የግብርና ምርቶች በሚከማቹበት መጋዘን ውስጥ የሚሠራ ደቡብ ኮሪያዊ በሮቦት ተቀርጥፎ መሞቱን ስካይ ኒውስ ዘግቧል፡፡
ካርቶን በማንሳት ላይ የነበረው ሮቦት በስህተት በ40ዎቹ የዕድሜ ክልል ውስጥ የሚገኘውን ጎልማሳ በማንሳቱ የሠራተኛው ሕይወት ሊያልፍ ችሏል፡፡
ጎልማሳው ሊሞት የቻለው ሮቦቱ በጭንቅላቱና በደረቱ ላይ ባደረሰበት ጉዳት ሲሆን፣ በደቡብ ኮሪያ የጎሲዮንግ አስተዳደር ፖሊስ፣ ሮቦቱ ደኅንነቱ የተጠበቀ ስለመሆኑና ያሉበትን እክሎች በመመርመር ላይ መሆኑን አስታውቋል፡፡
ከዚህ ቀደምም ባፒዮንግቴክ በሚገኝ የወተት ማቀነባበሪያ ፋብሪካ ውስጥ አንድ ሠራተኛ በሮቦት ከባድ ጉዳት እንደደረሰበት አሶሽየትድ ፕሬስ አስታውሷል፡፡