ የቆሎ መያዥ ቆሬ ተደርጎ ይቀርባል፡፡ ለእንግዳም በኮባ እየተደረገ ደራሮ ይሰጣል፡፡ የደራሮ በዓል ቡና በሚደርስበት ወቅት የሚከበር በዓል በመሆኑ ምርቱን ለሰጣቸው ፈጣሪ የአገር ሽማግሌዎችም ምሥጋና ያቀርባሉ፡፡ ለበዓሉ ታዳሚዎችም ምርቃትና ዘመኑ መልካም እንዲሆን ይለምናሉ፡፡ ‹‹ደራሮ›› ማለት አበባ ማለት ነው፡፡ ደራሮ ቡና በሚያብብበት ጊዜ የሚከበር የጌዴኦ ማኅበረሰብ ባህላዊ በዓል ነው፡፡ (ቅርስ ባለሥልጣን)
- Advertisement -
- Advertisement -
- Advertisement -
ፌርማታ ፅሁፎች
ትኩስ ፅሁፎች
- Advertisement -
- Advertisement -