Sunday, December 10, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ስፖርትኢትዮጵያ የምታስተናግደው የአፍሪካ የቦክስ ኮንፌዴሬሽን ጠቅላላ ጉባዔና ዝግጅቱ

ኢትዮጵያ የምታስተናግደው የአፍሪካ የቦክስ ኮንፌዴሬሽን ጠቅላላ ጉባዔና ዝግጅቱ

ቀን:

አፍሪካ በዓለም አቀፍ ስፖርታዊ እንቅስቃሴ ከፍተኛ ድርሻ አላት፡፡ የአፍሪካውያን ድምፅ የዓለም ስፖርትን ለመምራት ለሚሹ ትልቅ ቦታ አለው፡፡ በአንፃሩ የአፍሪካውያን ድምፅ  ከምርጫ ፍጆታነት አልፎ ስፖርቱን ማሳደግ ግን አልቻለም፡፡ ይልቁንም አፍሪካ ያላትን የተፈጥሮ ሀብት፣ እንዲሁም ወጣቱን ትውልድ በስፖርት አንፃ ተፎካካሪ ከማድረግ ባሻገር፣ ስፖርቱን እንመራለን የሚሉ ግለሰቦች ለምርጫ ፍጆታ ብቻ ሲጠቀሙት መመልከት የተለመደ ነው፡፡

በቅርቡ የአፍሪካ ቦክስ ኮንፌዴሬሽን መደበኛ ጠቅላላ ጉባዔ ለማከናው አዲስ አበባ ተመርጣለች፡፡ ከመደበኛ ጠቅላላ ጉባዔ በዘለለ አዲስ አበባ ጠቅላላ ጉባዔውን ወደ ኢትዮጵያ ለማምጣት ከፍተኛ ፈተና እንደገጠማት የኢትዮጵያ ቦክስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት አቶ ኢያሱ ወሰን ተናግረዋል፡፡

ቅዳሜ ኅዳር 8 ቀን 2016 ዓ.ም. በአፍሪካ ኅብረት አዳራሽ በሚሰናዳው መደበኛ ጠቅላላ ጉባዔ፣ የኢትዮጵያ ቦክስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት አቶ ኢያሱ ዕጩ ሆነው መቅረባቸው ተገልጿል፡፡

ከቦታ ምርጫ ጋር ተያይዞ ከፍተኛ ውዝግብ ሲያስተናግድ የቆየው የአፍሪካ ኮንፌዴሬሽን መደበኛ ጠቅላላ ጉባዔው ከአፍሪካ ውጪ ባለ አገር መሆን አለበት የሚል መከራከሪያ ሲቀርብበት ነበር፡፡

የአፍሪካ ቦክስ ፌዴሬሽን መደበኛ ጠቅላላ ጉባዔ ማክሰኞ መስከረም 29 ቀን 2016 ዓ.ም. በዱባይ እንደሚደረግ ተገልጾ የነበረ ቢሆንም፣ ከፍተኛ ውዝግብ አስነስቶ ነበር፡፡ ይህም መደበኛ ጠቅላላ ጉባዔው ‹‹በአፍሪካ እንጂ በዱባይ መሆን አይገባውም›› የሚል መከራከሪያ በመቅረቡ የአፍሪካ ቦክስ ኮንፌዴሬሽን ጠቅላላ ጉባዔውን ለማራዘም ተገዷል፡፡

የመደበኛ ጠቅላላ ጉባዔ በዱባይ ማድረግ የተፈለገበት ምክንያት የዓለም አቀፍ ቦክስ ፌዴሬሽን መስከረም 28 ቀን በዱባይ ለማድረግ ማቀዱን ተከትሎ እንደሆነና ከወጪ ቁጠባ አንፃር ታስቦ እንደሆነ ተብራርቶ ነበር፡፡

ሆኖም የአፍሪካ ቦክስ ኮንፌዴሬሽን የመተዳደሪያ ደንቡን አንቀጽ 17.7 በመጥቀስ ‹‹የአፍሪካ ቦክስ ኮንፌዴሬሽን ምርጫ በአፍሪካ ብቻ መሆን ይገባዋል›› በሚል በጻፈው ደብዳቤ መሠረት በዱባይ ሊደረግ የነበረው መደበኛ ጠቅላላ ጉባዔ ሊሰረዝ ችሏል፡፡

ምርጫው በአፍሪካ መከናወን እንዳለበት ከተወሰነ በኋላ፣ ኢትዮጵያ መደበኛ ጠቅላላ ጉባዔውን ለማስተናገድ ጥያቄ በማቅረቧ የአባላቱን ድጋፍ ማግኘቷን ተከትሎ ዕድሉን ማግኘቷን አቶ ኢያሱ ለሪፖርተር አስረድተዋል፡፡

ሆኖም ኢትዮጵያ መደበኛ ጠቅላላ ጉባዔውን ማስተናገዷ ቅሬታ የፈጠረባቸው የአፍሪካ አገሮች መኖራቸው የተጠቆመ ሲሆን፣ በተለይ አዲስ አበባ የአፍሪካ ኅብረት መቀመጫ በመሆኗ የአፍሪካ ቦክስ ኮንፌዴሬሽን ጠቅላላ ጉባዔውን በአዲስ አበባ ሊቀይር ይችላል የሚል ሥጋት በመኖሩ እንደሆነ ተነስቷል፡፡

ከዚህም ባሻገር ኢትዮጵያ በአፍሪካ መድረክ ስፖርት ለመምራት ዕጩ ፕሬዚዳንት ማቅረቧን ተከትሎ ለማሸነፍ ዕድል ይሰጣታል የሚል ጥርጣሬ መኖሩ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡ በሌላ በኩል ምርጫውን ተከትሎ ከፍተኛ ውዝግቦች ካስነሱ ጉዳዮች መካከል የምርጫውና የዕጩዎች ውክልና ሲሆን፣ 30 አገሮች ለምርጫ በቀረቡት ዕጩዎች ላይ ትችት ሰንዝረዋል፡፡

ይህም የሆነው ዕጩ ሆነው ከቀረቡት መከከል የተለያዩ የሙስና ክስ የቀረበባቸውና በአፍሪካ ቦክስ ኮንፌዴሬሽን የታገዱ መኖራቸውን ተከትሎ ነው፡፡

በሙስና ቅሌት ስማቸው ከተጠቀሰው መካከል የካሜሮኑ ዕጩ በርትራንድ ሜንዱጋ ይገኙበታል፡፡ እ.ኤ.አ. ከ2022 የአፍሪካ ቦክስ ኮንፌዴሬሽንን ለመምራት የተመረጡት ካሜሮናዊው በርትራንድ የግል ፍላጎታቸውን ያንፀባርቃሉ የሚል ክስ የተነሳባቸው ሲሆን፣ ከአንድ ዓመት በላይ መምራት ሳይችሉ ከኃላፊነታቸው እንዲነሱ የተደረገ ሲሆን፣ በዓለም አቀፍ ቦክስ ፌዴሬሽን ውስጥ ያላቸው ውክልናን ተነጥቀዋል፡፡

የቀድሞ ፕሬዚዳንት ዘንድሮም ዕጩ ሆነው የቀረቡ ሲሆን፣ ከተለያዩ የአፍሪካ አባል አገሮች ተቃውሞ እየደረሰባቸው ነው፡፡

ሌላው በምርጫው ዕጩ ሆነው ቀርበው የነበሩት የዑጋንዳ ቦክስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት ሞሰስ ሙሐንጊ ሲሆኑ፣ የአፍሪካ ቦክስ ኮንፌዴሬሽን መተዳደሪያ ደንብን በመጣሳቸው፣ እንዲሁም በአገራቸው የሕግ ጥላ ሥር ውለው ክስ የቀረበበቸው ናቸው፡፡ ሆኖም ከተለያዩ አገሮች ዕጩ ሆነው መቅረባቸው ቅሬታ በማስነሳቱ እስከ ቅርብ ጊዜ በምርጫ ውስጥ እንደሚሳተፉ ቢታወቅም፣ በመጨረሻ ራሳቸውን አግልለዋል፡፡

የምርጫ ሒደቱን ተከትሎ ውስብስብ ሒደትን ማለፋቸውን የሚያነሱት ኢትዮጵያዊው ዕጩ፣ በምርጫው ከፍተኛ ግምት ከተሰጣቸው መካከል ቀዳሚ ናቸው፡፡

ኅዳር 8 ቀን በአዲስ አበባ በአፍሪካ ኅብረት የመሰብሰቢያ አዳራሽ በሚከናወነው ምርጫ የካሜሮኑ ዕጩ በርትራንድ ሜንዱጋ እንዲሁም የሞሮኮ ሞሐመድ ቦድር ይገኙበታል፡፡

ኢትዮጵያን የወከሉት አቶ ኢያሱ ምርጫውን ማሸነፍ ከቻሉ በአፍሪካ መድረክ ስፖርቱን በመምራት ከቀድሞ የካፍ ፕሬዚዳንት አቶ ይድነቃቸው ተሰማ በመቀጠል ሁለተኛ ኢትዮጵያዊ ይሆናሉ፡፡

ኢትዮጵያ መደበኛ ጠቅላላ ጉባዔውን ለማሰናዳት ዝግጅቷን አጠናክራ መቀጠሏን የጠቀሱት አቶ ኢያሱ፣ እንግዶቿን በአግባቡ አስተናግዳ ለመሸኘት ከሁሉም ባለድርሻ አካላት ጋር በጥምረት ዝግጅት እየተደረገ እንደሚገኝ ተገልጿል፡፡..       

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ለሰው ልጅ መብት መከበር ስናወራ 75 ዓመት ሞላን!

በገነት ዓለሙ ዓለም ስለሰብዓዊ መብቶች ሲያወራ፣ ሲምል፣ ሲገዘት፣ ሲፈጠም፣ ቃል...

ካልተማከለ የካፒታል ገበያ ወደ ዘመናዊና የተደራጀ የሰነደ ሙዓለ ንዋዮች ገበያ

በእሱፈቃድ ተረፈ በአገራችን የካፒታል ገበያ አዋጅ መውጣትን ተከትሎ የተማከለ የሰነደ...

ለማይቀረው ምክክርና ድርድር እንዘጋጅ

በያሲን ባህሩ  የዘመናዊት ኢትዮጵያ ፖለቲካ ውዝግብ በትንሹ የአንድ ምዕተ ዓመት...

ደንብ አስከባሪዎች ደንብ ያክብሩ!

በአዲስ አበባ ከተማ ደንብ አስከባሪዎች፣ ሌሎች የፀጥታ አካላት፣ እንዲሁም...