Monday, December 11, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊአከርካሪ አጥንትና ፈተናው

አከርካሪ አጥንትና ፈተናው

ቀን:

የአከርካሪ አጥንት ሰዎች ቆመው እጃቸውን ወደ ላይ እንዲዘረጉ የሚያስችላቸው እንኳ ቢሆንም፣ ለሁልጊዜ የሚቆየውን የጀርባ ሕመምንም ይዞ ይመጣል፡፡ የጀርባ ሕመም ሸክሙ አስደንጋጭ ነው፡፡ በዓለም አቀፍ ደረጃ አንድ ቢሊዮን ሰዎች በአንድ ዓይነት የአከርካሪ ሕመምና የአካል ጉዳት እንደሚሰቃዩ ይገመታል፡፡

ለዚህ ነው፣ የአካል ብቃት እንቅስቃሴን አለማድረግ ለጀርባ ሕመም መንስዔ ከሆኑት መካከል አንዱ በመሆኑ፣ የዘንድሮ የዓለም የአከርካሪ አጥንት ቀን መሪ ቃል፣ ‹‹አከርካሪህን አንቀሳቅስ›› የሚለው የሆነው፡፡

በየዓመቱ ኦክቶበር 16 ቀን (ጥቅምት 6 በየአራት ዓመቱ ጥቅምት 5)፣ የዓለም አከርካሪ አጥንቅ ቀን መከበሩን ተከትሎ በአዲስ አበባ በጤና ሚኒስቴር አማካይነት ቀኑ ታስቦ ውሏል፡፡

አከርካሪ አጥንትና ፈተናው | Ethiopian Reporter | ሪፖርተር

በኃይሌ ግራንድ ሆቴል በተዘጋጀው መድረክ ላይ የጤና ሚኒስቴር የሜዲካል አገልግሎት መሪ ሥራ አስፈጻሚ ኢሉባቡር ቡኖ (ዶ/ር) እንደተናገሩት፣ ከኢትዮጵያ ሕዝብ መካከል 54 በመቶ ያህሉ በአከርካሪ አጥንት ሕመም በተለያየ ደረጃና መጠን ይሰቃያሉ፡፡ የአብዛኛዎቹ ሕመም ግን በቀላሉ መከላከል እንደሚቻል፣ ሁሉም ሰው በተለይ በሥራ ቦታ የአከርካሪ አጥንቱን ደኅንነት መንከባከብ እንዳለበት ጠቁመዋል፡፡

ይህም የሚሆነው በሥራ ቦታ ላይ ሠራተኞች ቀጥ ብለው እንዲቀመጡና በሚያደርጉት እንቅስቃሴ ሁሉ የአከርካሪቸውን አጥንት ጤና መጠበቅ እንደሚያስፈልግ አስረድተዋል፡፡

ጥናታዊ መረጃዎች እንደሚያሳዩት፣ ለብዙዎች የጀርባና ከአጥንት ሕመም ሰበቡ ተገቢ ያልሆነ አቀማመጥ ነው፡፡ ለረዥም ጊዜ ከመቀመጥ መቆጠብ ሕመሞችን ያስታግሳል፡፡ ከፍተኛ ተረከዝ ያላቸው ጫማዎችን አለመጠቀም፣ በእጅ የሚያዙ የሞባይል (ተንቀሳቃሽ) ስልኮችና የኤሌክትሮኒክስ መሣሪያዎች ሱስ በአንገት ላይ ከፍተኛ ጫናን ይፈጥራሉ፡፡ ክብደቶችን ማንሳት፣ ከባባድ ዕቃዎችን መጎተት ወይም መግፋት የዲስክ መንሸራተት ሊከሰት ይችላል፡፡

የዘንድሮው አከርካሪህን አንቀሳቅስ መሪ ቃል በሁሉም አገሮች በሁሉም የዕድሜ ክልል ውስጥ ያሉ ሰዎች ንቁ እንዲሆኑና የአከርካሪ ጤንነታቸውን በእንቅስቃሴ እንዲደግፉ ይተጋል።

የዓለም የአከርካሪ አጥንት ቀን ዋነኛ ግቡ፣ ማኅበረሰቡ በሚያከናውናቸው ተግባራት ጤናማ አቀማመጥ እንዲከተል ግንዛቤ ማስጨበጥ መሆኑን የተናገሩት የጤና ሚኒስትር ደኤታ አየለ ተሾመ (ዶ/ር)፣ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ አለማድረግ ለአከርካሪ ሕመምና ለአካል ጉዳት መንስዔ እንደሚሆንም ጠቁመዋል።

እንደ አገር ለሰዎች የሥራ ዕድል የሚፈጥረውን የኮንስትራክሽን ዘርፍ ምቹ በማድረግ፣ የሰው ኃይሉ ለአከርካሪ አጥንት ሕመም ያለበትን ተጋላጭነት ለመቀነስ የሚያስችል የማስገንዘቢያ ሥራን የከተማና ቤቶች ልማት ሚኒስቴር ከጤና ሚኒስቴር ጋር በትብብር እንዲሠራም ጥሪ አቅርበዋል።

እንደ ሚኒስትር ደኤታው አባባል፣ ከሁለት አሠርታት ወዲህ የኢትዮጵያ የሰው በሕይወት የመኖር ዕድሜ ከ40 ወደ 69 አሻቅቧል፡፡ ዕድሜ በጨመረ ቁጥር ደግሞ የአከርካሪ አጥንት ችግር መከሰቱ አይቀርም፡፡ ሁልጊዜ በእንቅስቃሴ ላይ ያሉ አርሶ አደሮች ለችግሩ እንደማይጋለጡ፣ በይበልጥ ተጋላጭ የሚሆኑት ግን ቢሮ ውስጥ ቁጭ ብሎ የሚሠሩ ናቸው፡፡

ከዚህ ዓይነቱ ችግር ለመላቀቅ ወይም ተጋላጭ ላለመሆን ቀጥ ብሎ መቀመጥና መንቀሳቀስ፣ ለተወሰነ ደቂቃ ያህል የሰውነት አካላትን ማሳሳብ፣ ውኃ የመጠጣትን ልምድ ማዘውተር፣ በኮምፒዩተር አጠቃቀም ላይ ጎንበስ ከማለት መጠበቅ በእጅጉ አስፈላጊ መሆኑን ሚኒስትር ደኤታው ሳይገልጹ አላለፉም፡፡

‹‹የኮንስትራክሽን ቦታዎች ከፍታ ያለው፣ ለመሥራትና ለመንቀሳቀስ የማይመቹና በከፍተኛ ሁኔታ ለአደጋ የሚያጋልጡ ናቸው፤›› ያሉት ደግሞ የከተማና መሠረተ ልማት ኮንስትራክሽን ሚኒስትር ደኤታ ወንድሙ ሰታ (ኢንጂነር) ናቸው፡፡

ዘርፉ ከግብርና ቀጥሎ ሰፊ የሥራ ዕድል የመፍጠር አቅም እንዳለው፣ በዚህም የተነሳ አብዛኛው ወጣትና ጎልማሳ በዘርፉ ተሰማርቶ ሕይወቱን እየመራበት መሆኑን አስረድተዋል፡፡

ሚኒስቴሩ ከዓለም ባንክ በተገኘ የገንዘብ ድጋፍ ከባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ጋር የሥራ ላይ ደኅንነትንና ጤናን የተመለከተ የሕግ ማዕቀፍ ለማዘጋጀት የሚያስችል ምርምር እያከናወነ መሆኑን አመልክተዋል፡፡

በዚሁ መድረክ የአካል ጉዳት ደርሶባቸውና የአከርካሪ አጥንታቸው ተጎድቶ ተገቢውን ሕክምና በማግኘት ሕልማቸውን ለማሳካት የበቁ እማኞች አሁን ያሉበትን ሁኔታ ከዚህ ቀደም ከነበረው ጋር በማነፃፀር ውይይት ተደርጓል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ለሰው ልጅ መብት መከበር ስናወራ 75 ዓመት ሞላን!

በገነት ዓለሙ ዓለም ስለሰብዓዊ መብቶች ሲያወራ፣ ሲምል፣ ሲገዘት፣ ሲፈጠም፣ ቃል...

ካልተማከለ የካፒታል ገበያ ወደ ዘመናዊና የተደራጀ የሰነደ ሙዓለ ንዋዮች ገበያ

በእሱፈቃድ ተረፈ በአገራችን የካፒታል ገበያ አዋጅ መውጣትን ተከትሎ የተማከለ የሰነደ...

ለማይቀረው ምክክርና ድርድር እንዘጋጅ

በያሲን ባህሩ  የዘመናዊት ኢትዮጵያ ፖለቲካ ውዝግብ በትንሹ የአንድ ምዕተ ዓመት...

ደንብ አስከባሪዎች ደንብ ያክብሩ!

በአዲስ አበባ ከተማ ደንብ አስከባሪዎች፣ ሌሎች የፀጥታ አካላት፣ እንዲሁም...