Sunday, December 10, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ዜናማንንም አናጠቃም!

ማንንም አናጠቃም!

ቀን:

የኢትዮጵያ የመከላከያ ሠራዊት የተመሠረተበትን 1900 ዓ.ም. መሠረት በማድረግ በየዓመቱ ጥቅምት 15 ቀን የመከላከያ ሠራዊት ቀን እንዲከበር በሕግ ተወስኗል። ይህንን መሠረት አድርጎም የመከላከያ ሠራዊቱ የተመሠረተበት 116ኛውን የመከላከያ ሠራዊት ቀን ባለፈው ሐሙስ ጥቅምት 15 ቀን በአዲስ አበባ መስቀል አደባባይ አክብሯል።

ማንንም አናጠቃም! | Ethiopian Reporter | ሪፖርተር በዕለቱም የአገሪቱ የጦር ኃይሎች ዋና አዛዥና ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድን (ዶ/ር) ጨምሮ የአገሪቱን ብሔራዊ ደኅንነት የሚመሩ ከፍተኛ በለሥልጣናት ተገኝተዋል። በምስሉ ላይ በግራ ጥግ የሚታዩትም የአገሪቱ የጦር ኃይሎች ዋና አዛዥና ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድና የመከላከያ ሠራዊት ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ ሲሆኑ፣ በስተቀኝ በኩል ደግሞ የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት (የአገሪቱ የስለላ ተቋም) ዋና ዳይሬክተር አቶ ተመስገን ጥሩነህና የመከላከያ ሠራዊቱ ምክትል ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ጄኔራል አበባው ታደሰ ናቸው። በምስሉ ላይ በጉልህ ከሚታዩት በስተጀርባ የክልል መንግሥታት ርዕሰ መስተዳደሮችና የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው የአፍሪካ አገሮች ወታደራዊ አመራሮች ናቸው። በዚህ የመከላከያ ሠራዊት ቀን ክብረ በዓል ላይም መከላከያ ሠራዊቱ እንደ አዲስ የታጠቃቸውን ዘመናዊ የጦር መሣሪያዎች የሚያሳይ ወታደራዊ ትርዒት ያቀረበ ሲሆን፣ የአገሪቱን የመከላከያ ሠራዊትና የፀጥታ ተቋማት የሚመሩት ባለሥልጣናት፣ ሚኒስትሮችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶችም ትዕይንቱን በአንክሮ ሲከታተሉ ነበር።

ማንንም አናጠቃም! | Ethiopian Reporter | ሪፖርተር ሪፖርተር ባደረገው የምስል ማጣሪያ በወታደራዊ ትዕይንቱ ላይ ከቀረቡት ዘመናዊ የጦር መሣሪያዎች መካከል በርከት ያሉት ከሩሲያ ምርቶች ጋር በእጅጉ የሚመሳሰሉ ከምድር ወደ አየር የሚወነጨፉ የተለያዩ የአየር ጥቃት መከላከያ ሚሳኤሎች፣ የተለያዩ መጠን ያላቸው ሮኬቶችን የተሸከሙ ማስወንጨፊያ ተሽከርካሪዎች፣ ረዥም ርቀት የሚመቱ መድፎችና ብረት ለበስ ታንኮች ይገኙበታል። በተጨማሪም፣ ከሦስት ዓመት በፊት በመንግሥት የቴሌቪዥን ጣቢያዎች ታይቶ የነበረው ሩሲያ ሰራሹ ፓንሲር (Pantsir) ፀረ-አውሮፕላን መድፍና ሚሳኤሎች በአንድ ላይ የተገጠሙበት መላውን የአገሪቱን የአየር ክልል መቃኘትና እስከ 36 ኪሎ ሜትር ርቀት ያሉ ዒላማዎችን መምታች የሚችል የአየር ጥቃት መከላከያ ሥርዓት በወታደራዊ ትዕይንቱ ላይ ከተስተዋሉት መካከል ይገኝበታል። በዕለቱ ከተስተዋሉት ዘመናዊ የጦር መሣሪያዎች መካከል በዓይነቱ ልዩና ከዚህ ቀደም ለዕይታ ቀርቦ የማያውቀው ተንቀሳቃሽ የኤሌክትሮኒክ ውጊያ መሣሪያ (mobile electronic warfare system) ነው። ይህ መሣሪያ “Kraukha-4” ከተሰኘው የሩሲያ ምርት ጋር በእጅጉ የሚመሳሰል ሲሆን፣ ከተቃራኒ ኃይል አውሮፕላኖችና ሄሊኮፕተሮች እንዲሁም የራዳር ጣቢያዎች የሚመነጩ ሞገዶችን በመመርመር ከለየ በኋላ ከፍተኛ ሞገድ በመልቀቅ ዒላማቸውን ለማዛበት ጥቅም ላይ እንደሚውል መረጃዎች ያመለክታሉ። አገሮች ወታደራዊ ትርዓቶችና የጦር መሣሪያ ትዕይንቶችን ከሚያካሂዱባቸው መሠረታዊ ምክንያቶች መካከል ዋነኛው ወታደራዊ አቅምን በማሳየት ጦርነትን አስቀድሞ ለመከላከል ነው። ጥቅምት 15 በአዲስ አበባ ከተማ በተካሄደው ወታደራዊ ትዕይንት ላይ የተገኙት የአገሪቱ የጦር ኃይሎች ዋና አዛዥና የአገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) ባደረጉት ንግግር፣ የኢትዮጵያ የመከላከያ ኃይል በየትኛውም ጊዜ ማጥቃትን ዓላማ አድርጎ ሠርቶ እንደማያውቅ፣ ሠራዊቱ እንደስያሜው ሁሉ ዓላማውም መከላከል ብቻ አንደሆነ በመጠቆም፣ አሁንም ማንንም አናጠቃም፤›› ብለዋል። ከቅርብ ጊዜ ጀምሮ በአንዳንድ ጉዳዮች ላይ ውይይት ያስፈልጋል (በባህር በር ጉዳይ) የሚል ጥያቄ በመነሳቱ ወረራ ሊካሄድ ይችላል የሚል ሥጋት በአንዳንድ ወዳጆች ዘንድ መፈጠሩን የተናገሩት ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ፣ ‹‹በዚህ በተከበረ ቀን መግለጽ የምፈልገው ኢትዮጵያ በኃይልና በወረራ ማሳካት የምትፈልገው አንዳች ነገር የለም። ለጋራ ጥቅም፣ ዕድገትና ብልፅግና ሁሉንም አሸናፊ በሚያደርጉ ጉዳዮች ከወንድሞቻችን ጋር ተወያይተን የጋራ ጥቅም የምናስከብር እንጂ በኃይል ወንድሞቻችን ላይ ቃታ የማንስብ አንደሆነ በአጽንኦት ላረጋግጥላችሁ እወዳለሁ፤›› ብለዋል። ይሁን እንጂ መከላከያ ሠራዊቱ ዘመኑን የዋጀ መሆን አለበት ብለዋል። መከላከያ ሠራዊቱ ባለበት የሚቆም ሳይሆን ዘመናዊ ትጥቅና አስተሳሰብ ያለው ሠራዊት ሆኖ ራሱን መገንባት እንዳለበት አሳስበዋል። ‹‹አሁን ያለንበት ዘመን ለግመታ የማይመችና ከየት እንደሚነሳ የማይታወቅ ሰፋፊ ችግር የሚያጋጥምበት በመሆኑ መፍጠን መፍጠርና ዘመንን መዋጀት ያስፈልጋል፤›› ብለዋል።

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ለሰው ልጅ መብት መከበር ስናወራ 75 ዓመት ሞላን!

በገነት ዓለሙ ዓለም ስለሰብዓዊ መብቶች ሲያወራ፣ ሲምል፣ ሲገዘት፣ ሲፈጠም፣ ቃል...

ካልተማከለ የካፒታል ገበያ ወደ ዘመናዊና የተደራጀ የሰነደ ሙዓለ ንዋዮች ገበያ

በእሱፈቃድ ተረፈ በአገራችን የካፒታል ገበያ አዋጅ መውጣትን ተከትሎ የተማከለ የሰነደ...

ለማይቀረው ምክክርና ድርድር እንዘጋጅ

በያሲን ባህሩ  የዘመናዊት ኢትዮጵያ ፖለቲካ ውዝግብ በትንሹ የአንድ ምዕተ ዓመት...

ደንብ አስከባሪዎች ደንብ ያክብሩ!

በአዲስ አበባ ከተማ ደንብ አስከባሪዎች፣ ሌሎች የፀጥታ አካላት፣ እንዲሁም...