Sunday, December 10, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ስፖርትዋሊያዎቹ በአዲስ አሠልጣኝ እየተመሩ የዓለም ዋንጫ ማጣሪያ ጨዋታን በሞሮኮ ያደርጋሉ

ዋሊያዎቹ በአዲስ አሠልጣኝ እየተመሩ የዓለም ዋንጫ ማጣሪያ ጨዋታን በሞሮኮ ያደርጋሉ

ቀን:

አዲስ አሠልጣኝ የተሾመላቸው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን (ዋሊያዎቹ)፣ በዓለም ዋንጫ የማጣሪያ ጨዋታ የሴራሊዮንንና የቡርኪና ፋሶ ብሔራዊ ቡድኖችን በሞሮኮ ይገጥማሉ፡፡

ዋሊያዎቹ ኅዳር 5 ቀን 2016 ዓ.ም. የሴራሊዮን ብሔራዊ ቡድንን የሚገጥሙ ሲሆን፣ ኅዳር 11 ደግሞ የቡርኪና ፋሶ ብሔራዊ ቡድንን ይገጥማሉ፡፡

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን፣ የኢትዮጵያ መድን እግር ኳስ ክለብ አሠልጣኝ ገብረ መድኅን ኃይሌን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ዋና አሠልጣኝ አድርጎ መሾሙ የሚታወስ ነው፡፡  

አሠልጣኝ ገብረ መድኅን ደግሞ መሳይ ተፈራ በምክትል አሠልጣኝነት፣ እንዲሁም ደሳለኝ ገብረ ጊዮርጊስን በግብ ጠባቂ አሠልጣኝነት የቡድኑ ረዳት ሆነው እንዲሠሩ መርጠዋል፡፡

በዚህም መሠረት ዋና አሠልጣኝ ገብረ መድኅን ለዓለም ዋንጫ ማጣሪያ ጨዋታ ቅድመ ዝግጅት ለማድረግ ለ30 ተጫዋቾች ጥሪ አቅርበው፣ በአዳማ ዝግጅት ሲያደርጉ ቆይተው፣ የመጨረሻ ምዕራፍ ዝግጅት በአዲስ አበበ ቢቂላ ስታዲዮም መደበኛ ልምምዳቸውን ሲያደርጉ ቆይተዋል፡፡

ዋሊያዎቹ በአዲስ አበባ ሲያደርጉት የነበረውን ልምምድ ካጠናቀቁ በኋላ፣ አሠልጣኝ ገብረ መድኅን 23 ተጫዋቾችን ለይተዋል፡፡ ወደ ብሔራዊ ቡድን ውስጥ እንዲካተቱ ጥሪ ከተደረገላቸው ተጫዋቾች መካከል የማሜሎዲ ሰንዳውንስ አጥቂ አቡበከርና በብሔራዊ ቡድን በማገልገል ልምድ ያካበተውና በቅርቡ ወደ አገር ውስጥ ሊግ ተመልሶ ለመቻል ፊርማውን ያኖረው ሽመልስ በቀለ፣ በጉዳት ምክንያት በስብስቡ ውስጥ ሳይካተቱ ቀርተዋል፡፡

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን አሠልጣኝ ውበቱ አባተ እየተመራ የተለያዩ አኅጉር አቀፍ ውድድሮች ላይ ስኬታማ ጉዞ አለማሳለፉ ይታወሳል፡፡  

በዚህም መሠረት ብሔራዊ ፌዴሬሽኑ ከአሠልጣኝ ውበቱ ጋር በስምምነት የተለያዩ ሲሆን፣ ለቀሪ ማጣሪያ ጨዋታዎች በቴክኒክ ባለሙያው ዳንኤል ገብረማርያም እየተመራ መቆየቱ ይታወሳል፡፡

የፌዴሬሽኑ የቴክኒክ ዳይሬክተርና ጊዜያዊ አሠልጣኝ ኢንስትራክተር ዳንኤል በቀሪ የአፍሪካ ዋንጫ ጨዋታዎች ከማሊና ግብፅ መግጠማቸው ይታወሳል፡፡

በመጨረሻም ዋሊያዎቹ በአሜሪካ ባደረጉት የቅድመ ዝግጅት መርሐ ግብር የአትላንቲክ ውቅያኖስ ዳርቻ ብሔራዊ ቡድን ከሆነው ጉያና ጨዋታ አድርገዋል፡፡ ዋሊያዎቹ ከአሜሪካ ጉዟቸው ከተመለሱ በኋላ ያለ ሥልጠና የቆዩ ሲሆን፣ ብሔራዊ ፌዴሬሽኑ በአገር ውስጥ የሚገኙ አሠልጣኞችን ከገመገመ በኋላ አሠልጣኝ ገብረ መድኅን ኃይሌን አሠልጣኝ አድርጎ ሾሟል፡፡

በ2015 ዓ.ም. ወደ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ያደገው መድን ኢትዮጵያ እግር ኳስ ክለብ ውጤታማ ጊዜ ያሳለፉት አሠልጣኝ ገብረ መድኅን ዋሊያዎቹን ደርበው እንዲያሠለጥኑ ኃላፊነት ተረክበዋል፡፡

እ.ኤ.አ. 2016 ዋሊያዎቹ በአሠልጣኝ አሸናፊ በቀለ እየተመሩ፣ በአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ጨዋታ ሲሳተፉ፣ አሠልጣኙ ውላቸው መቋረጡን ተከትሎ አሠልጣኝ ገብረ መድኅን በጊዜያዊነት ቀሪውን ሁለት ጨዋታ መምራታቸው ይታወሳል፡፡

አሠልጣኙ በመጀመሪያ የብሔራዊ ቡድን ተሳትፏቸው የሌሎች ብሔራዊ ቡድን 2 ለ1፣ እንዲሁም የሲሼልሲ ብሔራዊ ቡድንን 2 ለ1 መርታት ችለዋል፡፡

የቀድሞ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን አጥቂ የነበሩት ገብረ መድኅን፣ የአሠልጣኝ አስራት ኃይሌ ምክትል አሠልጣኝ በመሆን ማገልገላቸው ይታወቃል፡፡

ማጥቃትን መሠረት ያደረገ ቡድን በመገንባት የሚታወቁት አሠልጣኙ፣ ብሔራዊ ቡድኑ በአኅጉራዊ የውድድር መድረክ ላይ መሳተፍ የሚያስችል ቡድን በሒደት ለመመሥረት ውጥን እንዳላቸው በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ አንስተዋል፡፡

እንደ አሠልጣኙ ማብራሪያ ከሆነ፣ ‹‹ቀኑን ሙሉ ኳስ ሲያንከባልል የሚውል ቡድን አልፈልግም፡፡ ይልቁንም ጫና ፈጥሮ የሚያጠቃ ቡድን ነው መገንባት የምፈልገው፤›› በማለት አስተያየታቸውን ሰንዝረዋል፡፡

ከዚህም ባሻገር ጠንካራና ተፎካካሪ ብሔራዊ ቡድን መገንባት የአሠልጣኝ ግዴታ መሆኑ የተገለጸ ሲሆን፣ አሠልጣኙም በሒደት ጠንካራ ብሔራዊ ቡድን ለመገንባት እንደሚጥሩ ጠቅሰዋል፡፡

በሌላ በኩል በአገር ውስጥ የካፍ መሥፈርትን ያሟላ አንድም ስታዲዮም ባለመኖሩ፣ ዋሊያዎቹ አሁንም የማጣሪያ ጨዋታቸውን በሞሮኮ የሚያደርጉ ይሆናል፡፡

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በዓለም ዋንጫ የማጣሪያ ተሳትፎ ስኬታማ ጊዜ ያሳለፈው እ.ኤ.አ. 2014 በአሠልጣኝ ሰውነት ቢሻው እየተመራ ነበር፡፡ በጊዜውም ከአሥር የአፍሪካ ብሔራዊ ቡድን መካከል አንደኛው መሆን ችሎ ነበር፡፡

ከዚያ በኋላም ዋሊያዎቹ በዓለም ዋንጫ ማጣሪያ ከምድባቸው ማለፍ ተስኗቸው ቆይተዋል፡፡ ከዚህ ጋር ተያይዞም ብሔራዊ ቡድኑን የተረከቡት አሠልጣኝ ገብረ መድኅን ‹‹የት ድረስ ይጓዛሉ?›› የሚለው የሁሉም ስፖርት ወዳጅ የሚጠባበቀው ምላሽ ነው፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ለሰው ልጅ መብት መከበር ስናወራ 75 ዓመት ሞላን!

በገነት ዓለሙ ዓለም ስለሰብዓዊ መብቶች ሲያወራ፣ ሲምል፣ ሲገዘት፣ ሲፈጠም፣ ቃል...

ካልተማከለ የካፒታል ገበያ ወደ ዘመናዊና የተደራጀ የሰነደ ሙዓለ ንዋዮች ገበያ

በእሱፈቃድ ተረፈ በአገራችን የካፒታል ገበያ አዋጅ መውጣትን ተከትሎ የተማከለ የሰነደ...

ለማይቀረው ምክክርና ድርድር እንዘጋጅ

በያሲን ባህሩ  የዘመናዊት ኢትዮጵያ ፖለቲካ ውዝግብ በትንሹ የአንድ ምዕተ ዓመት...

ደንብ አስከባሪዎች ደንብ ያክብሩ!

በአዲስ አበባ ከተማ ደንብ አስከባሪዎች፣ ሌሎች የፀጥታ አካላት፣ እንዲሁም...