Monday, December 11, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊየትራፊክ ቁጥጥርና የፓርኪንግ አስተዳደር ችግሮችን ይፈታል የተባለ ቴክኖሎጂ ሥራ ላይ ሊውል ነው

የትራፊክ ቁጥጥርና የፓርኪንግ አስተዳደር ችግሮችን ይፈታል የተባለ ቴክኖሎጂ ሥራ ላይ ሊውል ነው

ቀን:

የትራፊክ ደንብ መተላለፍ፣ የቅጣት አፈጻጸምና የመኪና ማቆሚያ (ፓርኪንግ) አስተዳደር ሥርዓትን በቴክኖሎጂ የሚያግዝ ፕሮጀክት ቀርፆ ተግባር ላይ ሊያውል መሆኑን፣ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትራፊክ ማኔጅመንት ኤጀንሲ አስታወቀ፡፡

ከትራፊክ ቁጥጥርና ከመኪና ማቆሚያ አስተዳደር ሥርዓት ጋር ተያይዞ ከሚስተዋሉ ችግሮች መካከል የትራፊክ ደንብ መተላለፍ የቅጣት አፈጻጸም ሒደት በቴክኖሎጂ የተደገፈ አለመሆንና ወጥ የሆነ የመኪና ማቆሚያ አገልግሎት አሰጣጥ አለመኖር ዋነኛ ችግሮች ናቸው ሲሉ፣ የአዲስ አበባ ትራፊክ ማኔጅመንት ዋና ዳይሬክተር አቶ ክበበው ሚደቅሳ ዓርብ ጥቅምት 23 ቀን 2016 ዓ.ም. በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ አስታውቀዋል፡፡

‹‹የትራፊክ ቁጥጥርና የፓርኪንግ አስተዳደር ሥርዓት›› በሚል መጠሪያ ተግባራዊ ይሆናል የተባለው ፕሮጀክት፣ የትራፊክ ደንብ አስከባሪዎችንና የተቀጪዎችን ጊዜ የሚቆጥብ ከመሆኑም ባሻገር ቀልጣፋና ፈጣን አማራጮችን የሚያቀርብ ነው ሲሉ ዋና ዳይሬክተሩ ገልጸዋል፡፡

የደንብ ተላላፊዎችን ቅጣት መመዝገብና የአሽከርካሪና ተሽከርካሪዎችን መረጃ ማደራጀት፣ እንዲሁም የቅጣት ሪፖርቶችን ማውጣት ሲስተሙ (መተግበሪያው) ከሚሠራቸው ተግባራት መካከል ተጠቃሽ ናቸው ያሉት አቶ ክበበው፣ ፕሮጀክቱን ሥራ ላይ ለማዋል የዘርፉ ባለሙያዎችና አመራሮችና የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ባለሙያዎች ለአንድ ዓመት ጥናት አድርገውበት ተግባራዊ መሆን ጀምሯል፡፡

መተግበሪያውን በትራፊክ ፖሊስ ተሽከርካሪዎች ላይ በመግጠም በአካባቢው ያሉትን ተሽከርካሪዎች ሙሉ መረጃና የአሽከርካሪውን እንቅስቃሴ መከታተልና ሕጉን ሲተላለፉ ቅጣት፣ እንዲሁም ማስጠንቀቂያ መስጠት የሚያስችል መተግበሪያ መሆኑን የተናገሩት ደግሞ የተቋሙ ዋና አማካሪ ቀዳማዊ አንዱዓለም (ኢንጂነር) ናቸው፡፡

በእግራቸው ቁጥጥር ለሚያደርጉ የትራፊክ ፖሊሶች ደግሞ ለዚሁ ተግባር ብቻ የሚውል ታብሌት ስልክ እንደሚይዙና የተሽከርካሪውን ሰሌዳ ፎቶ በማንሳት ሕጋዊነቱን ማረጋገጥ፣ ቦሎ ማሳደስና አለማሳደሱን ጨምሮ ሙሉ መረጃውን መተግበሪያውን በመጠቀም ማወቅ የሚቻልበት ሲስተም ነው ያሉት ቀዳማዊ (ኢንጂነር)፣ የአሽከርካሪው መንጃ ፈቃድ ሐሰተኛ መሆኑ አለመሆኑንም ማረጋገጥ እንደሚቻል ተናግረዋል፡፡

በተለይ በትራፊክ ፖሊስ መኪና ላይ የሚገጠመው ካሜራ በአንድ ደቂቃ ውስጥ እስከ 1‚800 ተሽከርካሪዎችን መቆጣጠር የሚያስችል መሆኑን አማካሪው ገልጸዋለ፡፡

መተግበሪያው በአንድ ጊዜ ብዙ መረጃዎችን ከመሰብሰቡ ባሻገር የአሽከርካሪውን ባህሪ ይቀይራል ተብሏል፡፡ የአሽከርካሪውን እያንዳንዱን ስህተት ሲስተሙ መዝግቦ ስለሚያስቀር ጥቃቅን የሚባሉ ስህተቶችን ጭምር ላለመሥራት ጥንቃቄ እንዲያደርግ ያስችላል ሲሉ ቀዳማዊ (ኢንጂነር) አክለዋል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ለሰው ልጅ መብት መከበር ስናወራ 75 ዓመት ሞላን!

በገነት ዓለሙ ዓለም ስለሰብዓዊ መብቶች ሲያወራ፣ ሲምል፣ ሲገዘት፣ ሲፈጠም፣ ቃል...

ካልተማከለ የካፒታል ገበያ ወደ ዘመናዊና የተደራጀ የሰነደ ሙዓለ ንዋዮች ገበያ

በእሱፈቃድ ተረፈ በአገራችን የካፒታል ገበያ አዋጅ መውጣትን ተከትሎ የተማከለ የሰነደ...

ለማይቀረው ምክክርና ድርድር እንዘጋጅ

በያሲን ባህሩ  የዘመናዊት ኢትዮጵያ ፖለቲካ ውዝግብ በትንሹ የአንድ ምዕተ ዓመት...

ደንብ አስከባሪዎች ደንብ ያክብሩ!

በአዲስ አበባ ከተማ ደንብ አስከባሪዎች፣ ሌሎች የፀጥታ አካላት፣ እንዲሁም...