Sunday, December 10, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊበአንድ የባንክ ፈቃድ ከአንድ ጊዜ በላይ ምርት እንዳይገባ መከልከሉ አስመጪዎችን ሥጋት ውስጥ...

በአንድ የባንክ ፈቃድ ከአንድ ጊዜ በላይ ምርት እንዳይገባ መከልከሉ አስመጪዎችን ሥጋት ውስጥ ከቷል

ቀን:

የኢትዮጵያ ብሔራዊ  ባንክ፣ በኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን ጥያቄ መሠረት አስመጪና ላኪዎች በአንድ የባንክ ፈቃድ ከአንድ ጊዜ በላይ ምርት ወደ አገር ቤት እንዳያስገቡም ሆነ ወደ ውጪ እንዳይልኩ ትዕዛዝ መተላለፉ ሥጋት ውስጥ እንደከተታቸው ገለጹ፡፡

ብሔራዊ ባንክ ጥቅምት 19 ቀን 2015 ዓ.ም. ለሁሉም ባንኮች የጻፈው ደብዳቤ እንደሚለው ከሆነ፣ ኮሚሽኑ በወሰነው ውሳኔ አንዳንድ ላኪዎችና አስመጪዎች በአንድ የባንክ ፈቃድ በተለያየ ጊዜ ምርቶችን መላክና ማስመጣት የሚፈቅደውን ሕግ፣ የአገርን ጥቅም በሚያሳጣና በሕገወጥ መንገድ እየተጠቀሙበት በመሆኑ አንድ LC (LETTER OF CREDIT ለአንድ ምርት ብቻ እንዲሆን ሊያደረግ ነው፡፡

ትዕዛዙ ተግባራዊ የሚሆነው ኅዳር 10 ቀን 2016 ዓ.ም. በመሆኑ በአሁኑ ሰዓት በክፍልፋይ (Partial Shipment) መሠረት ስምምነት ያደረጉ ድርጅቶችን ያካተተ መሆን የለበትም ሲሉ ስማቸው እንዲጠቀስ ያልፈለጉ አስመጪና ላኪ ድርጅቶች ለሪፖርተር ተናግረዋል፡፡

አንዳንድ ባንኮች ከደንበኞቻቸው ጋር ያሰሩትን ስምምነት መቀየር እንደማይችሉና ትዕዛዙ ተግባራዊ መሆን ያለበት አዲስ ስምምነት ለሚያደርጉ ድርጅቶች መሆን እንደሚገባ ለብሔራዊ ባንክ ደብዳቤ እየላኩ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

በባንኮች በኩል የሚከፈተው LC (LETTER OF CREDIT) በገዥና በአቅራቢ ድርጅት መካከል የሚደረግ ጠንካራ ስምምነት መሆኑ ይታወቃል፡፡

የክፍልፋይ ስምምነት (Partial Shipment) ማለት ገዥውና አቅራቢ በስምምነታቸው መሠረት በአንድ ጊዜ ሁሉንም ምርት በተለያየ ምክንያት መላክ ስለማይቻል ከሥር ከሥር እየተመረተ ለመላክ የሚስማሙበት አካሄድ ነው፡፡

አንዳንድ ጊዜ ደግሞ በኮንቴይነር እጥረት፣ ገዥው በቂ ማከማቻ ቦታ ከሌለው፣ የክፍልፋይ ስምምነት ይደረጋል፡፡ ይህ ስምምነት ጥሬ ዕቃዎቹ በወቅቱ እንዲገቡ ያደርጋል እንጂ አገርን የሚጎዳ አይደለም ሲሉ አስመጪ ድርጅቶች ተናግረዋል፡፡

የአስመጪዎች ትልቅ ሥጋት የሆነው የክፍልፋይ ስምምነት (Partial Shipment) መሠረት የታዘዙት ዕቃዎች ጂቡቲ የሚደርሱት የጉምሩክ ኮሚሽን ውሳኔ ከሚጀመርበት ቀን በኋላ ነው፡፡

በአዲሱ ትዕዛዝ ቀድሞ ስምምነት የነበራቸውን በማካተቱ ምርቶቹ መጥተው ወደብ ላይ መዘግየት፣ የባንክ  ብድር መክፈል አለመቻል፣ የቀረጥ ክፍያ አለመስተናገድና ለተጨማሪ ‹‹ዴሜሬጅ›› ክፍያ እንደሚያወጡ ገልጸዋል፡፡

በመሆኑም ዕገዳው ቀድሞ ስምምነት የተደረገባቸውን ሳያካትት ከኅዳር 10 ቀን በኋላ ለሚደረግ አዲስ ስምምነት ፈቃድ መከልከል አለበት ብለዋል፡፡

በክፍልፋይ ጊዜ በአንድ የባንክ ፈቃድ በተለያዩ ወቅቶች ምርቶችን ማስገባት መፈቀዱ፣ አስመጪዎቹ ባንክ ከፈቀደላቸው የውጭ ምንዛሪ በላይ የሚያወጡ ምርቶችን የማስገባት ዕድሎችን እንደመፍጠሩ፣ በዚህም ባንኩ ከፈቀደላቸው ውጪ ጥቅም ላይ ያዋሉት ገንዘብ ከጥቁር ገበያ የተገኘ ነው የሚለውን ጥርጣሬ ከማሳደጉ ባለፈ፣ አሠራሩም ሕገወጥ ገበያን አበረታቷል በሚል የተላለፈ ትዕዛዝ ነው፡፡

በጉዳዩ ላይ ለሪፖርተር ማብራሪያ የሰጡት የዘርፉ ባለሙያ እንደሚሉት ከሆነ የክፍልፋይ ስምምነት (Partial Shipment) አገርን ችግር ውስጥ የሚከት አይደለም ብለዋል፡፡

ጉምሩክ ኮሚሽን ሕገወጥ ተግባርን ለመከላከል የሚፈልግ ከሆነ በቀላሉ ሕገወጦቹን በመለየት በሕግ መጠየቅ እንጂ በትክክለኛ አካሄድ የሚሠሩትንም በአንድ ላይ በማገድ መፍትሔ አይመጣም ሲሉ ገልጸዋል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ለሰው ልጅ መብት መከበር ስናወራ 75 ዓመት ሞላን!

በገነት ዓለሙ ዓለም ስለሰብዓዊ መብቶች ሲያወራ፣ ሲምል፣ ሲገዘት፣ ሲፈጠም፣ ቃል...

ካልተማከለ የካፒታል ገበያ ወደ ዘመናዊና የተደራጀ የሰነደ ሙዓለ ንዋዮች ገበያ

በእሱፈቃድ ተረፈ በአገራችን የካፒታል ገበያ አዋጅ መውጣትን ተከትሎ የተማከለ የሰነደ...

ለማይቀረው ምክክርና ድርድር እንዘጋጅ

በያሲን ባህሩ  የዘመናዊት ኢትዮጵያ ፖለቲካ ውዝግብ በትንሹ የአንድ ምዕተ ዓመት...

ደንብ አስከባሪዎች ደንብ ያክብሩ!

በአዲስ አበባ ከተማ ደንብ አስከባሪዎች፣ ሌሎች የፀጥታ አካላት፣ እንዲሁም...