Sunday, December 10, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊየሳተላይት ማምጠቂያ ቦታዎችን ለመገንባት የአዋጭነት ጥናት ሊደረግ ነው

የሳተላይት ማምጠቂያ ቦታዎችን ለመገንባት የአዋጭነት ጥናት ሊደረግ ነው

ቀን:

ሳይንሳዊ መሥፈርቶችን ያሟሉ ሁለት የሳተላይት ማምጠቂያ ቦታዎች መለየታቸውንና የአዋጭነት ጥናት ሊደረግ መሆኑን፣ የኢትዮጵያ የስፔስ ሳይንስና ጆኦስፖሻል ኢንስቲትዩት አስታወቀ፡፡

የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር አቶ አብዲሳ ይልማ ለሪፖርተር እንደተናገሩት፣ ኢትዮጵያ በሳይንሳዊ መሥፈርት በግምገማና በትንተና የተለዩ ሁለት የሳተላይት ማምጠቂያ ቦታዎች አሉ፡፡

ለማምጠቂያ አመቺ የሆኑ ቦታዎች የት ነው የሚገኙት? የሚል ጥያቄ ቢያነሳላቸውም፣ ለጊዜው በተለያዩ ምክንያቶች ቦታዎችን ለመግለጽ እንዳማይፈልጉና ሌሎች አገሮች እንደሚያደርጉት አዋጭነት ጥናት አስፈላጊ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

በቀጣይ ለማምጠቅ አመቺ የሆኑ ቦታዎች ከመለየት ባሻገር ቦታዎቹን መገንባት ከፋይናንስ አዋጪነት አኳያ የሚደረገው ጥናት በሒደት ላይ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡

ለሳተላይት የማምጠቂያ ቦታዎች ወደ ሰሜን ኢትዮጵያ አለመሆናቸውን፣ ነገር ግን በዚያ አካባቢዎች ለአስትሮኖሚ ምልከታ አመቺ ቦታዎች መኖራቸውን ተናግረዋል፡፡

እነዚህ ቦታዎች ተራራማና ከፍታማ በመሆናቸው አመቺነታቸው ከሳተላይት ማምጠቂያነት ይልቅ ለአስትሮኖሚ ምልከታ አመቺነታቸው እንደ አገር በጥናት የተረጋገጡ ሥፍራዎች መሆናቸውን አስረድተዋል፡፡

ቦታዎቹ ከፍታቸው እስከ 4,000 ሜትር በመሆናቸው፣ ለአስትሮኖሚ ምልከታ አመቺና የሚመረጡ እንደሆኑና ለዚህ ሥራ ከተመረጡት መካከል በአማራ ክልል ላሊበላ አካባቢ አቡነ ዮሴፍ የሚባለው ሥፍራ እንደሚገኝበት ጠቅሰዋል፡፡

ይህ በእንዲህ እንዳለ ለኮሙዩኒኬሽንና ለብሮድካስቲንግ አገልግሎት የሚውል የትራንስፓደር ኪራይ የሚወጣው ዓመታዊ ወጪ የቅርብ መረጃ እንደሌላቸው፣ ይሁን እንጂ የኮሙዩኒኬሽን ሳተላይት ለማምጣት የቴክኒካልና የፊዚቢሊቲ ጥናት ተጠናቆ ተግባራዊ ለማድረግ ፋይንስ የሚገኝበትን ጊዜ እየተጠባበቁ እንደሚገኙ አቶ አብዲሳ ተናግረዋል፡፡

የኮሙዩኒኬሽን ሳተላይት ለማምጠቅ ከ300 ሚሊዮን ዶላር እስከ 350 ሚሊዮን ዶላር ወጪ እንደሚጠይቅና ፋይናንሱ ሲገኝ ወደ ሥራ እንደሚገባ፣ በአንድና በሁለት ዓመታት ጊዜ ውስጥ ይሆናል? አይሆንም? ለማለት እንደማይችሉ አስረድተዋል፡፡

የዚህ ዓይነት ሳተላይት ወደ ሕዋ ማምጠቅ ከኢትዮጵያ አልፎ የቀጣናውን አገሮች ጨምሮ እንደሚሸፍን፣ ይህም ለአገሮቹ ትራንስፓደር አገልግሎት በማከራየት የውጭ ምንዛሪ የሚገኝበት መሆኑን አስረድተዋል፡፡

በሁለት ዓመታት ጊዜ ውስጥ ወደ ህዋ የምትመጥቀዋ የመሬት ምልከታ ሳተላይት የቆይታ ጊዜ አምስት ዓመታት መሆኑን፣ ከዚህ ቀደም  ከነበሩ ሳተላይቶች በምሥል ጥራት ጭምር የተለየ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

የኮሙዩኒኬሽንና የአየር ፀባይ ሳተላይቶች በህዋ ላይ የሚቆዩበት ጊዜ ለአሥራ አምስት ዓመታት መሆኑን፣ ይህም የሆነው ከመሬት ያላቸው ርቀት እስከ 36 ሺሕ ኪሎ ሜትር ከፍ ማለታቸው የቆይታ ጊዜያቸው ረዘም እንዲል ምክንያት ሊሆን እንደሚችል አስረድተዋል፡፡

ይሁን እንጂ በቅርቡ ሥራ ያቆሙትን የኢትዮጵያ ሳተላይቶች ለመሬት ምልከታ አገልግሎት የሚውሉ በመሆናቸው፣ ከመሬት ያላቸው ርቀት 628 ኪሎ ሜትር እንደሚደርስ ገልጸዋል፡፡

በዚህ ከፍታ ላይ ከፍተኛ የሆነ የአትሞስፌር ወይም የሰበቃ ኃይል በመኖሩ ምክንያት፣ ሳተላይቷ በሒደት ጉልበት እንዲቀንስና ኦርቢታቸውን ጠብቀው መንቀሳቀስ እንዲያቅታቸው ምክንያት መሆኑን እስረድተዋል፡፡፡

እንደ ዋና ዳይሬክተሩ ገለጻ፣ አንዳንዴ የቆይታ ጊዜያቸው ከታሰበው በላይ የሚቆዩ ሳተላይቶች በሌሎች አገሮች መኖራቸው ታውቋል፡፡

እ.ኤ.አ. በ1984 ወደ ህዋ ያመጠቀችውን የመሬት ምልከታ ሳተላይት ላንድሳትን 5 በምሳሌነት ያነሱት አቶ አብዲሳ፣ የሳተላይቷ ቆይታ እ.ኤ.አ እስከ 2003 ድረስ ወይም ለ29 ዓመታት ማገልገሏን አንስተዋል፡፡

በአጠቃላይ በቅርቡ አነጋጋሪ የሆነችው ኢትዮጵያ ያመጠቀቻቸው የሳተላይት አገልግሎት መቆምን ያስረዱት ዋና ዳሬክተሩ፣ የሳተላይት የቆይታ ጊዜያቸው በተላኩበት ተልዕኮ፣ በሚገኙበት ከፍታ፣ ይዘውት የሄዱት የኃይል መጠንና ከሄዱ በኋላ በሚጋጥማቸው ሁኔታዎች ጭምር የሚወሰን መሆኑን ገልጸዋል፡፡

ከተላኩት ሳተላይቶች የተገኙት መረጃዎችና የሰጡት አገልግሎት ምንድን ናቸው ብሎ ለሪፖርተር ላነሳላቸው ጥያቄ፣ ምላሽ የሰጡ ዋና ዳይሬክተሩ፣ በቅርቡ ሥራቸውን ካቆሙት ሳተላይት እስካሁን 26.4 ቴራ ባይት የሚሆን የሳተላይት ምሥል መቀበል መቻሉንና ከግብርና ሥራ አኳያ መረጃው መተሐራ የሽንኮራ ተክልን ለመቆጣጠር እንዳገለገለ አስረድተዋል፡፡

ከሳተላይት በተገኘው መረጃ መሠረት አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ በመጠቀም የሰብል ምርታማነት ትንበያ ፕላን ፎርም ለማዘጋጀት ጥቅም ላይ መዋሉን ተናግረዋል፡፡

የማሽላ ምርታማነትን ለመተንበይ የሚያስችል ሞዴል ለማዘጋጀት የሳተላይት መረጃ ጥቅም ላይ መዋሉንና ከቱሪዝም አኳያ በጋሞና ደቡብ ኦሞ ዞን መደረሻዎችንና ተቋማትን የሚያሳይ ‹‹ቪዚት ኢትዮጵያ›› የሚባል መተግበሪያ ማልማት መቻሉን አስረድተዋል፡፡

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ የደን ሽፋን በተለይም ጥብቅ ደን ሽፋኑን ለመለየት የሚያስችል መረጃ መገኘቱን ከውኃማ አካላት አኳያ የተገኙ መረጃዎች መኖራቸውን ተናግረዋል፡፡    

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ለሰው ልጅ መብት መከበር ስናወራ 75 ዓመት ሞላን!

በገነት ዓለሙ ዓለም ስለሰብዓዊ መብቶች ሲያወራ፣ ሲምል፣ ሲገዘት፣ ሲፈጠም፣ ቃል...

ካልተማከለ የካፒታል ገበያ ወደ ዘመናዊና የተደራጀ የሰነደ ሙዓለ ንዋዮች ገበያ

በእሱፈቃድ ተረፈ በአገራችን የካፒታል ገበያ አዋጅ መውጣትን ተከትሎ የተማከለ የሰነደ...

ለማይቀረው ምክክርና ድርድር እንዘጋጅ

በያሲን ባህሩ  የዘመናዊት ኢትዮጵያ ፖለቲካ ውዝግብ በትንሹ የአንድ ምዕተ ዓመት...

ደንብ አስከባሪዎች ደንብ ያክብሩ!

በአዲስ አበባ ከተማ ደንብ አስከባሪዎች፣ ሌሎች የፀጥታ አካላት፣ እንዲሁም...