Monday, December 11, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ዝንቅሞኞቹ

ሞኞቹ

ቀን:

በድሮ ጊዜ ነው ጥንት፡፡ ሁለት ሞኝ ባልና ሚስት ነበሩ፡፡ ከዕለታት አንድ ቀን ዶሮ አረዱና ሚስትዮዋ ሠርታ ሊበሉ ሲሉ ለጥርሳቸው መጎርጎሪያ የሚሆን ሣር የሌለ መሆኑን ያስተውሱና ሊያመጡ ወደ ዱር ሔዱ፡፡ ወደ ዱር ሲሔዱ መንገድ ላይ አንድ ተማሪ አገኛቸው ተማሪውም፡-

‹‹ወዴት ትሔዳላችሁ?›› ሲል ጠየቃቸው፡፡

‹‹ዶሮ አርደን ሠርተን አስቀምጠን ለጥርሳችን መጎርጎሪያ ሳር ልናጭድ ነው››

‹‹ቤታችሁ የት ነው››

‹‹ያ እዚያ ማዶ እመንገዱ ዳር ያለው ነው›› ብለው ነግረውት ወደ ሳር አጨዳ ተጓዙ፡፡

ተሜም እቤታቸው ሔደና ዶሮ ወጣቸውን ግጥም አድርጎ በልቶ ጠፋ፡፡ ባልና ሚስት ሳራቸውን አጭደው ተሸክመው እቤት ደረሱና ቢያዩ የወጡ ድስት ባዶውን ሆኖ ዝንብ ወርሮታል፡፡ በዚህ ጊዜ ዶሮ ወጣቸውን ዝንብ ነው የበላው ብለው በማመን በቤቱ ውስጠ ውር ውር የሚለውን ዝንብ መግደል ጀመሩ፡፡ ዝንቦች በእንስራው፣ በምጣዱ፣ በማሰሮው ላይ ሲያርፉ እነሱን አገኛለሁ በማለት የቤቱን ዕቃ ሁሉ ሲያነክቱት ቆዩ፡፡ በመጨረቫ አንዲት ዝንብ እሴትዬዋ ግንባር ላይ አረፈች፡፡ በዚህ ጊዜ ሴትዬዋ ዝንቧ ተነስታ እንዳትበር ቀስ ብላ በምልክት ባልዋን ጠቆመችው፡፡ ሰውየውም በያዘው ቆመጥ አስተካክሎ ግንባሯን ሲላት ጊዜ ውኃ ሳትል አረፈች ይባላል፡፡

  • ዘሪሁን አስፋው ‹‹የስነ ጽሁፍ መሰረታውያን›› (1992)
spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ለሰው ልጅ መብት መከበር ስናወራ 75 ዓመት ሞላን!

በገነት ዓለሙ ዓለም ስለሰብዓዊ መብቶች ሲያወራ፣ ሲምል፣ ሲገዘት፣ ሲፈጠም፣ ቃል...

ካልተማከለ የካፒታል ገበያ ወደ ዘመናዊና የተደራጀ የሰነደ ሙዓለ ንዋዮች ገበያ

በእሱፈቃድ ተረፈ በአገራችን የካፒታል ገበያ አዋጅ መውጣትን ተከትሎ የተማከለ የሰነደ...

ለማይቀረው ምክክርና ድርድር እንዘጋጅ

በያሲን ባህሩ  የዘመናዊት ኢትዮጵያ ፖለቲካ ውዝግብ በትንሹ የአንድ ምዕተ ዓመት...

ደንብ አስከባሪዎች ደንብ ያክብሩ!

በአዲስ አበባ ከተማ ደንብ አስከባሪዎች፣ ሌሎች የፀጥታ አካላት፣ እንዲሁም...