Monday, December 11, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊአዳዲስ የሚዲያ ፖሊሲዎች የተዘጋጁ ቢሆንም የአፈጻጸም ችግር እንዳለባቸው ተጠቆመ

አዳዲስ የሚዲያ ፖሊሲዎች የተዘጋጁ ቢሆንም የአፈጻጸም ችግር እንዳለባቸው ተጠቆመ

ቀን:

ኢትዮጵያ ባለፉት ዓመታት አዳዲስ የሚዲያ ፖሊሲዎችና ሕጎችን ማውጣትን ጨምሮ የተለያዩ ለውጦች ቢደረጉም፣ የጋዜጠኞች እስርና እንግልት መቆም እንዳልቻለ የኢትዮጵያ ሚዲያ ሴክተር ኢሊያንስና የኢትዮጵያ ብዙኃን መገናኛ ምክር ቤት ከባለድርሻ አካላት ጋር ጥቅምት 8 ቀን 2016 ዓ.ም. ባካሄዱት የውይይት መድረክ ላይ ተገለጸ፡፡

ባለፉት አምስት ዓመታት የመገናኛ ብዙኃን ፖሊሲዎች መውጣታቸው ጥሩ ቢሆንም፣ ነገር ግን የጋዜጠኞችን ደኅንነት ከማስጠበቅና መረጃን ለመገናኛ ብዙኃን ተደራሽ ከማድረግ አኳያ የተለያዩ ችግሮች እንደሚስተዋሉ በመድረኩ ላይ ተነስቷል፡፡

‹‹ጋዜጠኛ ካጠፋ መቀጣት አለበት›› ያሉት የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ምክር ቤት ዋና ሰብሳቢ አቶ አማረ አረጋዊ፣ መቀጣት ያለበት ፍርድ ቤት ቀርቦ እንጂ፣ ፍርድ ቤት ሳያውቀው መደረጉ በሕግ ማስከበር በኩል የምናየው ድክመት ነው ብለዋል፡፡

‹‹ጋዜጠኛው አጥፍተሃል ተብሎ ሲታሰርም ሆነ ፍርድ ቤት ሲቀርብ ሳይሆን ዕቃው ተወሰደ፣ ቢሮው ተዘጋ ሲባል ነው የምንሰማው፤›› ያሉት አቶ አማረ፣ ከሚዲያ ነፃነት ጋር ተያይዞ የሚቀርቡ ችግሮች ሳይሆኑ የሕግ አፈጻጸም ክፍተቶች እንደሚስተዋሉ ተናግረዋል፡፡

ለአብነትም በሕገ መንግሥቱ የተቀመጠው የሚዲያ ነፃነት የሚያሳየው ››ሐሳብን የመግለጽ መብት መኖሩን ብቻ ሳይሆን፣ ጋዜጠኛው ሐሳቡን ሲገልጽ በደልና ጥቃት እንዳይደርስበት መንግሥት ከለላ የማድረግ ግዴታ አለበት፤›› እንደሚል አቶ አማረ አስታውሰዋል፡፡

ነገር ግን አሁን በተግባር እየታየ ያለው እንኳንስ ከለላ መሆን ሳይሆን ጥቃት ነው የምናየው ብለዋል፡፡

ሌለው ትልቁ ችግር ብለው ያነሱት አቶ አማረ፣ በቂ መረጃ የማግኘት ችግር እንደሆነ ገልጸው፣ የመንግሥት ሚዲያዎችና የግል ሚዲያዎች እኩል መረጃ የማግኘት ዕድል እንደሌላቸው ተናግረዋል፡፡

በአጠቃላይ በሚዲያ ዘርፍ እየታዩ ያሉ ችግሮችን ለመቅረፍ በቅድሚያ ሚዲያው ከጥላቻ ንግግር ተላቆ ጋዜጠኞች ያላግባብ ሲታሰሩ በጋራ መከላከል እንዳለበትና በጥፋታቸው የሚታሰሩትን ደግሞ ምንድነው ያጠፉት ብሎ መጠየቅ ያስፈልጋል ብለዋል፡፡

ሚዲያው ትልቅ ተግዳሮት እየገጠመው እንደሆነ የተናገሩት ደግሞ በዘርፉ እየሠሩ ያሉት አቶ ኡስማን መሐመድ ናቸው፡፡

አቶ ኡስማን ተግዳሮቶች ብለው ካነሷቸው ጉዳዮች መካከልም ከመረጃ ዕጦት፣ ከገንዘብ ችግርና ከመንግሥትና ከፀጥታ አካላት ጋር በተገናኘ ያሉ ክፍተቶች ተጠቃሽ ናቸው ብለዋል፡፡

‹‹የሚዲያ ነፃነት ትናንትም ዛሬም የለም›› ያሉት አቶ ኡስማን በብዛት እየታየ ያለው መንግሥትን የሚያሞግሱ ሚዲያዎችና አክቲቪስቶች የበረከቱበት ነው ብለዋል፡፡

የኅትመት ሚዲያዎች ብዙዎቹ የተዘጉት ገንዘብ በማጣታቸው ብቻ ሳይሆን ነፃነቱና ምኅዳሩ ምቹ ባለመሆኑ ነው ሲሉ አብራርተዋል፡፡

በሚዲያ ዘርፍና በሰብዓዊ መብቶች ዙሪያ አማካሪ የሆኑት ኤልሳቤጥ ሳሙኤል (ዶ/ር) የኢትዮጵያ ሚዲያ ሴንተር አልያንስን በሚመለከት አካሄድኩት ባሉት ጥናት አንዳንድ ጋዜጠኞች ሙያቸውን አክብረው አለመሥራት ወይም የሙያ ብቃትና አተገባበር በሚፈልገው ደረጃ አለመሆናቸውን ተናግረዋል፡፡

በሌላ በኩል ጋዜጠኞች በተለይ ዲጂታል ቴክኖሎጂን የመጠቀም ዕውቀታቸው አናሳ መሆኑንና ለዚህም የተለያዩ ምክንያቶች በጥናቱ ላይ ተመልክቷል፡፡

በሌላ በኩል በሕግና በፖሊሲ ማዕቀፎችን በተመለከተ የሕጉ መርቀቅ እንዳለ ሆኖ ያመጡት ለውጥ የተዳሰሰ ሲሆን፣ የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን ነፃ ተቋም ሆኖ ተጠሪነቱ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መሆኑ ጥሩ ጅማሬ ነው ተብሏል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ለሰው ልጅ መብት መከበር ስናወራ 75 ዓመት ሞላን!

በገነት ዓለሙ ዓለም ስለሰብዓዊ መብቶች ሲያወራ፣ ሲምል፣ ሲገዘት፣ ሲፈጠም፣ ቃል...

ካልተማከለ የካፒታል ገበያ ወደ ዘመናዊና የተደራጀ የሰነደ ሙዓለ ንዋዮች ገበያ

በእሱፈቃድ ተረፈ በአገራችን የካፒታል ገበያ አዋጅ መውጣትን ተከትሎ የተማከለ የሰነደ...

ለማይቀረው ምክክርና ድርድር እንዘጋጅ

በያሲን ባህሩ  የዘመናዊት ኢትዮጵያ ፖለቲካ ውዝግብ በትንሹ የአንድ ምዕተ ዓመት...

ደንብ አስከባሪዎች ደንብ ያክብሩ!

በአዲስ አበባ ከተማ ደንብ አስከባሪዎች፣ ሌሎች የፀጥታ አካላት፣ እንዲሁም...