Monday, December 11, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊበሩብ ዓመት ከ700 በላይ ተቋማት ዕርምጃ ተወስዶባቸዋል

በሩብ ዓመት ከ700 በላይ ተቋማት ዕርምጃ ተወስዶባቸዋል

ቀን:

በኢትዮጵያ በምግቦች፣ በመድኃኒቶችና በመጠጦች ውስጥ ባዕድ ነገሮችን ከልሰው የሚሸጡ ግለሰቦችም ሆኑ ተቋማት በርካታ መሆናቸው በተደጋጋሚ ይነገራል፡፡ ተቋማቱ ተገቢ ቅጣት እንዲያገኙ መንግሥት እየሠራ ቢሆንም፣ ችግሩ ሥር የሰደደና ለያዥ ለገናዥ የከበደ መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምግብና መድኃኒት ቁጥጥር ባለሥልጣን ሪፖርት ያሳያል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የምግብና የመድኃኒት ቁጥጥር ባለሥልጣን የ2016 በጀት ዓመት የአንደኛ ሩብ ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርቱን ቅዳሜ ጥቅምት 10 ቀን 2016 ዓ.ም. አቅርቧል፡፡

የበጀት ዓመቱ የሩብ ዓመት ሪፖርቱን ያቀረቡት የባለሥልጣኑ ዕቅድና በጀት ዳይሬክተር አቶ አስመላሽ ደርጋሶ እንደገለጹት፣ ባለሥልጣኑ በአብዛኛው ጥሩ አፈጻጸም ነበረው፡፡

ብልሹ አሠራርን ለማምከን ከተሠሩ ሥራዎች መካከል የቢሮ ሠራተኛ በባሉጉዳይ ተሽከርካሪ እንዳይሠራ፣ በትርፍ ጊዜ ለግል ተቋማት እንዳያገለግል ወጥ አሠራር ማስቀመጥ የሚሉት ይገኙበታል፡፡

እንደ አቶ አስመላሽ፣ በሩብ ዓመቱ በጤና ተቋማት በተደረገ ቁጥጥር ከተገኙ ክፍተቶች መካከል፣ የተሰጣቸውን ግብረ መልስ ሰንደው አለማስቀመጥ፣ ግብረ መልሱን አለማየትና ክፍተቶቻቸውን አለማስተካከል፣ አመድ መቅበሪያ ቦታ አለማዘጋጀት፣ የግዥ ደረሰኝ በወቅቱ አለማቅረብ፣ በጤና ተቋማት ውስጥ የአገልግለት ጊዜያቸው ያለፈባቸው መድኃኒቶች መገኘት፣ በመድኃኒት ችርቻሮ ተቋማት መሪ ባለሙያ ያለመኖር ችግሮች ታይተዋል፡፡

ክፍተታቸውን ባላሻሻሉና ከኅብረተሰበቡ በቀረቡ ጥቆማዎች፣ ጉድለት በተገኘባቸው 18 የግል ድርጅቶችና የመንግሥት ጤና ተቋማት ዕርምጃ ተወስዷል፡፡

ለ31 መድኃኒት ችርቻሮ ድርጅቶች የጽሑፍ ማስጠንቀቂያ የተሰጠና በጊዜያዊነት የማሸግ ሥራ የተሠራ ሲሆን፣ የብቃት ማረጋገጫ የተሰረዘባቸውም እንዳሉ ሪፖርቱ ይጠቁማል፡፡

በምግብና ጤና ነክ ተቋማት ውስጥ ከታዩ ችግሮች መካከል፣ በተቋማቱ የፍሳሽ መስመር አለመኖር፣ የፍሳሽ አወጋገድ ላይ በኅብረተሰቡ በቂ ግንዛቤ አለመኖር፣ በተቋማት ሴፕቲክ ታንከር አለመኖር፣ አንዳንድ ተቋማት ፍሳሽ ወደ መንገድ መልቀቅ፣ የምግብ ማዘጋጃ ክፍል ጭስን ወደ መኖሪያ አካባቢ መልቀቅ፣ ሕገወጥ ዕርድ፣ ደካማ የቆሻሻ አያያዝና አወጋገድ የመጠቀሚያ ጊዜ ያለፈባቸው ምግብና መጠጥ መገኘት፣ ከባዕድ ነገር የተቀላቀሉ ምግቦች በገበያ መገኘታቸውም ይጠቅሳሉ፡፡  

ባለሥልጣኑ ባደረገው ፍተሻ በ734 ተቋማት ላይ ዕርምጃ የወሰደ ሲሆን፣ 1,248,500 ብር የሚያወጡ ወደ ኅብረተሰቡ ቢሠራጩ የጤና እክል የሚፈጥሩ ምግቦች፣ መጠጦችና የምግብ ማብሰያ፣ ማቅረቢያና ማሸጊያ መሣሪያዎች መወገዳቸውን ዳይሬክተሩ አስረድተዋል፡፡

235 ኪሎ ግራም የአገልግሎት ጊዜ ያለፈባቸው መድኃኒቶች የተወገዱ ሲሆን፣ እነዚህ መድኃኒቶች በገንዘብ ሲተመኑ 2,540,000 ብር የሚያወጡ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

በሪፖርቱም ለ303 የጤና ነክ ማምረቻ፣ ማከፋፈያና አገልግሎት ሰጪ ተቋማት አዲስ የብቃት ማረጋገጫ ለመስጠት ዕቅድ ተይዞ 92 በመቶ ሊሳካ መቻሉ ቀርቧል፡፡

በሪፖርቱ ከቀረቡት የምግብና የውኃ ናሙና ምርመራ ይገኙበታል፡፡ በዚህም 55 የምግብና መጠጥ ተቋማት የምግብ ናሙና ለማስመርመር ዕቅድ ተይዞ በ37ቶቹ መከናወኑን ጠቁመዋል፡፡

ከታዩ ድክመቶች መካከል ባለሥልጣኑ ያሉትን ተቋማት በሚፈለገው መልክ፣ ብቃትና ቁጥጥር ማድረግ አለመቻል፣ የመረጃ ልውውጥ ፈጣን አለመሆን፣ የተለያዩ የምግብና የውኃ ናሙናዎችን ማስመርመር አለመቻል እንዲሁም የመረጃ አያያዝ ችግር መኖር ይገኝበታል፡፡

የባለሥልጣኑ ዋና ሥራ አስኪያጅ ወ/ሮ ሙሉእመቤት ታደሰ እንደገለጹት፣ በሕገወጥ መንገድ የተሰማሩ ተቋማትን ተከታትሎ ዕርምጃ ለመውሰድ ተቋሙ እየሠራ ነው፡፡

ከዚህ በፊት የነበሩ ፖሊሲዎችን እንደ አዲስ ለማሻሻል ተቋሙ እየሠራ እንደሆነ ገልጸው፣ የሕክምና ተቋሞች ያሉባቸውን ክፍተቶች ለመፈተሽ፣ ከዚህ በፊት ከነበረው አሠራር በተሻለ ሁኔታ የሚሠራ መሆኑን አብራርተዋል፡፡

ከፍተኛ ስህተት የሠሩ የሕክምና ባለሙያዎች ጠጠር ያለ ቅጣት እንዲያገኙ እየተሠራ ነው ያሉት ዋና ሥራ አስኪያጇ፣ ይህም በተለያዩ የማጭበርበር ዘዴ የተሰማሩ ሰዎች እንዲታቀቡ ትልቅ አስተዋጽኦ ይኖረዋል ብለዋል፡፡    

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ለሰው ልጅ መብት መከበር ስናወራ 75 ዓመት ሞላን!

በገነት ዓለሙ ዓለም ስለሰብዓዊ መብቶች ሲያወራ፣ ሲምል፣ ሲገዘት፣ ሲፈጠም፣ ቃል...

ካልተማከለ የካፒታል ገበያ ወደ ዘመናዊና የተደራጀ የሰነደ ሙዓለ ንዋዮች ገበያ

በእሱፈቃድ ተረፈ በአገራችን የካፒታል ገበያ አዋጅ መውጣትን ተከትሎ የተማከለ የሰነደ...

ለማይቀረው ምክክርና ድርድር እንዘጋጅ

በያሲን ባህሩ  የዘመናዊት ኢትዮጵያ ፖለቲካ ውዝግብ በትንሹ የአንድ ምዕተ ዓመት...

ደንብ አስከባሪዎች ደንብ ያክብሩ!

በአዲስ አበባ ከተማ ደንብ አስከባሪዎች፣ ሌሎች የፀጥታ አካላት፣ እንዲሁም...