Sunday, July 21, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ኪንና ባህልየኢትዮጵያ ፊልም ፌስቲቫል በለንደን

የኢትዮጵያ ፊልም ፌስቲቫል በለንደን

ቀን:

በዳንኤል ንጉሤ

አራተኛው የኢትዮጵያ ፊልም ፌስቲቫል በለንደኑ ሪትዚይ ሲኒማ ጥቅምት 17 እና 18 ቀን 2016 ዓ.ም. በሀበሻ ቪው ቴክኖሎጂና መልቲሚዲያ አስተባባሪነት እንደሚካሄድ የድርጅቱ ሥራ አስፈጻሚና መሥራች ወ/ሮ ትዕግስት ከበደ ለሪፖርተር ገልጸዋል።

በፌስቲቫሉ ፀፀት እና ዝምታዬ የተሰኙ ሁለት የኢትዮጵያ ፊልሞች ለተመልካች ይቀርባሉ፡፡

የኢትዮጵያ ፊልም ፌስቲቫል በለንደን | Ethiopian Reporter | ሪፖርተር

ሀበሻ ቪው በአሜሪካ ቨርጂኒያ በ2008 ዓ.ም. የተቋቋመ ድርጅት ሲሆን፣ ከ2012 ዓ.ም. ጀምሮ በኢትዮጵያ ፈቃድ በማውጣት እየተንቀሳቀሰ መሆኑን ወ/ሮ ትዕግስት ጠቅሰው፣ ድርጅቱ የተቋቋመው በውጭ አገሮች የሚገኙ ኢትዮጵያውያን የአገራቸውን ፊልም የሚያዩበት አማራጭ ለመፍጠር መሆኑን አመልክተዋል፡፡ ድርጅቱ በተመሠረተበት ዓመት ‹‹ሀበሻ ቪው›› የተሰኘ አፕሊኬሽን በመክፈት ዳያስፖራው ለሦስት ዓመታት የኢትዮጵያን ፊልም በነፃ እንዲያይ አመቻችተው እንደነበር አስታውሰዋል።

ድርጅቱን ለማቋቋምና አፕሊኬሽኑን ለማበልፀግ በአጠቃላይ 2.5 ሚሊዮን ዶላር ፈጅቶብናል ያሉት ሥራ አስፈጻሚዋ፣ ‹‹የኢትዮጵያ ፊልም ኢንዱስትሪ ውስጥ ያሉ ፊልሞችን ከፍለን በመውሰድ አፕሊኬሽኑ ላይ በመጫን በውጪ አገር ያሉ ኢትዮጵያውያን ከፍለው የሚያዩበትን መንገድ አመቻችተናል፤›› ሲሉ ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ ፊልሞችን በፌስቲቫል ላይ በመውሰድ ማስመረቅና ማሳየት ከ2012 ዓ.ም. ጀምሮ በለንደን፣ ዋሽንግተንና ኒውዮርክ እንደጀመሩ ወ/ሮ ትዕግስት ጠቅሰው፣ ለመጀመሪያ ጊዜ ወስደው ያሳዩት ፊልም ‹‹ቁራኛዬ›› የተሰኘና በ2012 ዓ.ም. የተሠራ ባህላዊ ፊልም መሆኑን፣ በተከታዩ ዓመት በኮቪድ-19 ምክንያት ማሳየት ባይችሉም፣ በ2014 ዓ.ም. በሁለተኛው የለንደን ፌስቲቫል ላይ ድርድር፣ እንቆጣ፣ በድጋሚ ቁራኛዬ የተሰኙ ፊልሞችና አንበሳ የተሰኘ ዶክመንተሪ ፊልም በመውሰድ ማሳየታቸውን ገልጸዋል።

በዓምናው ሦስተኛው ፌስቲቫል ወቅትም ሦስት ፊልሞች ሒሩት አባቷ ማነው?፣ ሲነት እና ርዕስ ፈላጊ ለዕይታ በቅተዋል፡፡

በመጪው ሳምንት በለንደን ለሚካሄደው አራተኛው የኢትዮጵያ ፊልም ፌስቲቫል፣ ፀፀት የሚባል ከሠላሳ ዓመት በፊት የተሠራ ባለቀለም ፊልምና ዝምታዬ የተሰኘ በ2015 ዓ.ም. የተሠራ ፊልም እንደሚታዩ ወ/ሮ ትዕግስት ለሪፖርተር በሰጡት ቃለመጠይቅ ገልጸዋል።

የኢትዮጵያን ፊልሞች በውጪ አገር በእንደዚህ መልኩ ማሳየት የፊልም ኢንዱስትሪውን አነቃቅቶታል ያሉት ወ/ሮ ትዕግስት፣ አልፎ ተርፎም በአገር ውስጥ ተመልካች አጥተው የነበሩ ፊልሞች ከፌስቲቫሉ በኋላ ተወዳጅነታቸው የጨመሩ እንዳሉም ጠቅሰዋል፡፡

‹‹የአገራችንን የፊልም ስክሪፕቶችን በድርጅታችን በኩል በመውሰድ ከተለያዩ የውጭ አገር የፊልም ፕሮዳክሽን ካምፓኒዎች ጋር የመሥራት ዕቅድ አለን፤›› ያሉት ወ/ሮ ትዕግስት፣ የኢትዮጵያ ፊልሞች ኦስካር ላይ እንዲገቡና በዓለም አቀፍ ፊልም ዘርፍ ላይ ተሳታፊ ለማድረግ ጥረት እናደርጋለን ብለዋል።

በፊልም ኢንዱስትሪው ለሃያ ስምንት ዓመታት በመሥራት ዝናን ያገኘውና ዘንድሮ ከሚሄዱት ፊልሞች አንዱ በሆነው ዝምታዬ ላይ በትወና፣ በፋይናንስ እንዲሁም በፕሮዳክሽን የተሳተፈው ቴዎድሮስ ተሾመ በበኩሉ፣ ‹‹የአገራችንን ፊልሞች ለዓለም የማሳየት ዕድሎች ካገኘንና አቅማችንን ማሳየት ከቻልን ለፊልም ኢንዱስትሪያችን ጠቃሚ ነው፤›› ሲል ሐሳቡን ለሪፖርተር ገልጿል። አክሎም ፊልሞች ወደ ውጭ በወጡ ቁጥር በዚያ የሚኖሩት ኢትዮጵያውያን አገራዊ ፊልምን የማየት ፍላጎት ያነቃቃል ብሏል።

‹‹አብዛኞቹ የኢትዮጵያ ፊልሞች ኢትዮጵያዊነት የሚሸት ነገር የላቸውም በብዛት ከውጪ የተቀዱ ናቸው፤›› ያሉት ባለቅኔና ጸሐፊ ተውኔት አያልነህ ሙላቱ ናቸው፡፡ ለዚህም በዋነኝነት እንደ ችግር ያነሱት የፊልም ማሠልጠኛ አገራዊ ተቋም ባለመኖሩ ነው፡፡ በዚህም ምክንያት ጥሩ ባለሙያ ሊገኝ እንዳልተቻለ ገልጸው፣ መንግሥት ይኼንን ክፍተት መሙላት እንዳለበት አሳስበዋል።

የኢትዮጵያ ፊልሞች ወደ ውጪ አገር ሄደው የመታየት ዕድል ማግኘት መቻላቸው የኪነ ጥበብ ዓምዱን ከፍ ያደርገዋል ያሉት አያልነህ፣ ከሌሎች አገሮች ጋር የሚደረገው የልምድ ልውውጥ በባለሙያዎቹ ዘንድ ከፍተኛ የሞራል መነሳሳት እንደሚፈጥር ጠቅሰዋል።

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ኢትዮጵያዊ ማን ነው/ናት? ለምክክሩስ መግባባት አለን?

በደምስ ጫንያለው (ዶ/ር) የጽሑፉ መነሻ ዛሬ በአገራችን ውስጥ በተለያዩ አካባቢዎች ግጭቶችና...

ዴሞክራሲ ጫካ ውስጥ አይደገስም

በገነት ዓለሙ የዛሬ ሳምንት ባነሳሁት የኢሰመኮ ሪፖርት መነሻነትና በዚያም ምክንያት...

ኢትዮጵያ በምግብ ራሷን የምትችለው መቼ ነው?

መድረኩ ጠንከር ያሉ የፖሊሲ ጉዳዮች የተነሱበት ነበር፡፡ ስለረሃብ፣ ስለምግብ፣...

ደረጃውን የጠበቀ ስታዲየም በሌላት አገር ዘመናዊ ስታዲየም እየገነቡ ያሉ ክልሎች

አዲሱ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ዘመናዊ ስታዲየም ለማስገንባት ከ500 ሚሊዮን...