ዱብ አለች ከታክሲ
ቁመቷን ወደደው
ቅላቷን ወደደው
አንደኛው ፀጉሯን…
አንደኛው እግሯን
እገሌ ደረቷን
እንትና ቅጥነቷን፣ ጣቷን፣ ማጅራቷን ወዘተ…ወዘተ
“ውበት” ብሎ ነገር…
በተመልካች ስሜት እንዲህ ከተለካ
ምን ስንጠብቅ ብንውል…
የምንወዳት እንጂ
የጋራችን ቆንጂት አትመጣም ለካ!!
(ፍቅር እና ሽንቁር፣ ዳንኤል ሥዩም መንገሻ፣ 2010 ዓ.ም.)
ዱብ አለች ከታክሲ
ቁመቷን ወደደው
ቅላቷን ወደደው
አንደኛው ፀጉሯን…
አንደኛው እግሯን
እገሌ ደረቷን
እንትና ቅጥነቷን፣ ጣቷን፣ ማጅራቷን ወዘተ…ወዘተ
“ውበት” ብሎ ነገር…
በተመልካች ስሜት እንዲህ ከተለካ
ምን ስንጠብቅ ብንውል…
የምንወዳት እንጂ
የጋራችን ቆንጂት አትመጣም ለካ!!
(ፍቅር እና ሽንቁር፣ ዳንኤል ሥዩም መንገሻ፣ 2010 ዓ.ም.)