Sunday, December 10, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ስፖርትስትጠበቅ የነበረችው አትሌት ጉዳፍ ፀጋይ በዓለም ምርጥ አትሌት ሽልማት ላይ ሳትካተት ቀረች

ስትጠበቅ የነበረችው አትሌት ጉዳፍ ፀጋይ በዓለም ምርጥ አትሌት ሽልማት ላይ ሳትካተት ቀረች

ቀን:

የዓለም አትሌቲክስ ከወር በፊት ስም ዝርዝራቸውን ይፋ ካደረጋቸው 11 አትሌቶች መካከል የ5000፣ 10 ሺሕ እንዲሁም የ5 ሺሕ ሜትር ዳይመንድ ሊግ ክብረ ወሰን ባለቤት የሆነችው አትሌት ጉዳፍ ፀጋይ ተካታ የነበረ ቢሆንም፣ ከመጨረሻዎቹ አምስት ምርጥ የዓለም አትሌቶች ዝርዝር ውስጥ ሳትካተት ቀረች፡፡

ከጥቅምት 17 ቀን 2016 ዓ.ም. ጀምሮ ለሕዝብ ይፋ በሆኑ የድምፅ መስጫ አማራጮች መሠረት በተለያዩ ድረገጾች ድምፅ ሲሰጥ ቆይቷል፡፡

በዚህም መሠረት በዓለም አትሌቲክስ የማኅበራዊ ድረ ገጽ ሥር ለመምረጥ የሚፈልጉትን አትሌት ፎቶ በያዘው ልጥፍ ሥር ‹‹ላይክ›› እና ‹‹ሪቲዊት›› በማድረግ ድምፅ ሲሰጥም ነበር፡፡

ስትጠበቅ የነበረችው አትሌት ጉዳፍ ፀጋይ በዓለም ምርጥ አትሌት ሽልማት ላይ ሳትካተት ቀረች | Ethiopian Reporter | ሪፖርተር
የዓለም የማራቶን ክብረ ወሰን ባለቤቷ
ትዕግሥት አሰፋ

ከዚህም ባሻገር በማኅበራዊ ሚዲያው ከሚሰጠው ድምፅ ጎን ለጎን የዓለም አትሌቲክስ ካውንስል አባላትን 50 በመቶ ጨምሮ የዓለም አትሌቲክስ ቤተሰቦች  25 በመቶ፣ እንዲሁም የሕዝብ ምርጫን 25 በመቶ በማካተት አሸናፊዎቹ እንደሚለዩ ተጠቅሷል፡፡

በአንፃሩ በዓለም ሻምፒዮና በዳይመንድ ሊግ ከፍተኛ ግምት አግኝታ የነበረችው ጉዳፍ፣ በመጨረሻ አምስቱ ውስጥ ልትካተት እንደምትችል ከፍተኛ ግምት ሲሰጣት ብትቆይም፣ ሳትካተት ቀርታለች፡፡

የዓምናውን የበርሊን ማራቶንን ስታሸንፍ 18 ደቂቃዎችን በማሻሻል ሦስተኛዋ የዓለም የሴቶች የማራቶን ፈጣን ሰዓት ባለቤት መሆን ችላም ነበር። በወቅቱም በጊዜው የዓለም የሴቶች ማራቶን ክብረ ወሰን 2:14:04 በመግባት መጨበጥ የቻለችውን ኬንያዊቷ ብሪጅ ኮስጊና፣ እንግሊዛዊቷ ፓውላ ራድክሊፍን (2:15:25) በመከተል በ2:25:37 ሦስተኛዋ አትሌት መሆን ችላም ነበር።

ሆኖም ግን በዘንድሮው የዓለም ከምርጥ አምስት አትሌቶች ዝርዝር ውስጥ መካተት አልቻለችም፡፡ ምንም እንኳን ጉዳፍ በምርጥ አምስት የዓለም አትሌቶች ዝርዝር ውስጥ ባትካተትም፣ ሌላኛዋ የኢትዮጵያ ኩራት የሆነችውና በበርሊን ከተማ በተደረገው የማራቶን ውድድር 2፡11፡53 በመግባት ክብረ ወሰን ያሻሻለችው አትሌት ትዕግሥት አሰፋ ከምርጦቹ አምስት አትሌቶች አንዷ መሆን ችላለች፡፡

ትዕግሥት በሒደት የማራቶን ተሳትፎዋን፣ እንዲሁም ከዓመት ዓመት ሰዓቷን በማሻሻል፣ በዘንድሮው የበርሊን ማራቶን የዓለም ክብረ ወሰን ከመጨበጧም በላይ 2፡11፡53 በመግባት በሴቶችና በወንዶች መካከል ያለውን ሰዓት ማቀራረብ መቻሏ ጉድ ያስባለ ክስተት ነበር፡፡

ከዚህም በላይ ትዕግሥት በበርሊን ማራቶን ክብረ ወሰን የጨበጠችበት ሰዓት ማራቶን ፈር ቀዳጅ አበበ ቢቂላ በቶኪዮ ኦሊምፒክ 1957 ዓ.ም. የገባበትን 2፡12፡11 የበለጠ ሰዓት ማጠናቀቅ መቻሏ አብዛኛው ዘንድ አድናቆትን ፈጥሮ ነበር፡፡

ሩጫን በ200 ሜትር፣ 400 ሜትር፣ እንዲሁም 400 ሜትር ዱላ ቅብብል ወደ ረዥም ርቀቱ መግባት የቻለችው ትዕግሥት ወደ ጎዳና ሩጫ ከገባች በኋላ ከፍተኛ ጉዳት አስተናግዳ ከውደድር ርቃ ቆይታ ነበር፡፡

ጉዳቷ ከፍተኛ በመሆኑ በክራንች ለመሄድ ተገዳ የነበረችው ትዕግሥት፣ ጉዳቷ የከፋ እንደሆነና በሩጫ መቀጠል እንደማትችል ተነግሯት ነበር፡፡   

በዚህም መሠረት ተስፋ ያልቆረጠችው ትዕግሥት ቤተሰቦቿና አሠልጠኟ ዕርዳታ ወደ ልምምድ መመለስ መቻሏ ተገልጿል፡፡

ወደ ልምምድ ከተመለሰች በኋላ እስክታገግም ድረስ በ2020 እና 2021 ከማንኛውም ውድድር ርቃ ቆይታ ነበር፡፡ በዚህ ፈተና ውስጥ ያለፈችው አትሌቷ ከምርጥ አምስት የዓለም አትሌቶች ውስጥ አንዷ ሆናለች፡፡

በሌላ በኩል የዓለም አትሌቲክስ በዓመት ውስጥ ድንቅ ብቃት አሳልፈዋል ብሎ ስም ዝርዝራቸውን ይፋ ካደረጋቸው አትሌቶች መካከል ኬንያዊቷ ፈይዝ ኪፕዮንግ ትገኝበታለች፡፡

አትሌቷ በሃንጋሪ የተደረገው 19ኛው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮን 1500 እና 5000 ሜትሮች ወርቅ፣ 1500 ሜትር፣ የማይል ውድድር፣ እንዲሁም 5000 ሜትር ዓለም ክብረ ወሰን በማሸነፏ ከአምስቱ አትሌቶች ዝርዝር ውስጥ መካተት ችላለች፡፡

የዓለም ምርጥ አትሌት ሽልማት እንደሚያሸንፉ ግምት ከተሰጣቸው አትሌቶች መካከልም በቀዳሚነት ተጠቅሳለች፡፡

የዓለም አትሌቲክስ ስም ዝርዝራቸውን ይፋ ካደረጋቸው አትሌቶች መካከል 400 መሰናክል ኔዘርላንዳዊቷ አትሌት ፌምስ ቦል፣ የ100 እና 200 ሜትር የዓለም ሻምፒዮን የብር ሜዳሊያ ባለቤቷ ጃማይካዊቷ ሼሪካ ጃክሰን እንዲሁም በሱሉስ ዝላይ የዓለምና የዳይመንድ ሊግ አሸናፊ መሆን የቻለችው ቬንዙዌላዊቷ አትሌት ዮሊማር ሮጃስ ይገኙበታል፡፡

የዓለም አትሌቲክስ በማኅበራዊ ሚዲያ አማራጮች አማካይነት ሁለት ሚሊዮን ድምፅ መሰብሰብ መቻሉን ያስታወቀ ሲሆን፣ ይህም ክብረ ወሰን መሆኑን ጠቅሷል፡፡

እንደ ዓለም አትሌቲክስ መረጃ የዓመቱ ምርጥ አትሌት ሽልማት መርሐ ግብር ሰኞ ታኅሳስ 1 ቀን 2016 ዓ.ም. በፈረንሣይ ሞናኮ ከተማ እንደሚስተናገድ ታውቋል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ለሰው ልጅ መብት መከበር ስናወራ 75 ዓመት ሞላን!

በገነት ዓለሙ ዓለም ስለሰብዓዊ መብቶች ሲያወራ፣ ሲምል፣ ሲገዘት፣ ሲፈጠም፣ ቃል...

ካልተማከለ የካፒታል ገበያ ወደ ዘመናዊና የተደራጀ የሰነደ ሙዓለ ንዋዮች ገበያ

በእሱፈቃድ ተረፈ በአገራችን የካፒታል ገበያ አዋጅ መውጣትን ተከትሎ የተማከለ የሰነደ...

ለማይቀረው ምክክርና ድርድር እንዘጋጅ

በያሲን ባህሩ  የዘመናዊት ኢትዮጵያ ፖለቲካ ውዝግብ በትንሹ የአንድ ምዕተ ዓመት...

ደንብ አስከባሪዎች ደንብ ያክብሩ!

በአዲስ አበባ ከተማ ደንብ አስከባሪዎች፣ ሌሎች የፀጥታ አካላት፣ እንዲሁም...