Monday, December 11, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ዜናኢትዮጵያ የአሥር ዓመት ዕቅዷን ከቻይና ቤልት ኤንድ ሮድ ኢንሼቲቭ ጋር ለማሰናሰል ተስማማች

ኢትዮጵያ የአሥር ዓመት ዕቅዷን ከቻይና ቤልት ኤንድ ሮድ ኢንሼቲቭ ጋር ለማሰናሰል ተስማማች

ቀን:

ኢትዮጵያ የአሥር ዓመት የልማትና የአገር በቀል የኢኮኖሚ ሪፎርም ዕቅዷን ከቻይና ‹‹ቤልት ኤንድ ሮድ ኢንሼቲቭ›› ጋር አሰናስላና አስማምታ ለመፈጸም ተስማማች፡፡ በአዲስ አበባ የሚገኘው የቻይና ኤምባሲ ትናንት ጥቅምት 6 ቀን 2016 ዓ.ም. ያወጣው መግለጫ እንደሚያመለክተው፣ ኢትዮጵያ ይህን ስምምነት ማስፈጸም ለመጀመር ዝግጁ መሆኗን ገልጻለች፡፡

ኢትዮጵያ የልማት ዕቅዶቿን ከ‹‹ቤልት ኤንድ ሮድ ኢንሼቲቭ›› ጋር በማሳለጥ ዘርፈ ብዙ ጥቅም እንደምታገኝ የተገለጸ ሲሆን፣ ቻይና ተጨማሪ መዋዕለ ንዋይ በኢንዲስትሪ ፓርኮችና በልዩ የኢኮኖሚ ዞኖች (Special Economy Zones) ፈሰስ እንደምታደርግ በስምምነቱ ተገልጿል፡፡

ቻይና የኢንዱስትሪ ፓርኮች፣ ልዩ ኢኮኖሚ ዞን፣ ባቡርና ሌሎች ግንባታዎች በኢትዮጵያ እንዲደረጉ ተጨማሪ ድጋፍ እንደምታደርግ ተገልጿል፡፡ ከሰው ኃይል ልማት እስከ ፖለቲካና ፀጥታ ትብብሮች እንደሚደረጉ መግለጫው አትቷል፡፡

ሁለቱ አገሮች ስምምነቱን ያደረጉት፣ ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) አሥረኛ ዓመቱ እየተከበረ ባለው የቻይና ‹‹ቤልት ኤንድ ሮድ ኢንሼቲቭ›› ላይ ለመሳተፍ ቤጂንግ ከደረሱና ከፕሬዚዳንት ዢን ፒንግ ጋር ትናንት ከተገናኙ በኋላ ነው፡፡

በዚህ ቆይታቸው ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አሥራ ሁለት የመግባቢያ ሰነዶችና ሁለት የፍላጎት መግለጫዎች በሁለቱ አገሮች መሪዎች መካከል እንዲፈረሙ መደረጋቸው ተገልጿል፡፡ የስምምነቶቹ ዝርዝር በይፋ ባይገለጹም ቻይና ለኢትዮጵያ ተጨማሪ የዕዳ ስረዛን ታደርጋለች ተብሎ ይጠበቃል፡፡

በተለይ ፕሬዚዳንት ዢንፒንግና ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ (ዶ/ር) ትልቅ ዕርምጃ ሲሉ ያሞካሹት ስምምነት፣ የሁለቱ አገሮች ዲፕሎማሲያዊ ስምምነት ከ‹‹አጠቃላይ›› ወደ ‹‹የማይለዋወጥ›› (Allweather) ከፍ ማድረጋቸውን ነው፡፡ ይህም ማለት የኢትዮጵያና ቻይና ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ከእንግዲህ በማንኛውም ሁኔታ በክፉም በደጉም አይቀያየርም ማለት ይሆናል፡፡ እንዲህ ዓይነት ግንኙነት እንዲፈጠሩ ቻይና የምትፈቅደው በጣም ቅርቧ ለሆኑ የተወሰኑ አገሮች ነው፡፡

ቻይና በ‹‹ቤልት ኤንድ ሮድ ኢንሼቲቭ›› አፍሪካን፣ መካከለኛው ምሥራቅን፣ አውሮፓንና እስያን በየብስ፣ በአየርና ውቅያኖስ በመሠረተ ልማት ለማስተሳሰር እየሠራች ሲሆን፣ ምዕራባውያ ግን ይኼን እንደ ልማት ዕቅድ ብቻ ሳይሆን እንደ ፖለቲካዊ ፕሮጀክት ይቆጥሩታል፡፡

ይኼንኑ የቻይናን ጥረት ለመቀልበስ ያስችላል ያሉትን ፕሮጀክት አሜሪካና አጋሮቿ አስጀምረዋል፡፡ ህንድን፣ አፍሪካን፣ መካከለኛው ምሥራቅንና አውሮፓን የሚያስተሳስረው ይህ የአሜሪካ ፕሮጀክት ግን፣ እስካሁን በፋይናንስ እጥረት ጊዜ እየጠበቀ ነው፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ (ዶ/ር) በበኩላቸው የኢትዮጵያ መንግሥት ታይዋን የቻይና አንድ አካል መሆኗንና ብሔረ አንድነቷን ለማስጠበቅ ቻይና የምትወስዳቸውን ማናቸውም ዕርምጃ እንደምትደግፍ መናገራቸው ተገልጿል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ (ዶ/ር) የ‹‹አንድ ቻይና መርህ›› (One China Principle) ላይ ስምምነት ላይ መድረሳቸውን አዲስ አበባ የሚገኘው የቻይና ኤምባሲ ትናንት ማክሰኞ ባወጣው መግለጫ አስታውቋል፡፡

ምዕራባውያን አገሮች በተለይ አሜሪካ ታይዋን ከቻይና ተገንጥላ ራሷን የቻለች አገር እንድትሆን ድጋፍ ሲያደርጉ የቆዩ ሲሆን፣ ይህም ፍጥጫ ወደ ዓለም አቀፍ ጦርት ሊያመራ ይችላል የሚል ሥጋት መኖሩ ይገለጻል፡፡

ኢትዮጵያ ይህን ውሳኔ በይፋ በድጋሚ ያረጋገጠችው የምዕራባውያን አቻ ኅብረት የሆነውን ብሪክስ (BRICS) ባለፈው ወር ከተቀላቀለች በኋላ ነው፡፡

እንደ መግለጫው ከሆነ ሁለቱም አገሮች በየአካባቢያቸው ሰላምና ፀጥታን ለማስጠበቅ የሚያደርጉትን ጥረት አጠናክረው መቀጠል እንዳለባቸው ተስማምተዋል፡፡

ወትሮም በኢኮኖሚና ንግድ ውጥረት የተሞላው የአሜሪካና ቻይና ግንኙነት፣ ከሩሲያና ዩክሬን ጦርነት ወዲህ እየከረረ በመምጣት በተለይ እንደ አፍሪካ ባሉት ታዳጊ አገሮች ውስጥ የውክልና ጦርነት (Proxy War) እንዳያስከትል ተንታኞች ሥጋት አላቸው፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ለሰው ልጅ መብት መከበር ስናወራ 75 ዓመት ሞላን!

በገነት ዓለሙ ዓለም ስለሰብዓዊ መብቶች ሲያወራ፣ ሲምል፣ ሲገዘት፣ ሲፈጠም፣ ቃል...

ካልተማከለ የካፒታል ገበያ ወደ ዘመናዊና የተደራጀ የሰነደ ሙዓለ ንዋዮች ገበያ

በእሱፈቃድ ተረፈ በአገራችን የካፒታል ገበያ አዋጅ መውጣትን ተከትሎ የተማከለ የሰነደ...

ለማይቀረው ምክክርና ድርድር እንዘጋጅ

በያሲን ባህሩ  የዘመናዊት ኢትዮጵያ ፖለቲካ ውዝግብ በትንሹ የአንድ ምዕተ ዓመት...

ደንብ አስከባሪዎች ደንብ ያክብሩ!

በአዲስ አበባ ከተማ ደንብ አስከባሪዎች፣ ሌሎች የፀጥታ አካላት፣ እንዲሁም...