Monday, December 11, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊበክልሎች የመምህራን ደመወዝ ለወራት ሳይከፈላቸው እንደሚቆይና እስከ 60 በመቶ አላግባብ እንደሚቆረጥ ተነገረ

በክልሎች የመምህራን ደመወዝ ለወራት ሳይከፈላቸው እንደሚቆይና እስከ 60 በመቶ አላግባብ እንደሚቆረጥ ተነገረ

ቀን:

የኢትዮጵያ መምህራን ማኅበር በጅግጅጋ ከተማ ባካሄደው 36ኛው ጉባዔ ላይ፣ በክልሎች የበርካታ መምህራን ደመወዝ ያላግባብ እንደሚቆረጥ በስፋት መነሳቱ ተገለጸ፡፡

የማኅበሩ ጉባዔ ለሦስት ተከታታይ ቀናት ሲካሄድ ከኦሮሚያ፣ ከደቡብ ኢትዮጵያ፣ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ፣ ከሲዳማና ከሌሎቸም ክልሎች መምህራን ደመወዛቸው ያላግባብ እንደሚቆረጥ በስፋት መነሳቱን በስብሰባው የተሳተፉ የማኅበሩ አመራሮች ለሪፖርተር ተናግረዋል፡፡

የደቡብ ኢትዮጵያ መምህራን ማኅበር ፕሬዚዳንት አቶ አማኑኤል ጳውሎስ ለሪፖርተር እንደገለጹት፣ በክልሉ እስከ 60 በመቶ የሚደርስ የመምህራን ደመወዝ እንደሚቆረጥና ለዚህም የሚሰጠው ምክንያት አሳማኝ አይደለም፡፡

የፌዴራል መንግሥት የዓመቱን በጀት ወደ ክልሎች ቢልክም፣ ክልሎች ለወረዳዎች እንደማይልኩ፣ በጀቱ ለማዳበሪያ ክፍያ ዋለ በሚል ወደ መምህራን ሳይደረስ እንደሚቀር መምህራን መናገራቸው ተሰምቷል፡፡ አንዳንዴ ደመወዝ ለበርካታ ወራት ሳይከፈላቸው እንደሚጠብቁና ግማሽ ደመወዝ ብቻ እንደሚከፈላቸውም ተነግሯል፡፡

መንግሥት በአንድ በኩል ስለትምህርት ጥራት እየተናገረ፣ በሌላ በኩል የመምህራን ደመወዝ እንደማይከፈል፣ የደረጃ ዕድገትና የትምህርት ማሻሻያ እንደማይደረግ በጉባዔው ላይ መነጋገሪያ ነበር ተብሏል፡፡ የማኅበሩ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባል እንዳሉት፣ በክልሉ በርካታ ወረዳዎች ውስጥ በሚገኙ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የመጀመሪያ ዲግሪ ያላቸው መምህራን ውስን መሆናቸውን፣ የበጀት እጥረቱ በከፍተኛ ሁኔታ ያጠቃቸው መምህራን በ2016 ዓ.ም በጀት ዓመት ለሚከናወን ሥራ ከ2017 ዓ.ም. በጀት መበደራቸው ተገልጿል፡፡

ማኅበሩ በጅግጅጋ ባከሄደው ወይይት የመምህራኑ ጉዳዩ በስፋት መነሳቱ የተጠቀሰ ሲሆን፣ ለዚህ ችግር ክልሎች ጉዳዩን በባለቤትነት ወስደው መፍትሔ እንዲፈልጉ የትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ (ፕሮፌሰር) መናገራቸውን፣ የኢትዮጵያ መምህራን ማኅበሩ ፕሬዚዳንት ዮሐንስ በንቲ (ዶ/ር) ለሪፖርተር ተናግረዋል፡፡

ከሚኒስትሩ ጋር በነበረው ውይይትም ማኅበሩ ከዚህ ቀደም በደብዳቤና በሪፖርት መልክ ሲያቀርባቸው የነበሩ ጥያቄዎችን፣ የትምህርት ሚኒስትሩን በአካል በማግኘት የመምህራኑን ሕይወት ሊቀይሩ የሚችሉ ጥያቄዎች ተነስተው ማብራሪያ ተሰጥቶባቸዋል ብለዋል፡፡

በሁሉም ክልሎች የሚገኙ መምህራን በጉባዔው የኑሮ ሁኔታቸው እንዲሻሻል ለመንግሥት ጥያቄ አቅርበው ሚኒስትሩ እንደ ሁኔታው እየታየ ወደፊት የመምህራኑን ሕይወት ሊቀይር የሚችል ሥራ ይከናወናል ማለታቸውን ዮሐንስ (ዶ/ር) ተናግረዋል፡፡ በመድረኩ ከተነሱ ጉዳዮች መካከል ከአፋር ክልል ተፈናቅለው ወደ ትግራይ ክልል የሄዱ 500 መምህራን ወደ ሥራቸው እንዲመለሱ ምክክር ተደርጎበታል ብለዋል፡፡

በ2015 ዓ.ም. ክረምት ተቋርጦ የነበረው የመምህራን የክረምት ትምህርት እንዲቀጥል ስምምነት ላይ መደረሱን ፕሬዚዳንቱ ተናግረዋል፡፡

የትምህርት ሚኒስቴር ጉባዔውን በተመለከተ ሚኒስትሩን ጠቅሶ በድረ ገጹ እንዳሠፈረው፣ አገሪቱ አሁን ላለችበት አገራዊ ችግር የትምህርት ሥርዓት መውደቁ ምክንያት በመሆኑ፣ የመምህራን ማኅበር ችግሩን ተነጋግሮ መፍታት እንዳለበትና ማኅበሩ የሙያውን ክብር ለመመለስ ከኅብረተሰቡ ጋር ወይይት በማድረግ ተጠያቂነት እንዲሰፍን እንዲያደርግ ጠይቀዋል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ለሰው ልጅ መብት መከበር ስናወራ 75 ዓመት ሞላን!

በገነት ዓለሙ ዓለም ስለሰብዓዊ መብቶች ሲያወራ፣ ሲምል፣ ሲገዘት፣ ሲፈጠም፣ ቃል...

ካልተማከለ የካፒታል ገበያ ወደ ዘመናዊና የተደራጀ የሰነደ ሙዓለ ንዋዮች ገበያ

በእሱፈቃድ ተረፈ በአገራችን የካፒታል ገበያ አዋጅ መውጣትን ተከትሎ የተማከለ የሰነደ...

ለማይቀረው ምክክርና ድርድር እንዘጋጅ

በያሲን ባህሩ  የዘመናዊት ኢትዮጵያ ፖለቲካ ውዝግብ በትንሹ የአንድ ምዕተ ዓመት...

ደንብ አስከባሪዎች ደንብ ያክብሩ!

በአዲስ አበባ ከተማ ደንብ አስከባሪዎች፣ ሌሎች የፀጥታ አካላት፣ እንዲሁም...