Wednesday, December 6, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ዓለምየመካከለኛው ምሥራቅ የግጭት እምብርት

የመካከለኛው ምሥራቅ የግጭት እምብርት

ቀን:

በእስራኤል እና በፍልስጤም ታጣቂ ቡድን ሀማስ መካከል ለዓመታት በተለያዩ ጊዜያት ጦርነቶችና ግጭቶች ተከስተዋል፡፡ ከአሥር ቀናት በፊት ሐማስ በእስራኤል ላይ የፈጸመው ድንገተኛ የሮኬት ጥቃትም ድንገት የተፈጠረና የተፈጸመ ሳይሆን ለዓመታት የተጠራቀመ የመሬትና የፍትሕ ይገባኛል ጥያቄ የፈጠረው ነው፡፡

ዛሬ ላይ እስራኤልና ሀማስ ወደለየለት ጦርነት የገቡበት ምክንያትም፣ እስራኤል ፍልስጤም ይገባኛል በምትለው ሥፍራዎች ላይ በርካታ ሠፈራዎችን ማካሄዷ፣ በተለያዩ ጊዜያት በፍልስጤሞች ላይ ይፈጸማሉ የሚባሉት ጥቃቶች፣ በዓረቡ ዓለምና በእስራኤልና ወዳጆቿ መካከል ያለው የፖለቲካ ውጥረትና አለመግባባት የፈጠሩት ነው፡፡

የፍልስጤም ታጣቂ ቡድንና ለጋዛ ደግሞ የፖለቲካ ፓርቲ የሆነው ሀማስ፣ በተለያዩ ጊዜያት ከእስራኤል ጋር የሚገባበትና በሺዎች የሚቆጠሩ ንፁኃን ጭምር የሚያልቁበት፣ መሠረተ ልማት የሚወድሙበትና ሰብዓዊ መብት ጥሰት የሚፈጸሙበት ከሠፈራ ጋር የተያያዙ ጦርነቶች ተካሂደዋል፡፡

ሰሞኑን በእስራኤልና በሀማስ መካከል እየተካሄደ ያለው ጦርነት መነሻውም ይኸው እስራኤል በምሥራቅ ኢየሩሳሌም እያካሄደች ያለችው የሠፈራ ፕሮግራም መሆኑን ኤንፒአር በድረ ገጹ አስፍሯል፡፡

የመካከለኛው ምሥራቅ የግጭት እምብርት | Ethiopian Reporter | ሪፖርተር
ሀማስ ወደ እስራኤል 5,000 ሮኬት ተኩሷል፣ ከሺሕ በላይ ሞተዋል (ኒውዮርክ ታይምስ)

‹‹እስራኤል በምሥራቅ ኢየሩሳሌም ሼህ ጃራ የሚኖሩ ፍልስጤማውያንን በግድ ከቦታቸው እያፈናቀለች ነው›› የሚል ምክንያት ተሰጥቶት የተጀመረው ጦርነትም እስካሁን ከሁለቱም ወገኖች ከሁለት ሺሕ በላይ ሰዎች እንዲሞቱና በርካታ መሠረተ ልማቶች እንዲወድሙ ምክንያት ሆኗል፡፡

አልጀዚራ እንደዘገበው፣ በእስራኤልና በሀማስ መካከል ጦርነት ከተጀመረበት ከመስከረም 26 እስከ ጥቅምት 5 ቀን 2016 ዓ.ም. በጋዛ በኩል 2,808 ሰዎች ሲገደሉ፣ ከአሥር ሺሕ በላይ ጉዳት ደርሶባቸዋል፡፡

በእስራኤል ቁጥጥር ሥር በሚገኘው ዌስት ባንክ 57 ሲገደሉ፣ 5,200 ደግሞ ጉዳት ደርሶባቸዋል፡፡ ከእስራኤል ወገን 1,400 ሲገደሉ፣ 3,400 ጉዳት ደርሶባቸዋል፡፡ ከእነዚህ ውስጥ ደግሞ ብዙኃኑ ሴቶች፣ ሕፃናትና በጦርነቱ ተሳትፎ ያልነበራቸው ንፁኃን ናቸው፡፡ እስራኤልም ንፁኃንና ወታደሮች በሀማስ ታግተውብኛል ስትል ተሰምታለች፡፡

እስራኤል በስድስት ቀናት ብቻ 6,000 ቦምቦችን በጋዛ ሰርጥ ስታዘንብ፣ ሀማስ ወደ እስራኤል የተኮሳቸው ሮኬቶችም 5,000 ናቸው ተብሏል፡፡

በእስራኤልና በፍልስጤም መካከል ያሉ ዋና ችግሮች ምንድናቸው?

እስራኤልና ፍልስጤም የማይግባቡባቸው በርካታ ጉዳዮች አሉ፡፡ እስራኤል የምትባል አገር በጉልበት በፍልስጤማውያን ምድር የተፈጠረች ናት የሚለው አከራካሪ አጀንዳ፣ በሁለቱ በኩል ብቻ ሳይሆን የዓረቡን ዓለምና ምዕራባውያኑን ጭምር የከፋፈለ ነው፡፡

በፍልስጤም ስደተኞች ላይ የሚፈጸም በደል እስራኤና ፍልስጤምን ከማያግባቡ ነጥቦች የሚጠቀስ ሲሆን፣ አይሁዳውያንን በዌስት ባንክ ማስፈር ትክክል ነው? ወይስ አይደለም? የሚለውም በሁለቱ አገሮች ስምምነት ያልተደረሰበት አጀንዳ ነው፡፡

ኢየሩሳሌም የማናት? ሁለቱ አገሮች ሊካፈሉዋት ይገባል? ወይስ በአንዱ አገር መጠቅለል አለባት? እንዲሁም የፍልስጤም ግዛት እንደ እስራኤል መፈጠር አለበት? የሚለው እስካሁን መቋጫ ያልተገኘላቸውና ጦር እያማዘዙ የሚገኙ አጀንዳዎች ናቸው፡፡

እነዚህን ችግሮች ለመፍታት ምን ጥረት ተደርጓል?

በእስራኤልና ፍልስጤም መካከል እ.ኤ.አ. ከ1990ዎቹ እስከ 2010 ድረስ ሄደት መጣ የሚል የሰላም ውይይት ተደርጓል፡፡

በውይይቶቹ የመጀመርያ ጊዜያት አዎንታዊ ውጤቶች ተገኝተዋል፡፡ ፍልስጤም እስራኤልን እንደ አገር፣ እስራኤልም ታሪካዊ ጠላቴ ብላ የምትፈርጀውን የፍልስጤም ነፃ አውጪ ድርጅት (ፒኤልኦ) የተቀበሉበት ስምምነት ተደርጓል፡፡ ይህ በእስራኤልና በፍልስጤም መካከል የተደረገው የኦስሎ ስምምነት በወቅቱ የእስራኤል ተቀናቃኝ ፓርቲ መሪ የነበሩት ቤንያሚን ናታንያሁ ‹‹የኦስሎ ስምምነት ለእስራኤል የሞት ሥጋት ነው፤›› ካሉ በኋላ ደፍርሷል፡፡

እስራኤል በእስራኤል ቁጥጥር ሥር በሚገኘው የፍልስጤም ግዛት አይሁዶችን  ማስፈሯና የሠፈራ ፕሮጀክቶችን ማፋጠኗ በሁለቱ መካከል መታየት የጀመረውን ሰላም እንዲደፈርስ ምክንያት ሆኗል፡፡

የፍልስጤም ታጣቂ ቡድን ሀማስም አጥፍቶ ጠፊ ወደ እስራኤል መላክ መጀመሩ የሰላም ስምምነቱ አስገኝቶ የነበረውን ዕፎይታ ቀልብሷል፡፡

እ.ኤ.አ. ከ2000 በኋላ በ2003 የተደረጉ የሰላም ጥረቶችም ለውጥ አላመጡም፡፡ በ2014 በእስራኤልና በፍልስጤም መካከል በዋሽንግተን የተደረገ ውይይትም ሰላም አላመጣም፡፡

በአሜሪካ የቀድሞ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ዘመን፣ ‹‹የምዕት ዓመቱ ስምምነት›› የተባለ የሰላም ዕቅድ በአሜሪካ ተነድፎ የነበረ ቢሆንም፣ ፍልስጤማውያኑ ‹‹ለአንድ ወገን ያደላ ነው›› በሚል ሳይቀበሉት ቀርተዋል፡፡

ሰላም ማውረድ ባልቻሉት እስራኤልና ፍልስጤም ምክንያትም በሚሊዮን የሚቆጠሩ ዜጎች በሥጋት ጥላ ውስጥ እንዲኖሩ አስገድዷል፡፡

በሌላ በኩል ደግሞ አሜሪካ፣ የአውሮፓ ኅብረትና ምዕራባውያን ሀማስን እየኮነኑ ነው፡፡ የእስራኤል ቀኝ እጅ አሜሪካ ከዚህ ቀደም በቢሊዮን ዶላር የሚቆጠር የውትድርናና የኢኮኖሚ ድጋፍ ከማድረጓ ባለፈም፣ ለአሁኑ ጦርነት ተጨማሪ የጦር መሣሪያና ቁሳቁስ እንደምትልክ አስታውቃለች፡፡

ሩሲያና ቻይና ሀማስን ከመኮነን ይልቅ ግጭቱን ለማስቆም ሁለቱንም አገሮች ማማከርን መርጠዋል፡፡ የሀማስ ደጋፊ ኢራን በአሁኑ ጦርነት ከጀርባ እንደሌለችበት ብትገልጽም፣ የሀማስ ደጋፊ መሆኗ ግን ይታወቃል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ታዋቂው የኤሌክትሮኒክስ ብራንድ አይቴል የስትራቴጂ ለውጥ አካል የሆነውን አዲስ አርማ እና መለዮ ይፋ አደረገ።

በአለማችን ታዋቂ ከሆኑት የኤሌክትሮኒክስ ብራንዶች መካከል አንዱ የሆነው እና...

የጠቅላላ ጉባኤ ስብሰባ ጥሪ ለሸገር አነስተኛ የፋይናንስ ተቋም አ.ማ ባለአክሲዮኖች በሙሉ

ለሸገር አነስተኛ የፋይናንስ ተቋም አ.ማ ባለአክሲዮኖች በሙሉ የሸገር አነስተኛ የፋይናንስ...

[የክቡር ሚኒስትሩ ጸሐፊ፣ የሌላ ሚኒስትር ጸሐፊ ከሆነችው የቅርብ ወዳጇ ጋር በስልክ እየተጨዋወቱ ነው]

አንቺ ግን ምን ሆነሽ ነው? ጠፋሁ አይደል? ጠፋሁ ብቻ?! ምን ላድርግ ብለሽ...

በሱዳን ላይ ያጠላው የመከፋፈል ዕጣና ቀጣናዊ ተፅዕኖው

የሱዳን ጦርነት ስምንተኛ ወሩን እያገባደደ ይገኛል፡፡ ጄኔራል አብዱልፈታህ አልቡርሃን...