- ለምንድነው እንደዚያ ያሉት? አስቸግሮ ነው?
- እንደዚያ እንኳን አይደለም።
- በምን ምክንያት ነው ታዲያ?
- በሲቪክ ትምህርት ላይ ጥሩ አይደለም ነው የሚሉት።
- በሲቪክ ትምህርት ብቻ ነው?
- እንደዚያ ነው ያሉኝ።
- እንዴት?
- በክፍል ውስጥም፣ እንዲሁም ሰሞኑን በነበረው ፈተና ላይ ጥሩ እንዳልነበር ነው የነገሩኝ።
- ስለፈተናው የነገሩሽ ነገር አለ?
- አዎ። ስለ ገዥ ፓርቲ ተግባርና ኃላፊነት አስረዳ ተብሎ የሰጠው ምላሽ ቤተሰብ ድጋፍና ክትትል እንደማያደርግለት ያሳያል ነው የሚሉት።
- እንዴት?
- አንተም አልፎ አልፎ እንኳን ልታስጠናው አትሞክርም።
- ና እስኪ ወዲህ አንተ፡፡ ስለገዥ ፓርቲ ተግባርና ኃላፊነት አታውቅም።
- ኧረ አውቃለሁ።
- በዚህ ትምህርት ላይማ ጎበዝ መሆን አለብህ፣ እኔን እንዳታሳፍረኝ።
- እሺ።
- በል ና ወዲህ ላስረዳህ፡፡
- እሺ ዳድ፡፡
- ይኸውልህ …የአንድ ገዥ ፓርቲ ተግባርና ኃላፊነት ምንድነው ከተባልክ አገር መምራት ብለህ ነው መመለስ ያለብህ።
- አውቃለሁ።
- ታዲያ ለምን እንደዚያ ብለህ አልመለስክም?
- ብያለሁ።
- ታዲያ ምን አድርግ ነው የሚሉት? ትክክለኛ መልስ እኮ ነው የሰጠው?
- ግን ጥያቄው በዝርዝር አስረዳ የሚል ስለነበር ሌሎች መልሶችንም ጽፌያለሁ።
- አገር መምራት ከሚለው ሌላ መልስ ጽፈሃል?
- አዎ።
- ምን ምን አልክ?
- ምን ነበር ያልኩት … አዎ አስታወስኩት።
- እስኪ ንገረኝ?
- ሥልጠና መስጠት።
- ምን! … ሥልጠና መስጠት ነው ያልከው?
- አዎ!
- ወይ ጉድ…
- ተሳስቻለሁ እንዴ ዳድ?
- ቆይ እስኪ ሌላስ ምል አልክ?
- * ስለጠና ከሚለው ሌላ …?
- እ…. ሌላ ያልከው የለም?
- አለ።
- ምን አልክ?
- ምን ነበር ያልኩት …አዎ አስታወስኩት።
- ምን አልክ?
- ማጥናት።
- እ…?
- ተሳስቻለሁ እንዴ ዳድ?
- ስለ ገዥ ፓርቲ ሥልጣንና ተግባር እኮ ነው የተጠየቅከው?
- እኮ!
- ታዲያ ማጥናት እንዴት ይሆናል?
- ለምን አይሆንም ዳድ?
- እንዴት ይሆናል? እሺ ስለምንድነው የሚያጠናው አልክ?
- ስለ ተፈጥሮ።
- ምን…?
- ስለተፈጥሮና የሰውነት አካላት፡፡
- እ…?
- እንዴት እንደዚህ ልትል ቻልክ?
- ምነው? ተሳስቻለሁ እንዴ ዳድ?
- ቆይ… ማን ሲል ሰምተህ ነው?
- ማንም?
- ታዲያ ከየት አመጣኸው?
- ቴሌቪዥን ላይ አይቼ ነው።
- ምንድነው ያየኸው?
- ሥልጠና ሲሰጥ።
- እ…?
- ማሚ …ትላንት በቴሌቪዥን ሥልጠና ሲሰጥ ተላልፎ የለ?
- አዎ።
- እና እዚያ ላይ ሲወራ አልሰማሽም?
- ምን ሲወራ?
- ስለ ውኃና ስለ የሰውነት አካላት?
- በይ ይህንን ቴሌቪዥን ዝጊልኝ።
- Advertisment -
- Advertisment -