በዚህ ዓመት፣
ብንጣላ መታረቂያ
ብንታረቅ ለመጣያ
ትንሸ ቦታ መጠለያ
ትንሽ ቦታ መሠደጃ፡፡
ምናለበት፣
ለምናልባት ብንተውለት
ፍፁም መሆን ስለማንችል
ትንሽ ቦታ እንዋዋል፣ በልባችን ደግ እንሁን፡፡
በአንጎላችን መላወሻ፣
ትንሽ ቦታ እንተውለት
‹‹ምናልባት›› የምንልበት!!
ልክ እንደዓምና ለዚህ ዓመት
ብንጣላ መታረቂያ
ብንታረቅ ለመጣያ
ብንታሠር ይቅር ማያ
ትንሽ እንተው ባዶ ቦታ፡፡
ጥግ ድረስ የለም ሥራ፣ ጥግ ድረስ የለም ፋታ፡፡
በልባችን ደግ በኩል፣ እንፈልግ ባዶ ቦታ፣
የጳጉሜ ዓይነት ትንሽ ቦታ፡፡
ለዘመን መለወጫ፡፡
(ነብይ መኮንን፣ ስውር ስፌት ቁጥር 2፣ 2005 ዓ.ም.)