ከሰባት ወራት በፊት የሳፋሪኮም የውጭ ጉዳዮች ዋና ኃላፊና ተቆጣጣሪ ሆነው ተቀጥረው የነበሩት ሔኖክ ተፈራ (አምባሳደር) ሥራቸውን መልቀቃቸው ታወቀ፡፡
የፈረንሣይ፣ ስፔን፣ ፖርቹጋልና ሞናኮ አምባሳደር ሆነው ለሦስት ዓመታት ያገለገሉት ሔኖክ (አምባሳደር) ሥራቸውን እንዳጠናቀቁ፣ የሳፋሪኮም ቴሌኮሙዩኒኬሽን ኢትዮጵያ ኩባንያ የውጭ ጉዳዮች ኃላፊና ተቆጣጣሪ ሆነው መቀጠራቸው ይታወሳል፡፡
ሔኖክ (አምባሳደር) ‹‹በግል ምክንያት›› በሚል ሥራቸውን በራሳቸው ፈቃድ መልቀቃቸው ከመነገሩ በስተቀር፣ ተጨማሪ ምክንያቶች ስለመኖራቸው እሳቸውን አግኝቶ ለማነጋገር የተደረገው ጥረት አልተሳካም፡፡