Sunday, December 10, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ዜናመንግሥት የድርቁን አደጋ እየሸፋፈነ ነው ሲሉ ፓርቲዎች ከሰሱ

መንግሥት የድርቁን አደጋ እየሸፋፈነ ነው ሲሉ ፓርቲዎች ከሰሱ

ቀን:

በኢትዮጵያ የተለያዩ አካባቢዎች እያጋጠመ ያለውን የድርቅ አደጋ መንግሥት ሆን ብሎ እየሸፋፈነ እንደሚገኝ አምስት የተፎካካሪ ፓርቲዎች ገለጹ፡፡ ፓርቲዎቹ ዓርብ ጥቅምት 2 ቀን 2016 ዓ.ም. ባወጡት የጋራ መግለጫ፣ መንግሥት ለራሱ የገጽታ ግንባታ ሲል ሆን ብሎ የሰብዓዊ ቀውሶችን የመሸፋፈን ሥራ ይሠራል ሲሉ ከሰዋል፡፡

የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ)፣ የአማራ ግዮናዊ ንቅናቄ (አግን)፣ አንድ ኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (አኢዴፓ)፣ የኢትዮጵያ ሕዝባዊ አብዮታዊ ፓርቲ (ኢሕአፓ) እና እናት ፓርቲ በጋራ ያወጡት ይህ መግለጫ፣ አገሪቱን ወደተባባሰ ቀውስ ውስጥ በመክተት መንግሥትን ይከሳል፡፡

‹‹የዛሬዎቹ ገዥዎች ካለፉት ገዥዎች አልተማሩም፤›› የሚለው መግለጫው፣ ልክ የአፄ ኃይለ ሥላሴ መንግሥት ለራሱ ገጽታ ሲል የወሎን ረሃብ እንደደበቀው እንዲሁም የደርግ መንግሥት የገጠመውን የድርቅ አደጋ እንደደበቀው ሁሉ የአሁኖቹም አገሪቱ የገጠማትን ድርቅ እየሸፋፈኑ ይገኛል በማለት ነው የሚናገረው፡፡

በሰሜኑ ጦርነት ትግራይ፣ አማራና አፋር ክልሎች በአስከፊ ደረጃ ውድመት ማስተናገዳቸውን መግለጫው ይገልጻል፡፡ አምራች የሆነው ወጣት ኃይል በከፍተኛ ቁጥር በጦርነቱ መማገዱን ይጠቅሳል፡፡ ማምረት በማይቻልበት ሁኔታ ውስጥ ያሳለፈው የሰሜኑ የአገሪቱ ክፍል በተባይ፣ በግሪሳ ወፍና በድርቅ አደጋዎች መጠቃቱን ያነሳል፡፡

ነገር ግን ይህ ተደራራቢ አደጋ ‹‹የብልፅግና ጎዳናችንን ያጠለሻል›› በሚል ምክንያት ሆን ብሎ በመንግሥት የመሸፋፈን አካሄድ ይታያል ይላል፡፡ ዓለም አቀፍ የዕርዳታ ድርጅቶች ይህን ተረድተው በግጭትና በሰብዓዊ ቀውስ ውስጥ ይገኛል ላሉት የኢትዮጵያ ሕዝብ እጃቸውን እንዲዘረጉ ፓርቲዎቹ ጠይቀዋል፡፡

የዕርዳታ አገልግሎት የሚሰጡ ድርጅቶችና ግለሰቦች የሰብዓዊ ቀውስ በደረሰባቸው ቀጣናዎች ገብተው አገልግሎት እንዲሰጡ ሁኔታዎች እንዲመቻቹላቸው ጠይቀዋል፡፡ የኢትዮጵያ ሕዝብም ካለው ላይ በመቁረስ ለተቸገሩ ወገኖች እጁን እንዲዘረጋ ፓርቲዎቹ አክለው ገልጸዋል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ለሰው ልጅ መብት መከበር ስናወራ 75 ዓመት ሞላን!

በገነት ዓለሙ ዓለም ስለሰብዓዊ መብቶች ሲያወራ፣ ሲምል፣ ሲገዘት፣ ሲፈጠም፣ ቃል...

ካልተማከለ የካፒታል ገበያ ወደ ዘመናዊና የተደራጀ የሰነደ ሙዓለ ንዋዮች ገበያ

በእሱፈቃድ ተረፈ በአገራችን የካፒታል ገበያ አዋጅ መውጣትን ተከትሎ የተማከለ የሰነደ...

ለማይቀረው ምክክርና ድርድር እንዘጋጅ

በያሲን ባህሩ  የዘመናዊት ኢትዮጵያ ፖለቲካ ውዝግብ በትንሹ የአንድ ምዕተ ዓመት...

ደንብ አስከባሪዎች ደንብ ያክብሩ!

በአዲስ አበባ ከተማ ደንብ አስከባሪዎች፣ ሌሎች የፀጥታ አካላት፣ እንዲሁም...