Sunday, December 10, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ዓለምየኖቤል ሽልማት የ2023 አሸናፊዎች እነማን ናቸው?

የኖቤል ሽልማት የ2023 አሸናፊዎች እነማን ናቸው?

ቀን:

ዓመታዊው የኖቤል ሽልማት በተለያዩ ዘርፎች ተሸላሚ ያደረጋቸውን ልሂቃንን ባለፈው ሳምንት በተከታታይ ይፋ አድርጓል፡፡

የ2023 የኖቤል ሽልማት የተሰጠው በሰላም፣ በሕክምና፣ በሥነ ጽሑፍ፣ በምጣኔ ሀብት፣ በፊዚክስና በኬሚስትሪ ነው፡፡

የኖቤል የሰላም ሽልማትን ያሸነፈችው ኢራናዊቷ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ናርጅስ መሀመዲ ናት። በእስር ላይ ያለችው ኢራናዊት አክቲቪስት ናርጅስ መሀመዲ በሴቶች መብትና በኢራን የነፃነት ንቅናቄ ባደረገችው ጥረት የኖቤል የሰላም ሽልማት ተሸልማለች።

የኖቤል ሽልማት የ2023 አሸናፊዎች እነማን ናቸው? | Ethiopian Reporter | ሪፖርተር
ኢራናዊት አክቲቪስት ናርጅስ መሀመዲ

የኖርዌይ የኖቤል ኮሚቴ ናርጅስ ‹‹በኢራን ውስጥ በሴቶች ላይ የሚደርሰውን ጭቆና በመታገልና ሰብዓዊ መብቶችንና ነፃነትን ለሁሉም ለማዳበር ባደረገችው ትግል›› ብሎ ነው የሸለማት፡፡

ቢቢሲ እንደዘገበው፣ በሴቶች ላይ የሚደርሰውን ጭቆና በመታገል የምትታወቀው ናርጅስ፣ በኢራን መንግሥት ጥፋተኛ በመባሏ የሰላሳ ዓመት እስራት ተፈርዶባት ወህኒ ከወረደች ሁለት አሠርታትን አስቆጥራለች፡፡ ከእስራቱ በተጨማሪ 154 የጅራፍ ግርፋት እንደተፈረደባት ተዘግቧል። የኖቤል ኮሚቴውም ሽልማቱን ባበረከት ወቅት ‹‹የናርጅስ የጀግንነት ትግል ከፍተኛ ዋጋ አስከፍሏታል፤›› ብሏል።

የኖቤል ሽልማት የ2023 አሸናፊዎች እነማን ናቸው? | Ethiopian Reporter | ሪፖርተር
ሁለቱ የጤና ፕሮፌሰሮች ድሪው ዋይስማንና ካታሊን ካሪኮ

ቢቢሲ ዓለምን የተሻለች ለማድረግ የሚጥሩ 100 ሴቶችን በሚመርጥበት ፕሮግራሙ በዘንድሮው ዝርዝር ውስጥ ናርጅስን አካቷታል።

ከዚህ ቀደም ፓኪስታናዊቷ የትምህርት ተሟጋች ማላላ ዩሳፋዚ እንዲሁም  ጠቅላይ ሚኒስትር ዓቢይ አህመድ (ዶ/ር) ማሸነፋቸው ይታወሳል፡፡

  ሌሎቹ ተሸላሚዎች፣ የሃቫርድ ፕሮፌሰር የሆኑት ክላውዲ ጎልዲን በምጣኔ ሀብት፣ ፒየር አጎስቲኒ፣ ፌሬንክ ክራውዝና አን ኤል ሁሊየር በጋራ በፊዚክስ ‹‹በቁስ አካል ላይ የኤሌክትሮን ዳይናሚክስን በማጥናት፣ በኬሚስትሪ ለሙንጊ ባዌንዲ፣ ሉዊስ ብሩስና አሌክሲ ኢኪም የኖቤል ሽልማትን ተሸልመዋል፡፡

‹‹ለማይናገሩ ሰዎች ድምፅ በሚሰጡ የፈጠራ ተውኔቶቹ›› በሥነ ጽሑፍ የኖቤል ሽልማት የተሸለመው ኖርዌያዊው ደራሲ ጆን ፎሴ ነው፡፡

በሕክምና ዘርፍ ኤምአርኤንኤ የተባለውን የኮቪድ ክትባትን ለመሥራት የሚያስችል ቴክኖሎጂን ላዳበሩ ሁለት ፕሮፌሰሮች ካታሊን ካሪኮና ድሪው ዋይስማን የዚህን ዓመት የኖቤል  ሽልማትን በጋራ አግኝተዋል።

ቢቢሲ እንደዘገበው፣ ቴክኖሎጂው የኮቪድ ወረርሽኝ ከመከሰቱ በፊት በሙከራ ደረጃ ላይ የነበረ ሲሆን፣ አሁን በዓለም በሚሊዮኖች ለሚቆጠሩ ሰዎች ወረርሽኙን ለመከላከል ተስጥቷል። በአሁኑ ጊዜም ካንሰርን ጨምሮ ለሌሎች በሽታዎች ጥቅም ላይ ለማዋል ምርምር እየተደረገበት መሆኑ ተጠቁሟል።

‹‹በሰው ልጅ ዘመናዊ ታሪክ ውስጥ ላጋጠመው ከፍተኛ የጤና ሥጋት ሁለቱ ተሸላሚዎች ቀደም ሲል ባልታየ ሁኔታ ክትባት በማዳበር በኩል አስተዋጽኦ አበርክተዋል፤›› ሲልም የኖቤል ሽልማት ኮሚቴው አስተጋብቷል፡፡ 

ኤምአርኤንኤ የተባለው ቴክኖሎጂ በተለይ በኮቪድ ወረርሽኝ ወቅት በታማሚዎች ውስጥ በሽታውን ለመቋቋምና ለማጥፋት የሚያስችል ሁኔታን በመፍጠር ወሳኝ አስተዋጽኦ ማድረጉን የዘገበው ቢቢሲ፣ ካታሊን ካሪኮ በአሁኑ ጊዜ በሃንጋሪ ዩኒቨርሲቲ፣ ድሪው ዋይስማን ደግሞ በፔንሲልቬኒያ ዩኒቨርሲቲ ፕሮፌሰሮች ሆነው እያገለገሉ ይገኛሉ ብሏል።

የኖቤል የሰላም ሽልማት አሸናፊዋ ናርጅስ አንድ ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር እንደምታገኝ፣ ይህም ካለፈው ዓመት ጋር ሲወዳዳር አሥር በመቶ ብልጫ አለው ያለው የቢቢሲ ዘገባ በተጨማሪም ተሸላሚዎች ዲፕሎማና የኖቤል ኮሚቴው ባለ 18 ካራት ወርቅ ሜዳሊያም ይሸለማሉ።

የኖቤል የሰላም ሽልማት ከተቋቋመበት ከአውሮፓውያኑ 1901 ጀምሮ 110 ግለሰቦች እና 30 ድርጅቶች አሸናፊ ሆነዋል።

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ለሰው ልጅ መብት መከበር ስናወራ 75 ዓመት ሞላን!

በገነት ዓለሙ ዓለም ስለሰብዓዊ መብቶች ሲያወራ፣ ሲምል፣ ሲገዘት፣ ሲፈጠም፣ ቃል...

ካልተማከለ የካፒታል ገበያ ወደ ዘመናዊና የተደራጀ የሰነደ ሙዓለ ንዋዮች ገበያ

በእሱፈቃድ ተረፈ በአገራችን የካፒታል ገበያ አዋጅ መውጣትን ተከትሎ የተማከለ የሰነደ...

ለማይቀረው ምክክርና ድርድር እንዘጋጅ

በያሲን ባህሩ  የዘመናዊት ኢትዮጵያ ፖለቲካ ውዝግብ በትንሹ የአንድ ምዕተ ዓመት...

ደንብ አስከባሪዎች ደንብ ያክብሩ!

በአዲስ አበባ ከተማ ደንብ አስከባሪዎች፣ ሌሎች የፀጥታ አካላት፣ እንዲሁም...