እነዚህ ሦስት ቅርሶች ጠብቃቸው፡፡ የመጀመሪያው ፍቅር ነው፡፡ ሁለተኛው መካከለኛነት ሲሆን፣ ሦስተኛው ደግሞ በዓለም ላይ መቼም ቢሆን የመጀመሪያ አትሁን፡፡ በፍቅር ልበ ሙሉነትን ታገኛለህ፡፡ በመካከለኛነት የማመዛዘን ኃይል ይገበያል፡፡ ቀዳሚ ከመሆን በመቆጠብ መብሰልና ማስተዋል ይገኛል፡፡ ፍቅር ጀግንነት ካለ ኃይልን ማግኘት ይቻላል፡፡ ቀድሞ የሚሮጥ ቀድሞ ይጠፋል፡፡ በማጥቃት ጊዜ ፍቅር ኃይል ነው፡፡ በመከላከልም ጊዜ ምሽግ ነው፡፡ የፍቅር ስንቅ የታጠቀ አይጠፋም፡፡ (ታኦይዝም)
- አእምሮ ወንድምአገኘሁ ‹‹መረቅ›› (1965)