Monday, December 11, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊለስደተኞች የሚቀርበው ድጋፍ እየቀነሰ የጥገኝነት ጠያቂዎች ቁጥር መጨመሩ አሳሳቢ መሆኑ ተገለጸ

ለስደተኞች የሚቀርበው ድጋፍ እየቀነሰ የጥገኝነት ጠያቂዎች ቁጥር መጨመሩ አሳሳቢ መሆኑ ተገለጸ

ቀን:

  • ኢትዮጵያ ከአንድ ሚሊዮን በላይ ስደተኞችን እያስተናገደች ነው

ለስደተኞች የሚቀርበው ድጋፍ እየቀነሰ ባለበት ወቅት የጥገኝነት ጠያቂዎች ቁጥር በከፍተኛ መጠን መጨመሩ አሳሳቢ መሆኑን፣ የስደተኞችና ተመላሾች አገልግሎት አስታወቀ፡፡

የስደተኞችና ተመላሾች አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ጠይባ ሐሰን እንዳስታወቁት፣ በሶማሌላንድ በተከሰተ ግጭት በቅርቡ ከመቶ ሺሕ በላይ ስደተኞች ወደ ኢትዮጵያ ፈልሰው ገብተዋል፡፡ የስደተኞቹን መሠረታዊ ፍላጎት ማስተናገድ ቀላል አይደለም፡፡

በተመሳሳይ በሱዳን እየተካሄደ ባለው ጦርነት ከመቶ ሺሕ በላይ ስደተኞችን ወደ ኢትዮጵያ በመፍለሳቸውና ከፍተኛ ጫና በመፈጠሩ፣ ለጋሽ አገሮች የድጋፋቸውን መጠን እንዲጨምሩ ጥያቄ እንደቀረበላቸው ወ/ሮ ጠይባ ተናግረዋል፡፡

ኢትዮጵያ በአሁኑ ወቅት በአጠቃላይ ከአንድ ሚሊዮን በላይ ስደተኞችንና ጥገኝነት ጠያቂዎችን ተቀብላ፣ ሰብዓዊና መሠረታዊ አገልግሎቶችን በማሟላት እያስተናገደች መሆኗን ገልጸዋል፡፡

ስደተኞቹ በተለያዩ ክልሎች ውስጥ በሚገኙ ሰባት ማስተባበሪያ ጽሕፈት ቤቶች ሥር ባሉ 26 የስደተኞች መጠለያ ካምፖች ውስጥ ተጠልለው እንደሚገኙ ዋና ዳይሬክተሯ ተናግረዋል፡፡

‹‹በዓለም ላይ ሰብዓዊ ቀውሶች በመባባሳቸው ምክንያት ከ70 በመቶ በላይ የሚሆነውን የምግብ ዕርዳታ ሲያቀርብ የነበረው የአሜሪካ ዓለም ተራድኦ ድርጅት እጥረት ስለገጠመው፣ ሥርጭቱ ላለፉት ስድስት ወራት ተቋርጦ መቆየቱ ይታወሳል፤›› ያሉት ወ/ሮ ጠይባ፣ በአሁኑ ወቅት የአሠራር ሒደቱ እንዲቀየር በመፈለጉ፣ በስደተኞችና ተመላሾች አገልግሎት ይከናወን የነበረው ሥርጭት እንዲቆምና በአዲስ አሠራር ከሌሎች ተቋማት ጋር ለመሥራት ስምምነት መደረጉን አስታውቀዋል፡፡

የምግብ ዕርዳታ ሥርጭቱ ለምን እንደተቋረጠ ከጋዜጠኞች ለቀረበላቸው ጥያቄ፣ ‹‹የአሜሪካ ዓለም አቀፍ ተራድኦ ድርጅት የምግብ ዕርዳታ ሥርጭቱን በጥርጣሬ ሲመለከተው ነበር፤›› ያሉት ወ/ሮ ጠይባ፣ ነገር ግን ድርጅቱ ተፈጸሙ ያላቸውን ዝርፊያዎችና አንዳንድ ችግሮች መንግሥት ሙሉ በሙሉ ባይቀበላቸውም፣ የማስተዳደር ጉድለትና ስርቆትን ጨምሮ አንዳንድ ብልሹ አሠራሮች ተከስተው እንደነበር ተናግረዋል፡፡ ችግሩም ዓለም አቀፋዊና በማንኛውም አገር ሊያጋጥም የሚችል ነው ሲሉ ምላሽ ሰጥተዋል፡፡

‹‹ድርጅቱም እንደሚለው ሳይሆን እኛ እንደምንለው በሥርጭቱ ወቅት የተከሰቱ ጥቃቅን ችግሮች ሲሆኑ፣ ችግሩን ለማስተካከል ዕርጃዎች ተወስዷል፤›› ሲሉ ወ/ሮ ጠይባ አብራርተዋል፡፡

ኃላፊነት በጎደላቸው ከፍተኛ አመራሮችና ሠራተኞች አማካይነት የተፈጠሩ ችግሮችን እንደነበሩ አክለው፣ ድርጊቱን የፈጸሙ ሠራተኞችን ማባረራቸውን  ገልጸዋል፡፡

‹‹ዕርዳታው መቋረጡ ብቻ ሳይሆን ለምን ተቋረጠ?›› የሚለውን ዋና ምክንያት መነሻ በማድረግ ስህተቶቹ እንዳይደገሙ በጥንቃቄ እየተሠራ መሆኑን አክለዋል፡፡

‹‹ይህ ሥራ ከእጃችን ወጥቷል፡፡ ከዚህ በኋላ የሥርጭት ሒደቱን የሚያከናውኑት ዓለም አቀፍ በጎ አደራጎት ድርጅቶች ናቸው፤›› ያሉት ዋና ዳይሬክተሯ፣ ለዚህም  ስድስት ዓለም አቀፍ ተቋማት ተወዳድረውና ብቃታቸው ታይቶ ጭምር ከዚህ ቀደም በሥርጭት ሒደት ያልተሳተፉ ሰዎች ተመድበው እንደሚረኩበት ተናግረዋል፡፡

ዕርዳታው ተቋርጦባቸው በነበሩ ወራት በምግብ እጥረትና ተያያዥ በሆኑ ምክንያቶች በተከሰቱ በሽታዎች ጉዳቶች መድረሳቸውን አውስተው፣ በጋምቤላ ክልል ተቀስቅሶ የነበረው ግጭትም ከዚሁ ጋር የተያያዘ እንደነበር አብራርተዋል፡፡

በተለይ በጋምቤላና በሶማሌ ክልሎች በሚገኙ የመጠለያ ጣቢያዎች የሞቱ ሰዎች እንዳሉ የጠቆሙት ወ/ሮ ጠይባ የሟቾችን ቁጥር ከመግለጽ ተቆጥበዋል፡፡

እ.ኤ.አ. በታኅሳስ 2023 በጄኔቫ በሚካሄው የስደተኞች ጉባዔ ላይ ለመሳተፍ ኢትዮጵያ ከወዲሁ ዝግጅት እያደረገች መሆኑን አስታውቀዋል፡፡ 

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ለሰው ልጅ መብት መከበር ስናወራ 75 ዓመት ሞላን!

በገነት ዓለሙ ዓለም ስለሰብዓዊ መብቶች ሲያወራ፣ ሲምል፣ ሲገዘት፣ ሲፈጠም፣ ቃል...

ካልተማከለ የካፒታል ገበያ ወደ ዘመናዊና የተደራጀ የሰነደ ሙዓለ ንዋዮች ገበያ

በእሱፈቃድ ተረፈ በአገራችን የካፒታል ገበያ አዋጅ መውጣትን ተከትሎ የተማከለ የሰነደ...

ለማይቀረው ምክክርና ድርድር እንዘጋጅ

በያሲን ባህሩ  የዘመናዊት ኢትዮጵያ ፖለቲካ ውዝግብ በትንሹ የአንድ ምዕተ ዓመት...

ደንብ አስከባሪዎች ደንብ ያክብሩ!

በአዲስ አበባ ከተማ ደንብ አስከባሪዎች፣ ሌሎች የፀጥታ አካላት፣ እንዲሁም...