Monday, December 11, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ስፖርትየስፖርት ማደራጃ መተዳደሪያ ደንብ ሳያሟሉ ፌዴሬሽን ሊያቋቋሙ የነበሩ አካላት ታገዱ

የስፖርት ማደራጃ መተዳደሪያ ደንብ ሳያሟሉ ፌዴሬሽን ሊያቋቋሙ የነበሩ አካላት ታገዱ

ቀን:

  • ከሚኒስቴሩ የስፖርት ማደራጃ ጽሕፈት ቤት ዕውቅና አግኝተው ነበር

የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር የስፖርት ማኅበራት ማደራጃ መተዳደሪያ ደንብ የሚያዘውን ሳያሟሉና ዕውቅና ሳያገኙ ፌዴሬሽን ለማቋቋም ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ማኅበራት ላይ ዕገዳ መጣሉን አስታወቀ፡፡

የሚኒስቴሩን የስፖርት ማኅበራት ማደራጃ ዕውቅና አግኝተው፣ በፌዴሬሽንና በማኅበር ከተቋቋሙት ሦስት የቴኳንዶ ስፖርት ማኅበራት ውጭ፣ የቴኳንዶ ፌዴሬሽን ሊያቋቁሙ በነበሩ አካላት ላይ ዕገዳ መጣሉን ገልጿል፡፡

‹‹ወርልድ ፕሮ ቴኳንዶና ግሎባል ቴኳንዶ›› የተሰኙ ሁለት የስፖርት ማኅበራት በግለሰቦች አማካይነት ፌዴሬሽን ለማቋቋም ክልሎችን ለማሳመን ጥረት ሲያደርጉ እንደነበር ጠቅሰዋል፡፡

በሚኒስቴሩ ውሳኔ መሠረት የስፖርት ማኅበራት ስለሚያቋቁሙበት ሁኔታ ለመወሰን በወጣው መመርያ ቁጥር 907/2014 አንቀጽ 1(13) መሠረት የኢትዮጵያ ቴኳንዶ ፌዴሬሽን፣ የኢትዮጵያ ኢንተርናሽናል ቴኳንዶ ፌዴሬሽንና የኢትዮጵያ ዩናይትድ ቴኳንዶ ፌዴሬሽን ስፖርቶች በክልልና ከተማ አስተዳደር ተስፋፍተው ተግባራዊ እያደረጉ እንደሚገኙ ጠቅሶ፣ ከእነዚህ ውጪ የሚንቀሳቀሱት ሕጋዊ ዕውቅና የሌላቸው መሆኑን ጠቅሷል፡፡

በዚህም መሠረት በአገሪቱ ስፖርቱን ለማስፋፋት በብቸኝነት ከሚመሩት ሦስቱ ፌዴሬሽኖች ውጪ፣ አንዳንድ አካላት የቴኳንዶ ስፖርትን የተለያዩ ስያሜዎች በመስጠት ለማደራጀት እንቅስቃሴ ሲያደርጉ ደርሼባቸዋለሁ ሲል ያብራራል፡፡

ዕገዳ ከተጣለባቸው መካከል ‹‹ፕሮ ወርልድ ቴኳንዶ››፣ የተሰኘው የግለሰቦች ስብሰብ ለመጀመርያ ጊዜ ስድስት ዓይነት የማርሻል አርት ውድድር በኢትዮጵያ ለማሰናዳት ዕቅድ እንዳለውና ስፖርቱን ለመደገፍ ዓላማውን አንግቦ መምጣቱን ለፌዴሬሽኖቹ ማሳወቁ ተነግሯል፡፡

ከዚህ ጋር ተያይዞም ባለፈው ሐምሌ 19 ውድድሮችን ማሰናዳቱ ተጠቁሟል፡፡ ለመጀመርያ ጊዜ ባዘጋጀው የስድስት ዓይነት የማርሻል አርት ውድድር ለመካፈል ክለቦችና ማንኛውም ተወዳዳሪ ለምዝገባ 300 ብር መካፈሉ ተጠቁሟል፡፡

በዓለም አቀፍ ስፖንሰሮች አማካይነት ስድስት ዓይነት የማርሻል አርት ውድድሮችን በኢትዮጵያ ስፖርት አካዴሚ ያሰናዳው ሌጄንድ ማርሻል አርት የተሰኘው ተቋም፣ ከ900 በላይ ተወዳዳሪዎችን በክፍያ ማሳተፉ ተጠቅሷል፡፡

እንደ ሪፖርተር ምንጮች ከሆነ፣ ቀድሞ የቴኳንዶ ስፖርትን ለመደገፍና የውድድር ዕድሎችን ለማመቻቸት ወደ ኢትዮጵያ የመጣው ‹‹ሌጀንድ ማርሻል አርት›› ከውድድሩ መጠናቀቅ በኋላ በአዲስ መልክ ተደራጅቶና ‹‹ፕሮ ወርድልድ ቴኳንዶ›› የሚል ስያሜን ይዞ ፌዴሬሽን ሆኖ ለመቋቋም እንቅስቃሴ ጀምሯል፡፡

ከዚህም ባሻገር ፕሮ ወርልድ ቴኳንዶ በባህልና ስፖርት ሚኒስቴር ሥር በሚተዳደረው የስፖርት ማኅበራት ምዝገባ ድጋፍና ቁጥጥር መሪ ሥራ አስፈጻሚ አማካይነት የዕውቅና ደብዳቤ አግኝቶ በክልሎች እንቅስቃሴ ሲያደርግ እንደነበር ተገልጿል፡፡

በአንፃሩ አንድ የስፖርት ፌዴሬሽን ለማቋቋም አምስት ክልሎች፣ አሥር ክለቦች፣ የዳኞች ቁጥር፣ የባለሙያዎች፣ እንዲሁም የአሠልጣኞች ቁጥር መሟላት እንደሚጠበቅበት የማኅበራት ምዝገባ፣ ድጋፍና ቁጥጥር መተዳደሪያ ደንብ ይደነግጋል፡፡

ይሁን እንጂ ምንጮች ለሪፖርተር እንደሚያስረዱት ከሆነ፣ ሚኒስቴሩ የዕገዳ ደብዳቤ ከማውጣቱ አስቀድሞ ሁለቱ የቴኳንዶ ማኅበራት በስፖርት ማኅበራት ምዝገባ ድጋፍና ቁጥጥር መሪ ሥራ አስፈጻሚ አማካይነት ክልሎችና የከተማ አስተዳደሮች አስፈላጊውን ድጋፍ እንዲያደርጉ ደብዳቤ መጻፉ ጥያቄ አስነስቷል፡፡

ሌላው በባህልና ስፖርት ሚኒስቴር ዕገዳ የተላለፈበት፣ የኢትዮጵያ ግሎባል ቴኳንዶ በሚል ፌዴሬሽን ለማቋቋም ሲንቀሳቀስ የነበረ አደረጃጀት ነው፡፡

ከሚኒስቴሩ ግንቦት 1 ቀን 2015 ዓ.ም. የወጣው ደብዳቤ እንደሚያመለክተው፣ በአገር አቀፍ ደረጃ የግሎባል ቴኳንዶ ፌዴሬሽን ለማቋቋም እንዲያስችል፣ ከሌሎች ቴኳንዶ ስፖርቶች የሚለይበት ጥናት በማቅረብ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ውይይት ማድረጉን ያብራራል፡፡

ከዚህም በላይ የግሎባል ቴኳንዶ ፌዴሬሽን በቀጣይ ጊዜ ራሱን ችሎ እንደ አንድ ስፖርት ማኅበር የአገር አቀፍ ማኅበራት መመርያን ተከትሎ ለመደራጀት ስለሚፈልግ ሁሉም ክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች የድጋፍ ደብዳቤ እንዲጽፉ የሚያዝ ደብዳቤ ከስፖርት ማኅበራት ምዝገባ ድጋፍና ቁጥጥር መሪ ሥራ አስፈጻሚ ተልኳል፡፡

በዚህም መሠረት የተወሰኑ ክልሎችና አንድ ከተማ አስተዳደር የስፖርት ማኅበራት ስለሚቋቋሙበት ሁኔታ በወጣው መመርያ 50/2014 መሠረት የስፖርት ማኅበሩ የተቀመጡትን መሥፈርቶችን አሟልቶ ስለተገኘ የምስክር ወረቅት መስጠታቸው ተገልጿል፡፡

ሆኖም  የስፖርት ማኅበራት ምዝገባ ድጋፍና ቁጥጥር ሥራ አስፈጻሚ አማካይነት የተሰጠው የዕውቅና ደብዳቤ ‹‹ሕጋዊ አይደለም›› በማለት ሊቋቋሙ የነበሩትን የቴኳንዶ ስፖርት አደረጃጀቶች ማገዱን ሚኒስቴሩ አስታውቋል፡፡

በአንፃሩ ሚኒስቴሩ ከስፖርት አደረጃጀቶችና ፈቃድ ጋር በተያያዘ ወጥ የሆነ አሠራርን ላለመከተሉ አንዱ ማሳያ ለክልሎችና የከተማ አስተዳደሮች የሚላኩ ደብዳቤዎች የመናበብ ችግር ያለባቸው መሆኑ ይጠቀሳል፡፡

በኢትዮጵያ የስፖርት ሪፎርም ለማድረግ ሚኒስቴሩ ባስጠናው ጥናት መሠረት በማኅበር የተደራጁ ስፖርቶች ተሸጋሽገው ወደ ፌዴሬሽን እንዲጠቃለሉ ምክረ ሐሳብ መቅረቡ ይታወሳል፡፡   

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ለሰው ልጅ መብት መከበር ስናወራ 75 ዓመት ሞላን!

በገነት ዓለሙ ዓለም ስለሰብዓዊ መብቶች ሲያወራ፣ ሲምል፣ ሲገዘት፣ ሲፈጠም፣ ቃል...

ካልተማከለ የካፒታል ገበያ ወደ ዘመናዊና የተደራጀ የሰነደ ሙዓለ ንዋዮች ገበያ

በእሱፈቃድ ተረፈ በአገራችን የካፒታል ገበያ አዋጅ መውጣትን ተከትሎ የተማከለ የሰነደ...

ለማይቀረው ምክክርና ድርድር እንዘጋጅ

በያሲን ባህሩ  የዘመናዊት ኢትዮጵያ ፖለቲካ ውዝግብ በትንሹ የአንድ ምዕተ ዓመት...

ደንብ አስከባሪዎች ደንብ ያክብሩ!

በአዲስ አበባ ከተማ ደንብ አስከባሪዎች፣ ሌሎች የፀጥታ አካላት፣ እንዲሁም...