Monday, December 11, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
የሳምንቱ ገጠመኝየ ሳ ም ን ቱ ገ ጠ መ ኝ

የ ሳ ም ን ቱ ገ ጠ መ ኝ

ቀን:

ታክሲ ውስጥ ነኝ። የታክሲው ረዳት ላንቃው እስኪላቀቅ ይጮሀል። “ፒያሳ ፡ ጨረታ— ዊንግት… መዳሃንያለም… ፓስተር ጳውሎስ…“ ከጥቂት ደቂቃዎች በኋላ ታክሲው መንቀሳቀስ ጀመረ።

ብዙም ሳይጓዝ አንድ ጠና ያሉ ባለገብስማ ፀጉር አዛውንት ሮጥ ሮጥ ብለው እኔ ወደ ተሳፈርኩበት ታክሲ ዘልቀው  ከአጠገቤ ቁጭ አሉ። መቀመጫቸውን እያስተካከሉ በእጃቸው የያዟትን ከስራ ብዛት የተመናመነች አምስት ብር ወዲያው ለረዳቱ ዘረጉለት።

ረዳቱ ፊቱን ቅጭም እያረገ የት ኖት? አላቸው።  “ዊንጌት”  መለሱ፡፡  “10 ብር ነው!” አላቸው። ሰውዬው ኮስተር ብለው እንኳን ዊንጌት መድኃኔዓለምም አሥር አይደለም..” አሉት።

እየተነጫነጨ ተቀበላቸው። “ሽንኩርት 100 ብር ሲገባ መብታቹ አይታያችሁም…” አለ ረዳቱ ብስጭት በተቀላቀለበት አነጋገር። ታክሲ ውስ ያለው ተሳፋሪ በሙሉ  ፈገግ አሰኘው፡፡ ፈገግ ከማለት ውጭ ምን አማራጭ አለ!። አዛውንቱ ወደ እኔ  ዞረው ጨዋታ ጀመሩ።

“ኤድያ ለዚህ መድኃኒቱ ደርግ ነበር፣ ቃሊቲ አካባቢ የሚመረት ትልቅ ዳቦ ያከፋፍል የነበረ ዳቦ ቤት ሲቀብጠው የዳቦውን መጠን ቀንሶ አመረተ። የዛኔ ዳቦው ራሱ ምን ያህል ነበር ትልቅነቱ ዋጋውን ተወው፡፡ ታድያ በዚያ ጊዜ የዳቦውን መጠን የቀነሱ ነጋዴዎችንና አምራቾች መካከል የተወሰኑትን ደርግ  ሰብሰብ አድርጎ በአደባባይ አሠልፎ ረሸናቸው፡፡  ሕዝብ በረሃብ ከሚያልቅ እናንተን በጥይት ብሎ…” አሉ፡፡

መረሸንን እንደ ጀግንነት ሲያወሩ ግራ ገብቶኝ የሆ ነገር ጣል ላደር ስዘጋጅ፣ “ምን ይኼ ብቻ…” ብለው ቀጠሉ ። “በርበሬ በረንዳ በርበሬ ከሸክላ ጋር ቀላቅለው የሸጡ ነጋዴዎችን ሰብስቦ ረሸነ…›› እንዳሉ መውረጃቸው ደረሰና “ወራጅ!” አሉ። “ዕፎይ!” አልኩ ትንሽ ቢቆዩ ረዳቱንና ሾፌሩን የሚያስረሽኑ መስሎኝ። በእርግጥ የረዳቱ ከሕግ አግባብ ውጪ ተጨማሪ ሒሳብ ቢጠይቅም ንግግሩ ግን በቀላሉ ከአዕምሮዬ ሊጠፋ አልቻለም፡፡

አሁን ያለው የሸቀጦችና የአትክልት ዋጋ ንረት ስናየው ሰሞኑን ሯጮቻችን ካስመዘገቡት ሪከርዶች ጋር የሚተናነስ አይመስልም። ንረቱ ወደ ማይክሮ ሰከንድ እየተጠጋ ይመስላል። “ሽንኩርት ስንት ነው?” ብለህ ሳትጨርስ የሚጨምርበት ሁኔታ ነው ያለው።

በተለይ የነዳጅ ጭማሪው በየወሩ እንደሚዘለው የምግብና የሸቀጣ ሸቀጥ ዋጋም ሩጫውን ጨምሯል በዚህም ህዝቡ ጭማሪውን እየሰማ “ወይ ጉድ!”  ከማለት በቀር ምንም ጥያቄ ሲያቀርብ አይሰማም።

ለዚህም ይመስላል ረዳቱ ጣል ያረጋት አነጋገር ከአዕምሮዬ ያልጠፋችው ሳይበላ አይኖር ታድያ ምን ይደረግ”’ ያላት፡፡ የኢትዮጵያ የምግብ እህል ዋጋ ግሽበት 28.2 በመቶ መድረሱን መንግሥት እየገለጸ እንደሚገኝና ይህም እያደገ እንጂ እየቀነሰ እንደማይሄድ ነው ያብራራው።

ከጥቂት ዓመታት በፊት ሃያና ሃያ አምስት ብር የነበረው የፓስታ ዋጋ በሦስት እጥፍ ጨምሮ ሰባና ሰማንያ ብር መግባቱ ያውም ፍጥነቱ፡፡  “ማይክሮ ሰከንድ” ያልኩትን እንዳትዘነጉ አሁን ይሄኔ መቶ ገብቶ ሊሆን ይችላልና!!” ዘይገርም ነገር ነው።

ሰሞኑን ገበያን ያረጋጋሉ ተብሎ በመንግስት ወደ ተቋቋሙት የሸማቾች ኅብረት ሥራ ማኅበራት መካከል ወደ አንዱ ጎራ ብዬ ነበር። አንዳንድ የምግብ እህሎች ዋጋ እየጠየቅሁ ሳደርቃት ግርም ያላት ሻጯ ምክር ብጤ ጣል አረገችልኝ።

“የወዳጅነቴን ልንገርህ፣ ፓስታ 59 ብር ነው፡፡ አሁን እንዲያውም ከሦስት በላይ እንዳትሸጡ ተብለናል፣ ከትናንት ወዲያ 55 ብር የነበረው አራት ብር ጨምሮ 59 ብር ገብቷል። እና ሳይረፍድብህ አሁን ብትገዛ ይሻላል፡፡ ተመልሰህ ስትመጣ ሊጨምር ስለሚችል ማለቴ ነው…” ብላ  ሳቋን ለቀቀችው።

“ቆይ ግን እናንተ ዋጋውን በመቀነስ ገበያውን እንድታረጋጉ አይደል እንዴ የተፈጠራችሁት…” አልኳት። ‘”ወይ ማረጋጋት ልጄ እኛም ልንረጋጋ አልቻልንም፡፡ የዛሬ ሳምንት ያስገባነው ዕቃ ሳያልቅ ጭማሪው ይመጣና ራሱኑ ዋጋ ጨምረን እንድንሸጥ ስለምንታዘዝ አዲሱና አሮጌው ዋጋ እየተምታታብን እኛን ራሱ አላረጋጋ ብሎን ተቸግረናል…” ብላኝ እርፍ፡፡

ከሸማቾቹ ተሻግሬ ፊት ለፊት በቅርቡ ወደተከፈተው የአትክልት መሸጫ ማእከል ዘለቅሁ። በተንጣለለው ጊቢ ውስጥ አትክልትና ፍራፍሬ በብዛት ተደርድሯል፡፡

ወደ አንዱ ነጋዴ ቀረብ ብዬ የተለመደ ጥያቄዬን አቀረብኩ፡፡

 “ቲማቲም ስንት ነው!” 

“ቀንሷል 4 !” አለኝ፡፡

 “ሽንኩርቱስ!“ አስከተልኩ፡፡

“እሱ ያው ነው 90!” አለኝ።

አንዳንዴ ዝም ብለህ ጠይቀህ መሄድ መቼም ያሳፍር የለ፡፡  “ሁለት ኪሎ ሽንኩርት መዝንልኝ…” ስለው ቆፍጠን ብሎ “ከአምስት ኪሎ በታች አይሸጥም!” አለኝ።

ማለፊያ መለያያ አገኘሁና ወደ አቮካዶ መሸጫ ሥፍራ አመራሁ። የሚያማምሩ አቮካዶዎች ገና ሳይወርዱ በአይሱዙ ላይ ሆነው እየተሸጡ አስተዋልኩና “አንድ ሁለት ሦስት ኪሎ ትሸጡ ይሆን?” ስል ጠየኩ:: ሻጩ ሳቅ ብሎ “ከ25 ኪሎ በታች አይሸጥም” አለኝ፡፡

“ወይ ገበያ ማረጋጋት” መንግሥት በየአካባቢው ለንግድ ሥራ ዓይን የሆኑ ሥፍራዎች ላይ ገበያ ያረጋጋሉ በሚል ያቋቋማቸው መገበያያዎች ከአምስትና ከሃያ ኪሎ በታች አይሸጥም ካሉ፣ ገበያ ለማረጋጋት ሳይሆን የተሰቀለውን ዋጋ ለማርጋት የተቋቋሙ ሆነዋል አትሉኝም፡፡                                                             

 (ሚስባህ አወል፣ ከአዲስ አበባ)

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ለሰው ልጅ መብት መከበር ስናወራ 75 ዓመት ሞላን!

በገነት ዓለሙ ዓለም ስለሰብዓዊ መብቶች ሲያወራ፣ ሲምል፣ ሲገዘት፣ ሲፈጠም፣ ቃል...

ካልተማከለ የካፒታል ገበያ ወደ ዘመናዊና የተደራጀ የሰነደ ሙዓለ ንዋዮች ገበያ

በእሱፈቃድ ተረፈ በአገራችን የካፒታል ገበያ አዋጅ መውጣትን ተከትሎ የተማከለ የሰነደ...

ለማይቀረው ምክክርና ድርድር እንዘጋጅ

በያሲን ባህሩ  የዘመናዊት ኢትዮጵያ ፖለቲካ ውዝግብ በትንሹ የአንድ ምዕተ ዓመት...

ደንብ አስከባሪዎች ደንብ ያክብሩ!

በአዲስ አበባ ከተማ ደንብ አስከባሪዎች፣ ሌሎች የፀጥታ አካላት፣ እንዲሁም...